መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው __

0
0

ወጣቱ የአንድን አርሶ አደር ቆንጆ ልጃገረግ ማግባት ፈልጓል፡፡ እናም ወደ አባቷ ቀርቦ ፍቃዳቸው ይሆን ዘንድ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ አባት ልጁን ከእግር ጥፍሩ እስከ እራስ ፀጉሩ እየተመለከቱት አንድ ተግባር ሰጡት፡፡ “ናስኪ ልጄ! ሂድና እዛ እመስኩ መሐል ቁምና እነዚህን ሦስት ኮርማዎች ተራበተራ እለቃቸዋለሁ፡፡ ከሦስቱ ኮርማ ያንደኛውን ኮርማ ጅራት የያዝክ እንደሁ ልጄን እድርልሃለሁ፡፡ ታገባታለህ” አሉት፡፡ ወጣቱ በታዘዘው መሰረት ከግጦሹ ሜዳ ሁኖ መጠባበቅ ጀመረ፡፡ የኮርማዎቹ በረት እንደተከፈተ ትልቅ ኮርማ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቅ ሻኛ የተሸከመ ኮርማ ሲመጣ ተመለከተው፡፡ ወጣቱ “ይሄስ ይለፈኝ የቀጣዩን ኮርማ እይዘዋለሁ” ብሎ ወሰነና አስተላለፈው፡፡ ሁለተኛው ሲመጣ የሚያየውን ማመን አልቻለም፡፡ ከመጀመሪያው በላቀ ግዙፍ ሆነበት፡፡ “የሚቀጥለው ኮርማ (ሦስተኛው ማለቱ ነው፡፡) የፈለገውን ይሁን እሱን እይዘዋለሁ” በማለት ይሄኛውን ወደ ጥግ በመሸሽ አሳለፈው፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ የኮርማዎች በር ሲከፈት ወጣቱ ፈገግ አለ፡፡ ከበረቱ የወጣው ኮርማ ደከም ያለ ነበር፡፡ ወጣቱ የኮርማውን ጅራት ለመያዝ እንዲያመቸው አቋቋሙኝ አስተካክሎ ጠበቀው፡፡ ኮርማው እሱጋ ሲደርስ ዘሎ ወጣበት ነገር ግን የኮርማውን ጅራት መያዝ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ኮርማው ጅራተ ቆራጣ ስለነበር ሙሉ ጅራት አልነበረውምና፡፡

ሕይወት በመልካም አጋጣሚዎች (Opportunities) የተሞላች ናት፡፡ አንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ቀላል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን የተሻለ ይገኛል በማለት እጅ የገባን መልካም እድል ማሳለፍ የማይመጣን እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም ያመለጠ መልካም አጋጣሚ መልሶ እራሱ አይመጣም፡፡ ይህ ማለት ግን ሌላ መልካም አጋጣሚ የለም ማለት አይደለም፡፡ የከፋ ወይም የተሻለ ይኖራል፤ይመጣልም፡፡ እራሱ የበፊቱ ግን አይመጣም፡፡ አንዴ ካመለጠ መልሶ እንደማይገኝ ሲናገሩ መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው ይሉታል፡፡ ቁንጮ ልጆች በአብዛኛው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት ላይ ቁጢጥ አድርገው የሚተውት የፀጉር አቆራረጥ ነው፡፡ መልካም አጋጣሚም እንደመጣ ፊት ለፊት ካልይዙት ዘወር ካለ መላጣ ስለሆነ መያዝ አይቻልም ሲሉ ነው ቁንጮ ነው ያሉት፡፡ ስለሆነም ሁሌም ከፊትህ የመጣን መልካም አጋጣሚ ይዋል ይድር ሳትል ተጠቀምበት ነው መልዕክቱ፡፡

ምንጭ፡ NEVER MISS FIRST OPPORTUNITY!

(#ምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)

17-09-2007 ዓ.ምhttps://www.facebook.com/groups/bookforall/?fref=nf

Like
1
ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
‹‹ስጋን ማመን አርዶ ነው!››
‹‹ስጋን ማመን አርዶ ነው!››(አሳዬ ደርቤ)‹‹ምሳዬን የት...
By Assaye Derbie 2017-11-12 07:31:32 0 0
Shopping
Can Minidumperfactory Electric Garden Loader Manage Materials Across Garden Sites
Electric Garden Loader usage has become increasingly common in daily garden work as landscaping...
By Minidumperfactory Minidumperfactory 2025-12-18 07:00:40 0 0
Uncategorized
የመጀምሪያዋ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የጦር መርከብ ኢትዮጵያዊ የሆነ ስም ከመያዟ በፊት P.C. 1616 ትባል ነበር። ይህች ዘመናዊ መርከብ ከአሜሪካን መንግስት በእርዳታ የተገኘች ነበረች።
1616 ኢትዮጵያዊ የሆነ ስም እንዲወጣላት በማስፈለጉ በጊዜው የነበረውን ተጨባጭ ሁ...
By Dagmawisol 2017-12-16 09:06:27 0 0
Sports
Our security vs their offense: Atlanta Falcons
The Contemporary Orleans Saints and Atlanta Falcons will duke it out inside the Superdome this...
By BgmntFtball BgmntFtball 2026-02-06 06:21:21 0 0
Uncategorized
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመሠራረት ምን ይመሥላል?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አየር መንገድ ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ...
By Dagmawisol 2017-12-04 06:54:03 0 0