Ethiopian Social Network Ethiopian Social Network
Search Results
ሁሉንም ዕይ
  • አባል ይሁኑ
    Sign In
    አዲስ ምዝገባ
    ፍለጋ

Directory

  • Users
  • Posts
  • Pages
  • Groups
  • Events
  • Blogs
  • Marketplace
  • Funding
  • Offers
  • Movies
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    በኬንያ በታክስ ጭማሪ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተቃውሞው ቀጥሏል
    በኬንያ ረቂቅ የታክስ ጭማሪ አዋጅን በመቃወም በናይሮቢ እና በሌሎችም አካባቢዎች በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች የተቃውሞ ሰልፍ አካሂደዋል። የታክስ ጭማሪውን በመቃወም ለወራት በማኅበራዊ ሚዲያ ሲደረግ የነበረው ዘመቻ፣ ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተቀይሯል። የታክስ ጭማሪው የሚደረገው ብድርን ለመክፈል እና ለልማት ሥራዎች እንደሆነ መንግስት ይገልጻል። መንግስት ከረቂቅ አዋጁ ውስጥ የተወሰኑትን እንደሚተው ቢያስታውቅም፣ ዛሬ ሐሙስ የተቃውሞ ሰልፉ መቀጠሉ ታውቋል። የታክስ...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያን ስምምነት ያጣጣለችው ደቡብ ኮሪያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ልትልክ እንደምትችል አስታወቀች
    ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ በጦርነት ወቅት የጋራ መከላከያ እንዲኖራቸው ያደረጉትን ስምምነት ያወገዘው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት፣ ለዩክሬን ጉዳት የማያደርሱ አቅርቦቶችን በገደብ ለመስጠት የሚከተለውን ፖሊሲ በድጋሚ እንደሚያጤነው አስታውቋል። የፕሬዚዳንቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን ሐሙስ ዕለት አስተያየታቸውን የሰጡት፣ ጽህፈት ቤቱ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ፒዮንግያንግ ላይ ባደረጉት ጉባዔ የደረሱበትን ስምምነት...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    በሉዊዚያና አሥርቱ ትዕዛዛት በትምህርት ክፍል ውስጥ እንዲሰቀል የሚያዝ አዋጅ ጸደቀ
    በአሜሪካ በሉዊዚያና ግዛት አሥርቱ ትዕዛዛት በሕዝብ ትምህርት ቤት ክፍሎች ውስጥ እንዲሰቀል ትላንት ረቡዕ በአዋጅ ተደንግጓል። ውሳኔው በሪፐብሊካኖች ቁጥጥር ሥር ያለው የግዛቲቱ የሕግ አውጪ ም/ቤት የወግ አጥባቂዎችን አጀንዳ ለማስፈጸም የወሰደው ሌላ እርምጃ እንደሆነ በመነገር ላይ ነው። በሪፐብሊካዊው ሃገረ ገዥ ጄፍ ላንድሪ ትላንት የተፈረመው ሕግ፣ የፖስተር መጠን ያለውና በቀላሉ መነበብ የሚችል አሥርቱን ትዕዛዝ የያዘ ሰሌዳ በመንግስት በጀት በሚንቀሳቀሱና...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    የኤርትራ መሠረታዊ መብቶች ስልታዊ በሆነ መንገድ ታፍነዋል - ተመድ
    የኤርትራ መንግሥት የሕዝቡን መሠረታዊ መብቶች እና ነጻነቶች በኃይል እና በዛቻ በማፈን ሥልጣኑን ለማጠናከር እየተጠቀመበት ነው ሲሉ የሰብአዊ መብቶች ባለሞያ አስታወቁ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ ልዩ የሰብአዊ መብቶች ሪፖርት አቅራቢ የሆኑት ሞሐመድ አብደልሰላም ባቢከር ሐሙስ ዕለት ለድርጅቱ ሰብአዊ መብቶች ምክርቤት ባደረጉት ንግግር "በኤርትራ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ነው። በዘፈቀደ እና በድብቅ የሚፈጸሙ እስር እና የግዳጅ መሰወርን ጨምሮ ከባድ የሰብአዊ...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    የውጭ ባንኮች በኢትዮጵያ ሊሠሩ የሚችሉበትን ድንጋጌ የያዘ የዐዋጅ ረቂቅ ይፋ ኾነ
    የውጭ ባንኮች፣ በኢትዮጵያ በባንክ ዘርፍ የሚሳተፉበትን አግባብ የሚዘረዝር “የባንክ ሥራ ረቂቅ ዐዋጅ” ተዘጋጅቶ ይፋ ኾኗል። የዐዋጅ ረቂቁ፣ የውጭ ባንኮች፣ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት የሚይዙትን ተቀጥላ ወይም ቅርንጫፍ ለመክፈት ፈቃድ እንደሚያገኙ ይደነግጋል። ይኸው ረቂቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በዛሬ ኀሙስ ስብሰባው ላይ ውይይት ከሚያደርግባቸው የዐዋጆች ረቂቆች መካከል አንዱ እንደኾነ ተጠቅሶ የነበረ ቢኾንም ውይይት አልተደረገበትም።...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    በማረቆ ልዩ ወረዳ እና በምሥራቅ ጉራጌ ግጭት 88 ተጠርጣሪዎች ታሰሩ
    በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በማረቆ ልዩ ወረዳ እና በምሥራቅ ጉራጌ ዞን መስቃን አካባቢ ባለው ግጭት የጠረጠራቸውን 88 ሰዎችን ማሰሩን፣ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ። የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መንግሥት ሰዎችን እያሰረ ያለው፣ “ከሕግ አግባብ ውጭና ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ባልተጣራ ማስረጃ ነው፤” ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    በኖኖ ወረዳ የሠርግ ላይ ጥቃት ሙሽሮችን ጨምሮ 27 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
    በምዕራብ ሸዋ ዞን በኖኖ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በሠርግ ሥነ ሥርዓት ላይ በተፈጸመ ጥቃት 27 ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች 17 መቁሰላቸውን፣ በወረዳው የቢፍቱ ጃለላ ቀበሌ አስተዳዳር እና ተጎጂዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ጥቃቱ የደረሰበት የጊፍቲ ጃለላ ቀበሌ ሊቀ መንበር አቶ ነስሩ ዑመር፣ በዕለቱ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ በተወረወረው ቦምብ እና በተከፈተው ተኩስ ከተገደሉት ውስጥ ተጋቢ ሙሽሮችም እንደሚገኙበት ገልጸዋል። ጥቃቱን ተከትሎ...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • VOA - Amharic shared a link
    2024-06-21 08:34:02 -
    AMHARIC.VOANEWS.COM
    በኢትዮጵያ የሚኖሩ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ጠየቁ
    በኢትዮጵያ ያሉ ስደተኞች፣ ከአገልግሎት አቅርቦት እና ከጸጥታ ጋራ የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጥሪ አቀረቡ። በሰሜን ጎንደር ዞን በዓለምዋጭ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ በአካባቢያቸው፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውጥ ተደርጎ፣ አንድ ስደተኛ በበራሪ ጥይት መቁሰሉን ገልጸው፣ በኹኔታው ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል፡፡ በምዕራብ ጎንደር ዞን ያሉት...
    0 Comments 0 Shares
    Please log in to like, share and comment!
  • Displaying (28889-28896 of 303214)
  • «
  • Prev
  • 3610
  • 3611
  • 3612
  • 3613
  • 3614
  • Next
  • »
© 2025 Ethiopian Social Network Amharic
English Amharic
ያግኙን Directory