ሰርጋቸው ደማቅ ስለነበር ለምን ይፋታሉ?

0
0

(አሌክስ አብርሃም)

እንዴት ናችሁ ጓዶች ….ከሰሞኑ የፍች ወሬ በርከት ብሎ ሰነበተ ፌስቡክ ላይ? … ይች ፌስቡክ መቸም ፍች ስትወድ በስመአብ !! እውነቴንኮ ነው ….እንትናና እንትና ተጋቡ የሚል ፖስት ያውም ሙሽራው ሱፍ ለብሶ ወገቡን ይዞ አንዴ እንደበረኛ ተወርውሮ ተኝቶ …አንዴ ፈረስ ላይ ነብስና ስጋው እየተሟገተ ፊቱ ‹‹አቫተር ›› መስሎ …. የተነሳውን ፎቶ ሁሉ ለጥፎ ሶስት ላይክና አራት ኮሜንት ብቻ ታያላችሁ ….‹‹ ተፋቱ ›› ሲባል ስምንት መቶ ላይክ አራት ሽ ኮሜንት ሶስት ሽ ሸር ! ውይ ፌስቡክ ፍች ስትወድ ይች ሾይጣን ሂሂ!አይዞን የሰው ባህሪ ነው !


የሰርግ ፎቶ ስል ምን ትዝ አለኝ …አንዴ ጓደኛችን አግብቶ ሰርግ ሄድንና የመስክ ፎቶ ተብሎ በቃ አገልግል ነሽ ሞሰብ ነሽ …ፈረስ ነሽ ጦርና ጋሻ …የቀረ ነገር የለም …አድዋ ዘማች መስለን ከአዲስ አበባ ወጣ ወዳለ ሜዳና ወንዝ ወዳለበት ቦታ ጎረፍን ! ፎቶ አንሽው እዛ ሜዳ ላይ ሙሽራውን ፍዳውን አሳየው ….‹‹እ …አሁን አንተ ከላይ እሷ ከታች …አሁን ደግሞ አንች ከላይ ሁነሽ ከንፈሩን በስሱ ትስሚዋለሽ …ሙሽራው ፈገግ አለ

(ምን አስገለፈጠው መቸም ህዝብ ፊት እንትን …አይደረግ ጅል…) እንላለን ፀሃዩ አማሮን …ሙሽራዋ ደግሞ ፍዝዝ ያለች ነገር ከንፈሩን እየተባለች ግንባሩ ላይ ቀይ ሊፒስቲኳን ለደፈችበት …(ወደፊት ሲጋቡ በመጥበሻ ግንባሩን እንደምትፈነክተው አመላካች ነው ሲል ከመካከላችን የነበረ አንድ የስነልቦና ባለሙያ ማብራሪያ ሰጠን…በነገራችን ላይ ይሄ የስነልቦና ባለሙያ በትንሽ ትልቁ ነገር እያለቀሰ እና ራሴን አጠፋለሁ እያለ ስንት ጊዜ መሰላችሁ በምክር ያተረፍነው ‹ተው እንጅ ምንድነው ተምሮ እንዳልተማረ መሆን› ብለን ) እና ‹‹የማታዋጣ ሚስት ግንባር ትስማለች›› የሚለው ተረት ‹‹የማያዋጣ ባል ቅንድብ ይስማል ›› የሚለውን አባባል ተክቶ ስራ ላይ የዋለው የዛን ቀን ነው !!

ከዛ….ሙሽራው እንደዛ ጅስሙ ግሎ በቃ ቶሎ መሽቶ ወደቤት ሂደን …ምናምን እያለ ሲደሳሰት ….የተረገመ ፎቶ አንሽ ምን ቢለው ጥሩ ነው ….አሁን ደግሞ ጫማህን አውልቅና እግርህን ወንዙ ውስጥ ዘፍዝፈው …እሰይ ! እንዲህ ቀዝቀዝ ይበል እንጅ ሃሃሃ ! ባል ከዛ ቀን ጀምሮ ቀዝቀዝ ያለ አባወራ ሆነ በቃ ! በተለይ ያሳዘነኝ …ፎቶ አንሽው ‹‹ አሁን ሙሽሪትን አንሳና ተሸከማት ›› ሲለው ዞር ብሎ እኛን አየን ….(ቅድም እሷ ከላይ አንተ ከታች ሲባል ያላስታወሰንን አሁን ያፈጣል እንዴ) አንዳንዱ ሰው ደስታውን እንደዶሮ አጥንት ብቻውን ቅርጥፍ ያደርግና ሸክሙ ላይ ‹‹ወዳጅ ለመቸ ነው ዘመድ ለክፉ ቀን…እርዱኝ እንጅ በኔ የደረሰው እህህ ምናምን ›› ይላችኋል …እዛው ተሸከም ባክህ ! በዚህ ፀሃይ እንኳን ያንተ ሚስት የያዝናት ሃይላንድ ውሃም ከብዳናለች !

