ሁለቱ ወንድማማቾች ___

በአንድ የገጠር መንደር በቤተሰቦቻቸው የእርሻ ማሳ በጋራ እያመረቱ የሚተዳደሩ ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንደኛው ትዳር መስርቶ ብዙ ቤተሰብ የሚያስተዳደር ሲሆን አንደኛው ግን ገና አላገባም ብቻውን ነው የሚኖር፡፡ በምርት መሰብሰቢያ ወቅት ያገኙትን ምርት እኩል ይካፈሉ ነበር፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ትዳር ያልመሰረተው ለእራሱ እንዲህ አለ፡፡ “ያገኘነውን ምርት እኩል መካፈል ፍተሃዊ አይደለም፡፡ እኔ ብቻየን ስለሆንኩ ትንሽ ነገር ነው ሊበቃኝ የሚችለው፡፡” እንዲህ ብሎ መሸት ሲልለት ጨለማውን ተግነ አድርጎ ከጎተራው ኬሻ ሙሉ ጥራጥሬ እያነሳ በቤታቸው መካከል ባለው መስክ አቋርጦ ከወንድሙ ጎተራ ይሞላለት ነበር፡፡ በተመሳመሳይ ሁኔታ ትዳር የመሰረተው ወንድሙም ለእራሱ እንዲህ ይላል “ምርታችንን እኩል መካፈላችን ትክክል አይደለም፡፡ ሁኖ ሁኖ እኔ ባለ ትዳር ነኝ በመጭዎቹ አመታት አንዳች ነገር ቢፈጠር እንኳን ልጆቼና ሚስቴ ይንከባከቡኛል፡፡ ይሄ ወንድሜ ግን ብቻውን ነው፡፡ ማንም የሚንከባከበው የለውም ስለሆነም” አለና መሸት ሲልለት ጨለማውን ተግነ አድርጎ ኬሻ ሙሉ ጥራ ጥሬ እየወሰደ ከላጤ ወንድሙ ጎተራ ይጨምራል፡፡ እንዲህ እንዲህ እያሉ ዓመቱ ተጋመሰ የእህል ጎተራቸው ያልቀነሰበት ምክንያት ግን እንቆቅልሽ ሆኖባቸዋል፡፡ ከዛም አንድ ቀን ምሽት ሁለቱም እንደልማዳቸው አንደኛው ላንደኛው ኬሻ ሙሉ ጥራጥሬውን ይዘው ሲተላለፉ ሁኔታዎች ተገጣጠሙና መንገድ ላይ ተጋጩ፡፡ ቀስ አድርገው ሸክማቻን አውርደው ሲተያዩ ወደንድማማቾቹ ነበሩ፡፡ በልባዊ ፍቅር ተቃቀፉ፡፡ ፊት ለፊት ተነጋግረው የበለጠውን አንደኛው መውሰድ እንዲችል ማድረግ ጠፍቷቸው አይደለም ግን አንተ ትብስ አንተ ትብስ እየተባባሉ ውሳኔ ላይ መድረስ እንደማይችሉ ስላወቁ የፈጠሩት መላ ይመስላል፡፡ እንኳንስ ስጡ ሳይባሉ ለመስጠት መፍቀድ ቀርቶ ቢጠየቁ እንኳ እኩል ድርሻየ ነው ማለት በሚቻልበት ሁኔታ የበለጠውን ለመስጠት መሻት ከልባዊ ፍቀር ውጭ ሊመጣ አይችልም፡፡ ለሰጨውም ሆነ ለተቀባዩ ሳይቀንስ የሚሰጥ ስጦታ ልባዊ ፍቅር ብቻ ነው፡፡ እንዲህ አይነታ ፍቀር ይስጠን ነው የሚባለው፡፡ ምንጭ፡ Story of Two Brothers (#ምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ) 17-09-2007 ዓ.ም

- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes