መጨከክ
መጨከክ
(አሳዬ ደርቤ)
ከሰባት ሰማይ ስር ካለ ጎጆ መሃል
ማጣት፣ መንጣት እንጂ…
ኦናነት ታቅፎ -አይቻልም መጉደል፡፡
.
ልክ እንደ ማረሻው- እንደ መኮትኮቻው
አንገቱን ቀልብሶ ምነው ሆዴን በላው?
የሰለብኩ ይመስል ቆሎውን ከቃጢው፡፡
እንዲህ ነው ሲታጣ- እንዲህ ነው ሲቸግር
ቁራሽ አልባ ሰፌድ- ጥሬ ያጣ ሴደር
የቆፈነው መዳፍ- እንጨት መሰል እግር
የተጠማ እንስራ- ያቀረቀረ አንገት
ምድርን የሚወቅስ- ስቃይ ያዘለ ፊት፤
.
አሁን እግር ጥሎህ ከጎጆው ብትከትም
እግዜሩን አይወቅስም፣ መንግስቱን አያማማም
ቢጠናም ቀኑን ነው- አቀርቅሮ 'ሚረግም፡፡
ግና እንደምታዬው…
ከኩበት ኩይሳው- ከወናው ሙሃቻ
ከአመዱ መሃከል- ከምዳጃው ዳርቻ
መንግስት ተዠርፍጧል- በአምሳለ ጉልቻ
ቁናው ጥሬ ሲይዝ- ‹‹ግብር አምጣ›› ብቻ!
እዚህ ጉልቻ ላይ ወረቀት ይጣዳል
ሪፖርት ተሰፍቶ እንጎቻ ይሆናል፡፡
ከዚያም…
ቁና ሙሉ ቁጥር- አሃዝ ተደምሮ
የተሰጠው አባት-ያው'ና አቀርቅሮ
በረመጥ አገር ላይ እሳት ተቸግሮ፡፡
.
ዋናው ማምከን እንጂ- አብዝቶ መበደል
እንደ እንቅብ፣ ሞሰቡ- ምድጃው ጭር ሲል
ለካስ አንደ ዶሮ- ሰው'ም ይጨክካል፡፡
Search
Categories
- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes
Read More
አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም
(አሌክስ አብርሃም)
ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ...
ወርቃማው ደብዳቤ !
(አሌክስ አብርሃም)
እንዴት ናት ኢትዮጲያ እንዴት ነው አፈሩ ጤናቸው እንዴት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ?ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህናናቸው...
በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ
በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው...
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ
ኢትዮጵያ ከቻይና በመቀጠል ከሶሪያ እኩል የኢንተርኔት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ላይ ገደቦችን በመጣል በዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች ሲል ፍሪደም ሃውስ...