_ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር

0
0

__ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር

“The graveyard is the richest place on earth, because it is here that you will find all the hopes and dreams that were never fulfilled, the books that were never written, the songs that were never sung, the inventions that were never shared, the cures that were never discovered, all because someone was too afraid to take that first step, keep with the problem, or determined to carry our their dream.”― Les Brown
ለምን እንደሆነ ባላውቅም ብዙዎቻችን ስለሞት ማሰቡን አንወድም። ለነገሩ ሞት ምን ደስ የሚል ነገር አለውና። ለማለት የፈልግኩት ግን ስለ ሞት ማሰቡም ሆነ ማውራቱን ከመጥላታችን በላይ አኗኗርችን ሲቃኝ ሞትን ፈጽሞ የዘነጋነው ይመስላል። ጎረቤታችንን እየወሰደ እያየን እንኳን እኛን ደፍሮ የሚነካን አይመስለንም። ለዚህ ነው አለቅጥ የምንዘናጋው። መጽሃፍ ቅዱስ ላይ ሳይዘጋጁ ተዘናግተው መኖር የሚያመጣውን ጣጣ የሚያስረዳ ድንቅ ታሪክ አለ።
“በዚያን ጊዜ መንግስተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አስር ቆነጃጅትን ትመስላለች፤ ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከነሱ ጋር ዘይት አልያዙምና ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ። እኩለ ሌሊትም ሲሆን እነሆ ሙሽራው ይመጣል ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ሁካታ ሆነ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሱና መብራታቸውን አዘጋጁ። ሰነፎቹም ልባሞቹን መብራታችን ሊጠፋብን ነው ከዘይታቹህ ስጡን አሏቸው። ልባሞቹ ግን መልሰው ምናልባት ለእኛ እና ለእናንተ ባይበቃስ ይልቅስ መደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሏቸው። ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ ደጁም ተዘጋ። በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቆነጃጅት መጡና “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ክፈትልን አሉ”፤ እርሱ ግን መልሶ “እውነት እላችኋለው አላውቃችሁም” አለ። ቀኒቱን እና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ አላቸው።

ነገ ለሁላችንም የቅርብ እሩቅ ነው፤ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል። የብዙዎቻችን አኗኗር ልክ እንደ አምስቱ ሰነፍ ቆነጃጅት ነው። ለብዙ ነገሮች ቀጠሮን መያዝ እንወዳለን። ሞትን እንደጥላችን ይዘነው እንደምንዞር ስለምንዘነጋ እርምጃችን ዘገምተኛ ነው። ለሁሉ ነገር ነገን እንመርጣለን፤ ነገ ሲመጣ ደግሞ ሌላ ነገ ይወለዳል። ከላይ የሰፈረው የሌስ ብራውን አባባል ትልቅ እውነት ነው። መቃብር በምድር ብዙ ሃብት ያለበት ስፍራ ነው። ምክንያቱም ጥቂቶች ብቻ ናቸው የተሰጣቸውን ተሰጥዎ ተጠቅመውበት የሚያልፉት። ብዙዎቻችን ግን አይምሮዋችንን ሳንጠቀምበት፤ ሰውነታችን ሳንሰራበት፤ እውቀታችንን ሳንገለገልበት ጀምበራችን ትጠልቃለች።

ተዘጋጅቶ መኖር በመንፈሳዊውም ሆነ በስጋዊው ህይወታችን ወሳኝ ነገር ነው። ብዙ እውነቶች ሳይነገሩ፤ ብዙ ይቅርታዎች ሳይጠየቁ፤ ብዙ ካሳዎች ሳይከፈሉ፤ ወደመቃብር ወርደዋል። ለዚህ ነው ሌስ ብራውን መቃብርን ሃብት የተሞላበት ስፍራ ሲል የገለጸው። ልክ እንደ ሰነፎቹ ቆነጃጅት የቅንነትን ዘይት፤ የእውነትን ዘይት፤ የይቅርታን ዘይት፤ የተስፋን ዘይት በእለት ተእለት ኑሮዋችን ይዘን ስለማንዞር፤ ድንገት ሙሽራው ሲመጣ ፤ ጨለማ ይወጠናል፤ ደጁ በላያችን ይዘጋል።

አያድረገው እንጂ ነገ ትሞታላችሁ ቢባል ፤ለነገ የሳደርናቸው ስንት ሃሳቦች አብረውን ይሞታሉ?ለነገ ያቆየናቸው ስንት ግቦች አብረውን መቃበር ይወርዳሉ?ሳንፈትሽ ያቆየናቸው ስንት ተሰጥዖዎች ቁልቁል ይቀበራሉ? ሳይፈንጥቁ የኖሩት ስንት ተስፋዎች ይቀጫሉ?ያላበረከትናቸው ስንት ደግነቶች አፈር ይበላቸዋል? ያልተነገሩ ስንት ይቅርታዎች ላይመለሱ ይሞታሉ? ያለተተነፈሱ ፍቅሮች ሳያብቡ ይሞታሉ?

ሞትን እንደማሰብ ብርታትን የሚሰጥ እና ቀናውን መንገድ የሚመራ ሃይል ያለ አይመስለኝም። መጨራሻን ሞት መሆኑን ስናውቅ ይህችንን አለም መልካም ከማድረግ በቀር ምንም ምርጫ ሊኖረን ባልተገባ ነበር። ነጋችን ዋስትና እንደሌለው ስንረዳ ሰውን ሰው ሊያሰኘው የሚችሉትን ምግባሮች ለማድረግ ቀጠሮ ባልያዘን ነበር። እናም አላማህን ፈጽሞ አታዘግየው ማን እንደሚቀድምህ አታውቅምና። ህይወታችንን ሙሉ ከስርዓት ውጪ ኖረን፤ ለንስሃ ጊዜ እናገኛለን ብለን አንዘናጋ። ዘይታችንን ሙሉ አድረገን እንጓዝ በሩ መቼ እንደሚዘጋብን አናውቅምና።
(Source Asharaye)

Like
2
ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90...
By Dawitda 2017-11-14 18:21:39 0 0
Uncategorized
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር አያሌ ዜጐችን በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት ተምረው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ማስቻሉ በጥናት...
By Seller 2017-11-15 07:31:38 0 0
Uncategorized
መጨከክ
መጨከክ(አሳዬ ደርቤ)ከሰባት ሰማይ ስር ካለ ጎጆ መሃልማጣት፣ መንጣት እንጂ… ኦናነት ታቅፎ -አይቻልም መጉደል፡፡.ልክ እንደ ማረሻው-...
By Assaye 2017-11-12 13:07:06 0 0
Other
How Supply Chain Management Impacts Customer Satisfaction and Profitability
In today's hyper-competitive market landscape, the success of a business is no longer just...
By abhinavshina 2025-06-16 08:50:11 0 0
Uncategorized
Macaafa Qulqulluu!!
Ergaa jireenya dhugaa fi Amantii.
By T002 2017-11-15 04:43:20 0 0