0 Comments
0 Shares
Directory
-
Please log in to like, share and comment!
-
AMHARIC.VOANEWS.COMእጅግ ከፍተኛ የአካባቢ አየር ሙቀት መጠንና የሚያስከትላቸው የጤና ጠንቆችእስከ ኅልፈተ ሕይወት የሚያደርስ ጉዳት እያስከተለ ባለው ከፍተኛ የአካባቢ አየር ሙቀት ሳቢያ የሚመጣው የጤና ሁከት በሁለት እንደሚከፈል ለሞያዊ ትንታኔው የጋበዝናቸው እንግዳችን ዶክተር ነጋ ዓሊ ይናገራሉ። በእንግሊዝኛው አጠራሩ Heat Stroke በመባል የሚታወቀው ሸንቋጭ የፀሐይ ሐሩር የሚያስከትለው የጤና ሁከት ዋና ዋና ምልክቶች ምንነት እና በተለይ ለሐሩር ተጋላጭ የኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ማንነትም አስረድተውናል። ዶክተር ነጋ፣ ከዋሽንግተን ዲሲ ከተማ...0 Comments 0 Shares
-
AMHARIC.VOANEWS.COMየሳህል ታጣቂዎች ወደ ናይጄሪያ መግባታቸው አሳሳቢ ሆኗልበአፍሪካ የሳህል ቀጠና አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ከቤኒን ጋር የሚያዋስኑ ድንበሮችን አቋርጠው ወደ ሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ መግባታቸውን የሚገልፅ አዲስ ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ የቀጠናው የፀጥታ ተንታኞች የናይጄሪያ ባለሥልጣናት ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እያስጠነቀቁ ነው። ቲሞቲ ኦቢየዙ ከአቡጃ ያደረሰንን ዘገባ ስመኝሽ የቆየ በዛሬው አፍሪካ ነክ ርእሶች ይዛዋለች።0 Comments 0 Shares
-
AMHARIC.VOANEWS.COMበፕሬዚዳንታዊ ምርጫው አነጋጋሪ የኾነው የፅንስ ማቋረጥ ሕጋዊነት ሽረትየዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ከሁለት ዓመት በፊት በዚኽ ወር፣ እ.ኤ.አ. በ1973፥ ፅንስ ማቋረጥን ሕጋዊ የሚያደርገውን ውሳኔ በመሻር፣ በአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ውሳኔ አሳልፏል። በዚኽ ዓመት ኅዳር ወር በሚካሔደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ ፅንስ ማቋረጥ እንደ ትልቅ ጉዳይ አነጋጋሪ እየኾነ ነው። የቪኦኤ ከፍተኛ ዘጋቢ ካሮሊን ፕረሱቲ፣ በጉዳዩ ላይ የሚያዘው አቋም፣ በፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ዘመቻው ምን ዓይነት ጫና እንደሚያሳድር...0 Comments 0 Shares
-
AMHARIC.VOANEWS.COMበናይሮቢ ፖሊስ ለተቃውሞ የወጡ ሰልፈኞችን በአስለቃሽ ጭስ በተነየኬንያ ፖሊስ በቅርቡ የአገሪቱ ፓርላማ ያረቀቀውን መጠነ ሰፊ የግብር ጭማሪ የሚጠይቅ ረቂቅ የፋይናንስ ሕግ ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷል። ሰልፈኞቹ ወደ ፓርላማ እንዳይገቡ ለማድረግ ቁጥሩ የበዛ ፖሊስ ተሰማርቷል። የኬንያ መንግስት ሃገሪቱ ያለባትን ግዙፍ ዓለም አቀፍ ዕዳ ወለድ ክፍያ ለመቀጠል ያስፈልገኛል በሚል ያቀረበውን ረቂቅ ሕግ በመቃወም ከቅርብ ቀናት ወዲህ በወጣቶች የሚመራ የማኅበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ በኬንያ እየጨመረ መምጣቱ...0 Comments 0 Shares
-
AMHARIC.VOANEWS.COMዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት በቀድሞው የሩስያ መከላከያ ሚንስትር ላይ የእስር ማዘዣ አወጣዓለም አቀፍ የወንጀል ችሎት - አይሲሲ በቀድሞው የሩስያ መከላከያ ሚንስትር ሰርጌይ ሾይጉ እና በሩስያው ወታደራዊ አዛዥ ጄኔራል ቫለሪ ገራሲሞቭ ላይ ዛሬ የእስር ማዘዣ አውጥቷል። አይሲሲ በመግለጫው ይፋ እንዳደረገው ሁለቱ ተጠርጣሪዎች እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከጥቅምት 2022 እስከ መጋቢት 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ ‘የሩስያ ጦር ኃይሎች በዩክሬን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማቶች ላይ ባደረሱት የሚሳኤል ጥቃት ተጠያቂ ስለመሆናቸው በቂ ማስረጃ...0 Comments 0 Shares
-
AMHARIC.VOANEWS.COMየጋዛ ጦርነቱ የረሃብ ቸነፈር ሥጋትበጋዛ ሰርጥ ያለው እጅግ አደገኛ ሁኔታ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተደገፈው የምግብ ዋስትና ሪፖርት አስታወቀ። የእስራኤል እና የሐማስ ጦርነት እስከቀጠለ እና የሰብዓዊ ረድኤት አቅርቦት እስከተገደበ ድረስ በመላዋ ጋዛ የረሐብ ቸነፈር አደጋው አይቀሬ መሆኑን ሪፖርቱ አስገንዝቧል። በእንግሊዝኛ የምህጻር መጠሪያው አይፒሲ የተባለው የተቀናጀ የምግብ ዋስትና ምዕራፎች ትንተናው ሪፖርት ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ የጋዛ ነዋሪዎች የረሐብ...0 Comments 0 Shares
-
AMHARIC.VOANEWS.COMበጋምቤላ ከተማ ግጭት ሁለት ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለጸበጋምቤላ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ ምሽት በጀመረውና በማግስቱ ሰኞም በቀጠለው ግጭት፣ ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የክልላዊ መንግሥቱ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ፣ በግጭቱ ሁለት ሰዎች መገደላቸውንና አራት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡ በጋምቤላ ከተማ የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ እና የሪፈራል ሆስፒታሎችም፣ በግጭቱ የቆሰሉ ሰዎችን እያከሙ እንደሚገኙና የሞቱም መኖራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።0 Comments 0 Shares