ግን አልጨከንበትም እንደሬሳ እግርና ራሷን ይዘን እንደግሬደር ማፈሻ የተዘረጋ እጁ ላይ አሳቀፍነው (ደግሞ ፀጉሬን እንዳታበላሹ ነግሪያለሁ …ብላ ትቆጣለች እንዴ ኩርንችት ልንላት ነበር ሙሽራ ክቡር ነው ብለን ዝም አልን) በስንት መከራ እየተንገዳገደ አቅፏት ተነሳ …ፊቱ በቃ የኦሎምፒክ ክብደት አንሽ ነበር የሚመስለው! አንዳንድ ሚስቶች ደግሞ ሲታቀፉ ዝልፍልፍ የሚሉት ነገር አለ (አማላይ መኮኑ ነው) …ከምር! ማቀፉ ይቅር ሰው እንዴት መታቀፍ ያቅተዋል ….‹‹በመሃበር ታቀፊ አለ ክበበው) እንዲህ አይነት ፎቶ ስታዩ የሰርግ ፎቶ ሳይሆን ሙሽሪት ራሷን ስታ አፋፍሶ ይዟት ወደሆስፒታል የሚሮጥ ነው የሚመስለው ….

ወደዋናው ጉዳይ እንመለስ ኧረ ….(ምንድነው ስራ የላችሁም እንዴ ዝም ብላችሁ ትሰማላችሁ ….ወቸ ጉድ !)እና መቸስ በፍቅር ክንፍ እንደማለት ሁሉ አይንህን ላፈር መባባልም የነበረ ያለና የሚኖር ነው . . . ከሰሞኑ እህት እፀ ህይዎት ተፋታች መባሉን ተከትሎ ከሰፊው ህዝብ እስከታዋቂ ሰዎቻችን ወሬውን እንደጉድ እያራገቡት ነበር …የገረመኝ ነገር ታዲያ ‹‹እንደዚያ በደመቀ ሰርግ ተጋብተው እንዴት ይፋታሉ›› ብሎ እንደትልቅ ነጥብ ኮስተር ብሎ የሚከራከረው ሰው መብዛት ነው ! ጓዴ የሰርግ ድምቀት በለው … የመልክ ድምቀት በለው ሃብት በለው ….. ዘመድ በለው …. በሁለት ወንድና ሴት መሃል አንዴ አለመፈለግ ከነፈሰ ምንም ምድራዊ ሃይል እንደገና መፈለግን አያመጣውም !! እደግመዋለሁ ካልፈለክ ታንክ ቢደገንብህም አትፈልግም!

እና ሰው ደግሞ ካልፈለገ ሌላ ምንም ምክንያት አያስፈልገውም !በቃ አብሮ መሆን አልፈለገም !! ፍችን አልደግፍም ግን ሰው በቃኝ ብሎ ከሄደ በቃ በቃኝ ነው !! አንዳንዱ በሰው ህይዎት ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ሁሉ ያምረዋል …የሆነ መፎክር ነገር

‹‹ አልፈልግሽም ማለት ህዝብን መናቅ ነው ›› 
‹‹ነው! ›› 
‹‹አገራችን በተያያዘችው የእድገትና ልማት ጎዳና የእገሊት ባሏን መፍታት ልማት ያደናቅፋል›› …
‹‹ያደናቅፋል!›› 
‹‹ለሰርጋቸው ያወጡት ብር ለመንገድ ስራ ቢውል ጥሩ ነበር ››
‹‹ነበር›› 
‹‹እሷ ማን ስለሆነች ነው የምትፋታው ››
‹‹ታው›› . . . ሃሃ

ወደዚህኛውም ጉዳይ ስንመጣ ውስጣቸውን እግዜር ይወቅ … ቢያንስ ለልጆቻቸው ሲሉ መታረቅ እና ሰከን ብለው ማሰብ ከቻሉ አሪፍ ! ካልሆነ ግን እሷም ቆንጆ ነች አሪፍ ተዋናይትም ነች…እሱም ፀዳ ያለ ሰው ነው….ሁለቱም ደግሞ ከወጣትነት ብዙም አራቁም ….እንግዲህ ከውጭ ማየት የሚቻለው ይሄን ብቻ ነው …እና …መልካም ህይዎት በየፊናቸው ! እትት ብትት የለም !

ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር አያሌ ዜጐችን በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት ተምረው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ማስቻሉ በጥናት...
By Seller 2017-11-15 07:31:38 0 0
Uncategorized
አንዳንድ ነገሮች ስለ ግማደ መስቀሉ
(ዳንኤል ክብረት) ስለ ግማደ መስቀሉ አመጣጥ ግሼን በሚገኘው በመጽሐፈ ጤፉት የተጻፈውን ባለፉት ዘመናት ስናነበውና ስንሰማው ኖረናል፡፡ እስኪ ዛሬ ደግሞ...
By binid 2017-11-25 13:26:59 0 0
Dance
Can Sterilization Flat Roll Adapt to Hopeway AMD Workflows?
In environments that rely on structured preparation and calm precision, the Sterilization Flat...
By fufuhua123 2025-12-18 01:30:08 0 0
Uncategorized
_ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር
__ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር “The graveyard is the richest place on earth,...
By Seller 2017-12-01 08:05:09 0 0
Uncategorized
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)፡ፒስ ነው ጋይስ?!ቃሉን የማያጥፈው መንግስታችን "መጪው ዘመን የከፍታ ነው" ባለው መሰረት ከሰሞኑ ዶላሩን...
By andualem 2017-11-12 15:14:07 0 0