አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም 

0
0

(አሌክስ አብርሃም)

ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ አዳሜ እና አዳሚት ከንፈሩን አሞጥሙጦ እየጎረፈ መሆኑን ሰማን ! እና እንደተባለው ከሆነ ሴትዮዋ ካየቻቸው ከሁለት መቶ በላይ ከንፈሮች ስለባለከንፈሮቹ ተናግራ የተሳሳተችው አንዷን ብቻ ነው አሉ! የትምህርት ደረጃቸውን …ስማቸውን … ኧረ ብዙ ነገር ብቻ ብዙ ነገር መጠንቆል እንደቻለች ነው የተመሰከረላት!! ጌታ ይገስጻት አሜን ! ብለን አሁን ስለዴሞክራሲ እናወራልን:)

ወገኖቸ ከንፈር ስል ግን ምን ትዝ አለኝ ? ከሰሞኑ ፌስ ቡክ ላይ ዞር ዞር ስል አንዳንድ እህቶች ከንፈራቸውን ጎላ አድርጎ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፈው ተመለከትኩ . . አንዳንዴ ፌስቡክ ላይ የምንለጥፈውን ፎቶ ከመለጠፋችን በፊት ሁለት ጊዜ ብንመለከተው ምናለ…የአገር ገፅታን መገንባት ቢያቅተን የዚች ሚስክን የፌስቡክ ሰፈራችንን ገፅታ ሆስፒታል አናስመስላታ ! እንዴ!

ካየኋቸው ሶስት ‹‹ከንፈር ቀደም›› ፎቶዎች ውስጥ ሁለቱ በከፍተኛ ደረጃ አንጀቴን ሲበሉት አንዱ ግን እንባየ በአይኔ እንዲሞላ ሁሉ አደረገኝ ! ከምር ! ነገሩ ‹‹ሴክሲ›› የመሆን ሙከራ ቢሆንም ግን እኔ የከንፈሮቹ መጎሳቆልና በዛ ሁሉ ቻፕስቲክና ሊፒስቲክ እንኳን ሊወዙ አለመቻላቻው ምን ያህል ‹‹ ኦቨር ዩዝ›› እየተደረጉ ነው ብየ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ! ወይስ የኑሮ ጉዳት የደረሰባቸው ከንፈሮች… ?

አንዱ ከንፈርማ ጭራሽ ለፎረንሲክ ምርመራ ከአስክሬን ላይ የተነሳ ሁሉ ነው የሚመስለው …ክስል ከማለታቸው ቋንጣ መሆናቸው ምን አጉል መካሪ ይሆን ያስለጠፋቸው ….መልሸ ደግሞ ኤጭ ባይለጠፍ ቢቀርስ ሰው እንዴት በዚህ ሚስኪን ከንፈር አስተዛዝኖ ላይክ ይቀበላል ብየ ተበሳጨሁ ! ወገብ ይዞ መነሳት በስንት ጠዓሙ ! አሁንኮ ወገኖች በአይፎን መስተዋት ፊት ስልፊ የሚነሱ እህቶች ከእነሱ ይልቀ ስልኩ የሚያማልልበት ደርጃ ላየ ደርሰናል( ይች አገር ግን ወዴት እየሄደች ነው:)

ታዲያ ለአንድ ፖለቲከኛ ወዳጀ ፎቶዎቹን አሳየሁት ፊቱን ቅጭም አድርጎ ከስልኩ ላይ ቀደም ሲል ያስቀመጠውን የሚያምር የከንፈር ፎቶ ከፍቶ ‹‹ተመልከት ዲሞክራሲ ያለበት አገር እና የሌለበት አገር የከንፈር ልዩነት …. እዚች አገር ላይ ወንድ የለም እንጅ ወንድ ቢኖርማ እንዲህ የእህቶቻችንን ከንፈር ያደረቀውን ወያኔን ተፋልመን ማውረድ ነበር ›› ብሎ ዛተ ! እኔም ክፉኛ ዴሞክራሲ ናፈቀኝና ለሌላ ነገር ሳይሆን ለልምድ ልውውጥ ‹‹ይሄ የማነው ከንፈር ›› በማለት ጠየኩ ....ይሄን ከንፈር ከዚህ በፊት የት ነው የማውቀው እያልኩ ….

‹‹የአንጀሊና ጆሊ !!›› አለኝ ኮስተር እንዳለ!! ቀጠል አድርጎም ተመልከት ይሄን የአንጀሊና ጆሊ ከንፈር በአንድ ሳመንት ብቻ ከሃያ ሚሊየን በላይ ህዝብ ላይክ አድርጎታል ! አለኝ ! እውነትም ዓለም "በዴሞክራሲ ፍቅር አብዷል" ብየ እኔም አገሬን በመወከል ያንን ዴሞክራሲያዊ ከንፈር ላይክ አደርኩት ጓደኛየ ቀጠለ " የኛዎቹን ተመልከት የስልሳ ብር ሊፒስቲክ አክስረው ሰላሳ ሰው ብቻ ነው ላይክ … በዛ ላይ ኮሜንቱ ….

ኮሜንት ከፍተን ማንበብ ጀመርን ከአንጀሊና ከንፈር ስር አንዱ ምን ብሏል ‹‹በሳመር እንደሚፈነዳ ውብ አበባ የሚያስጎመጅ ቢታይ የማይጠገብ ከንፈር ››

ከኛው ሚስኪን ከንፈር ስር (ልጅቱ አይኗን አስለምልማ የፌስ ቡክን ወንድ ሁሉ በማማለል ከንፈሯ ለአንድ ሳምንት መነጋገሪያ ይሆን ዘንድ 79 ሰው ታግ አድርጋ የለጠፈችው " ከንፈር ቀደም " ፎቶ ስር

‹‹ አንች ከክፍለ ሃገር አዲስ አበባ ድረስ ፒስታ ፒስታውን በከንፈርሽ እየተራመድሽ ነው እንዴ የመጣሽው ›› የሚል ኮሜንት !! የተረገመ ! ታዲያ ዴሞክራሲ በየት በኩል ይለፍ. ... (ይች አገር ግን ወዴት እየሄደች ነው:)

ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ ወሰደ
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።በዚህ መሰረት የድርጅቱ ሊቀ...
By Samri mola 2017-11-28 08:05:40 0 0
Uncategorized
መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው __
ወጣቱ የአንድን አርሶ አደር ቆንጆ ልጃገረግ ማግባት ፈልጓል፡፡ እናም ወደ አባቷ ቀርቦ ፍቃዳቸው ይሆን ዘንድ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ አባት ልጁን ከእግር...
By Dagmawisol 2017-11-14 07:48:20 0 0
Uncategorized
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመሠራረት ምን ይመሥላል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አየር መንገድ ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ...
By Dagmawisol 2017-12-04 06:54:03 0 0
Uncategorized
‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ››
አሌክስ አብርሃም‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ››(ከድድ አድማስ ኋላ) እዚህ አራዳ ህንፃ የሚባለው አንደኛ...
By Binid Dre 2017-11-25 13:33:42 0 0
Other
Why Choosing the Right Microsoft 365 Services Provider Matters for Healthcare Organizations
Healthcare organizations are experiencing unprecedented digital transformation as they strive to...
By Dannypatil Dannypatil 2026-06-29 10:55:55 0 0