ከቆንጆ ሴቶች ጀርባ

0
0

ከቆንጆ ሴቶች ጀርባ ....!
«ዘውድአለም ታደሰ»

ትናንትም እንደፈረደብኝ አንድ የቀረኝ ጓደኛዬን ድሬ እያጨበጨብኩ ወደቤት ገባሁ! በቃ የኔ ኑሮ እንደድንኳን በየሰርግ ቤቱ መተከል ሆኖ ቀረ ማለት ነው የቶጳ ሂብራታሳብ? ኦሮሮሮሮ አለ ቴዲ አፍሮ!!

“ከስኬታማ ወንድ ጀርባ አንድ ሴት አለች” ይባላል። (በርግጥ ከስኬት-አልባ ወንድ ጀርባ ሴትም እሴትም እንደማይኖር የታወቀ ነው)
ከስኬታማ ወንዶች ጀርባ ሴቶቹ እንደማይጠፉት ሁሉ ግን ከቆንጆ ሴቶች ጀርባም ቡጢ የጨበጠ ባል አይጠፋም።

ትናንት ማሂን ሰርጉ ላይ አገኘኋት! ማሂ የሰፈራችን ክሊዮፓትራ ነች! አረጋሃኝ ወራሽ እስቲ ዘለል ዘለል የሚል ዘፈን ያቀነቀነው እሷን አይቶ ነው ሁሉ ይባላል። ማለቴ ስትራመድ ማይዘል ነገር የላትም :) ፐ አረማመድ ... መሬት ላይ እየተራመደች ሳይሆን ደመናው ላይ እየተንሳፈፈች ነው ሚመስለውኮ። የእግሯ ውበት ምነው መሬቱን ባረገኝ የሚያስብል ነው። ተረከዟ ከዚያች ወረንጦ የድሮ ሚስቴ ፊት ይለሰልሳል። የሆነ ተራምዳበት ምታውቅ አይመስልም። ለነገሩ ጫማው ነው! እንደኛ በቻይና ጫማ አትቃጠል :) በቃ ምናል በዚህ እግር አንዴ በጫማ ጥፊ በተመታሁ የሚያስብል ማራኪ እግር ነው ያላት። ልክ እንዳየኋት ዘልዬ እንደሀረግ ተጠመጠምኩባት። እሷን አቅፌ አካባቢውን ቃኘት ቃኘት ሳደርግ ከጀርባዋ ሮበርት ሙጋቤን የመሰለ ባል ቡጢ ጨብጦ ቆሟል! አረ ይሄ ሰውዬ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎበት የለንዴ? ቤት በኩል ዞሮ መጣ? ምናምን እያልኩ ሳስብ ጥርሱን ነክሶ አንገቱን ነቀነቀ!በተከበርኩበት ሐገር ደመከልብ እንዳያደርገኝ ብዬ ማሂን ቀስስስ ብዬ ለቀቅኋት!

ውይ ሴቶች ግን ለማግባት ፍጥነታቸው? አሁን ምናባቷ አጣደፋት? ደሞኮ የልጆቿ ብዛት ... አንዱ ጡጦ ሳይጥል ሌላ ልጅ መድገሟን ሰማሁ! የሱ ሲገርመኝ በዘጠኝ ወሯ ሶስተኛ ልጅ መውለዷን ስሰማ «እነዚህ ሰዎች ተኝተው አያድሩም እንዴ?» ብዬ ተበሳጨሁ። ብስጭቴን ብታዩትኮ ልጆቿን በኔ ደሞዝ ምታሳድጋቸው ነው ሚመስለው።
ብቻ ሴቶቹ በጣም ይቸኩላሉ! የሆነ የሩጫ ውድድር ነው ሚያደርጉት እኮ ቶሎ ያገባ ሜዳሊያ ምናምን ነገር ሚሸለም ነገር! .... ብቻ ለኛም እግዜር አለን! ጀሊሉ ሰርግ ቤት ያጣናትን ግራ ጎን ለቅሶ ቤት ይጥልልን ይሆናል። who knows? ብላለች ቲቲ ላቭ :)

