በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት ስራ ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶች ተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት ሊሰጡ ነው
በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶችን ለተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት መስጫነት እያዘጋጃቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ከትራንስፖርት ባለስልጣንና ከአንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመሆን በእርጅና ምክንያት አገልግሎት ያቋረጡ አውቶቡሶችን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ጥናት አካሂዷል።
አውቶቡሶቹ ለኢንተርኔት ካፌ፣ ለፀጉር ቤት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሸቀጣ ሸቀጥና ለቅርጻ ቅርጽ መሸጫነት በሚያመች መልኩ እየተጠገኑ መሆኑንና እየተጎተቱ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ አገልግሎት እንደሚሰጡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ዘርዑ ስሙር...