መጨከክ

መጨከክ
(አሳዬ ደርቤ)
ከሰባት ሰማይ ስር ካለ ጎጆ መሃል
ማጣት፣ መንጣት እንጂ…
ኦናነት ታቅፎ -አይቻልም መጉደል፡፡
.
ልክ እንደ ማረሻው- እንደ መኮትኮቻው
አንገቱን ቀልብሶ ምነው ሆዴን በላው?
የሰለብኩ ይመስል ቆሎውን ከቃጢው፡፡
እንዲህ ነው ሲታጣ- እንዲህ ነው ሲቸግር
ቁራሽ አልባ ሰፌድ- ጥሬ ያጣ ሴደር
የቆፈነው መዳፍ- እንጨት መሰል እግር
የተጠማ እንስራ- ያቀረቀረ አንገት
ምድርን የሚወቅስ- ስቃይ ያዘለ ፊት፤
.
አሁን እግር ጥሎህ ከጎጆው ብትከትም
እግዜሩን አይወቅስም፣ መንግስቱን አያማማም
ቢጠናም ቀኑን ነው- አቀርቅሮ 'ሚረግም፡፡
ግና እንደምታዬው…
ከኩበት ኩይሳው- ከወናው ሙሃቻ
ከአመዱ መሃከል- ከምዳጃው ዳርቻ
መንግስት ተዠርፍጧል- በአምሳለ ጉልቻ
ቁናው ጥሬ ሲይዝ- ‹‹ግብር አምጣ›› ብቻ!
እዚህ ጉልቻ ላይ ወረቀት ይጣዳል
ሪፖርት ተሰፍቶ እንጎቻ ይሆናል፡፡
ከዚያም…
ቁና ሙሉ ቁጥር- አሃዝ ተደምሮ
የተሰጠው አባት-ያው'ና አቀርቅሮ
በረመጥ አገር ላይ እሳት ተቸግሮ፡፡
.
ዋናው ማምከን እንጂ- አብዝቶ መበደል
እንደ እንቅብ፣ ሞሰቡ- ምድጃው ጭር ሲል
ለካስ አንደ ዶሮ- ሰው'ም ይጨክካል፡፡
ፍለጋ
Categories
- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes
Read More
የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90...
አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም
(አሌክስ አብርሃም)
ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ...
~~~~~~ Alert! Alert! Alert! ጥንቃቄ!!! ~~~~~
በሳዑዲ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን~~~~~~~~//~~~~~~~~//~~~~~~~~~ከነገ ማለትም እ.ኤ.አ ከኖቬምበር 15 ማለዳ ጀምሮ ላልተወሰኑ...
ከነጠላው ስር !!
(አሌክስ አብርሃም)
የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ ሁሉ በግ መስሎን ተበላን ጓዶች !!እኛ ኢትዮጲዊያን በተለይ በዚህ ሰአት ‹‹ፈጠራ...
መርከቧ በባሕሩ ላይ፣ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ላይ?
(ዳንኤል ክብረት)
ታዋቂው ሩሲያዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ባለሞያ ዶክተር ሰርጌይ ላቭሮቭ ‹Reformation in the...