ሰርጉ ጥሩ ነበር። ያው ምግብ አለ! ምግብ ስል ....... አረ ኦገኖች ሼም ቀርቷል! አረ ሃበሻ ሼም ትቷል! አንዳንዱኮ ሰሃኑ ላይ የሚቆልለው ምግብ ከግብፅ ፒራሚድ ምንም አይተናነስም። የእንጀራውስ ብዛት ... ከፊቴ የነበረው ሰውዬ ይሄን ቁርጥ እንደአንሶላ እየዘረጋ ሲያነጥፈው። እየዘረጋ ሲያነጥፈው ( የአልቤርጎ አልጋ አንጣፊ ሳይሆን አይቀርም) ... በዚያ ላይ ልክ እንደምርጫ ፈተና ምንም ድስት አያልፍም ሃያ ምናምን አይነት ወጥ በአንድ ሳህን ላይ እንደምንም አብቃቅቶ እያለከለከ ሲሄድ ምግብ ሳይሆን ቀንበር የተሸከመ ነበር ሚመስለው ... አረ ሃበሻ ሼም ትቷል ጓዶች ... አረ ሼም ቀርቷል!!

አንዱ ደሞ ሙሽሮቹ ኬክ እየቆረሱ እያለ
እየተደነቃቀፈ ፣ ሚዜዎቹን እየገፈታተረ፣ ተንደርድሮ ወደሙሽራዋ ሮጡ ልክ ፊትለፊቷ ሲደርስ ኮቱ ስር ወዳለው ኪስ እጁን ሰደደ ... ሁሉም ሰው በድንጋጤ ክው አለ! ማን ነው? ምንድነው? የድሮ ፍቅረኛዋ ነው? ከኪሱ መሳሪያ ነው ሚያወጣው? .... መጨረሻውን ለማየት ጓጓን! ሙሽሪትና ሙሽራ ደንግጠዋል! ሚዜዎቹ ዘሎ ለማነቅ በተጠንቀቅ ቆሙ! ሰውየው ግን ዘና ብሎ ከኪሱ አሮጌ አስር ብር አውጥቶ ምራቁን እንትፍ አለበትና ሙሽሪት ግንባር ላይ ለጥፎ እየተንጎማለለ ዞር አለ! ጉድ አልኩ እኔ። መቼም ለጉድ ነው የጎለተኝ! :)
ኬክ ስል ግን .... የኛ ሐገር ሰርጎች ሲደረጉ ግርርርም ከሚሉኝ ልማዶች አንዱ አደባባይ እንደታቦት በመኪና ሚዞሩት ነገርና ኬክ እየተጎራረሱ ሚበሉት ነገር ነው። የምር ግን ምንድነው ትርጉሙ?
እኔ ስገምት ይሄ ስርአት የተጀመረው ኬክ ብርቅ በነበረበት ዘመን ነው። የሆነ ፍሪዳ እንደሚጣለው ምናምን ኬክ መጣል አኩሪ ባህል ነበር። እንዴ ድሮኮ ኬክ ለመብላት ራሱ የነበረው ትግል ኢህአዴግ ደርግን ለመጣል ከታገለው ትግል በምንም አይተናነስም! ልዩነቱ የሰርግ ቤት ታጋዮች ኬክ ለመብላት 17 አመት አይፈጅባቸውም :)

