በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት ስራ ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶች ተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት ሊሰጡ ነው

በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶችን ለተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት መስጫነት እያዘጋጃቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው ከትራንስፖርት ባለስልጣንና ከአንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ጋር በመሆን በእርጅና ምክንያት አገልግሎት ያቋረጡ አውቶቡሶችን መልሶ መጠቀም የሚያስችል ጥናት አካሂዷል።
አውቶቡሶቹ ለኢንተርኔት ካፌ፣ ለፀጉር ቤት፣ ለካፌና ሬስቶራንት፣ ለሸቀጣ ሸቀጥና ለቅርጻ ቅርጽ መሸጫነት በሚያመች መልኩ እየተጠገኑ መሆኑንና እየተጎተቱ ወደተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ አገልግሎት እንደሚሰጡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ዘርዑ ስሙር ተናግረዋል።
ስራው የቴክኖሎጂ እውቀት ሽግግር ከመፍጠር ባሻገር በመዲናዋ ያለውን የመስሪያ ቦታ ችግር በማቃለልና የስራ እድል በመፍጠር የጎላ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው የገለጹት።
አውቶቡሶቹ ከኢንተርኔት አገልግሎት ባሻገር የጽህፈት መሳሪያ መሸጫ፣ የፕሪንትና ኮፒ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገው የተጠገኑ በመሆኑ በርካታ ወጣቶች ተደራጅተው የመስራት እድል ያገኛሉ ብለዋል።
በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ከ700 በላይ አንበሳ አውቶቡሶች መኖራቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።

ፍለጋ
Categories
- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes
Read More
ዳይ እየተሰዳደብን ...
«ዘውድአለም ታደሰ»
ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖልኛል። ጭራሽ እየሩሳሌምን ለእስራኤል አሳልፈን አንሰጥም! አንሰጥም!...
ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
ትንሹ ልጅ እናቱን “ማሚ ለምን ታለቅሻለሽ?” ሲል ጠየቃት “ምክንያቱም...
አይኔን በሌላ ሰው አይን ሳየው!
(አሌክስ አብርሃም)
ፍቅረኛየ በየቀኑ እንዲህ ትለኛለች“ አብርሽ ‹የ› ” በቃ ‹ የ›...