ከኬኩ ስነስርአት በኋላ ያ አስር ብር ለሙሽሪት የሸለመው ሰውዬ "ሳም አረጋታለሁ" የሚለው ዘፈን ሲከፈት ወደሙሽራዋ እየጠቆመ እኩል መዝፈን ጀመረ «አረ ይሄ ሰው ምንሼ ነው?» አለ ቤተ ዘመዱ። የሙሽራው ታናሽ ወንድም ብረት ይገፋል፣ ደረቱ መቀመጫ ነው ሚያህለው ቦክስ ጨበጠ። ሰውየው ማንን ሊፈራ?
“ሳም ፣ ሳም ፣ ሳም፣ ላርግሽ ሳም” ይላል።
ጠርጥር .... አለ ሰርገኛው! ዲጄው እግዜር ይስጠው ዘፈኑን ወደ ትዊስት ቀየረው። ሰውየው ከመቅፅበት ሴራሚኩ ላይ ትዊስት ሲጨፍር አንሸራቶት በግምባሩ ክንብል፣ ሙሽራው «አሰይ» አለ በሆዱ። ደጋግፈን አንስተን «ምነው?» ብንለው «አውቄ ነው። የዳንሱ አንዱ ፓርት ነው» አለን ፈገግ ብሎ። ፊቱ ላይ ግን ከባድ ሀፍረት ይታይ ነበር።

በስተመጨረሻ ለሙሽሪት ስም ይውጣ ተባለ።
የቀበሌያችን የሸማቾች ማህበር ሃላፊ ተነስተው «ያው ያባይ ጉዳይ በውስጥና በውጪ ደባ ዘገየም አይደል? እንግዲህ ጉባኤው ተተሰማማ "ብጥር ቀኑ" ትባል» ሲሉ ከተቃዋሚ ፓርቲ እማማ ዝናሽ ተነስተው ተቃውሞ አሰሙ።
«ምንድነው?» ተባሉ
«እቺ ልጅኮ የአቶ ይድነቃቸውና የወይዘሮ ይመኙሻል ፍሬንጂ የኢህአዴግ ፍሬ አይደለችም። ይልቅ አባይ፣ ብጥር ቀኑ ፣ ምናምኑን ትተን በእስር የሚማቅቁት ወገኖቻችንን ለማሰብ «ታሰረች» ብትባልስ?» የሚል ሃሳብ አመጡ። በዚህ ሁኔታ ሁሏም ፖለቲካዋን በዳቦ ስም ሙሽሪት ላይ ለመጫን ሙከራ ስታደርግ ቆይታ መጨረሻ ላይ ግን ማህበረሰቡ ከመንግሰትም ከህገመንግስትም የማያነካካ ስም ብሎ «ስኳር ነሽ» አላት!
ድንቄም ከፖለቲካ መራቅ እቴ «አረ የማይነሳ ስም እያነሳችሁ እንዳታስፈጁን» አሉ ጋሽ በቄ። «ደሞ ስኳር ነሽ ብላችኋት ይሄ መንግስት አፋፍሶ በኬንያ በኩል ኤክስፖርት ቢያደርጋት የማን ያለህ ልንል ነው?» አሉ! አይ ጋሽ በቄ ሃሃ

ፍለጋ
Categories
Read More
Art
Al Hamriya Call Girls +971528648070 Pakistani Call Girls in Al Hamriya By Dubai Call Girls
Al Hamriya Call Girls +971528648070 Pakistani Call Girls in Al Hamriya By Dubai Call Girls She...
By heenaparker516 2025-06-06 14:55:38 0 0
Art
Business Bay Escort Girls 0509101280 Escort Call Girls in Business Bay
Business Bay Escort Girls 0509101280 Escort Call Girls in Business Bay She left. She said that...
By heenaparker516 2025-06-06 15:39:52 0 0
Uncategorized
እንቆቅልሽ የሆነው የወተት ምርት
ኢትዮጵያ በቀንድ ከብቶች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ፣ በዓለም ከ10 አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም ከወተት ሀብቷ ማግኘት የሚገባትን ያህል ጥቅም...
By Seller 2017-12-22 07:02:06 1 0
Art
How to get escorts in Dubai 0528648070 Verified Bur Dubai Escorts
How to get escorts in Dubai 0528648070 Verified Bur Dubai Escorts She left. She said that Dad...
By heenaparker516 2025-06-06 15:34:33 0 0
Art
Escort Service Fujairah{0527406369} in Escorts Fujairah
Escort Service Fujairah{0527406369} in Escorts Fujairah She left. She said that Dad told her that...
By heenaparker516 2025-06-06 15:39:03 0 0