የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ ወሰደ

0
0
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

በዚህ መሰረት የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ አባይ ወልዱ ከድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነታቸው ተነስተው በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ዝቅ ብለው እንዲያገለግሉ ወስኗል።

በተጨማሪም የድርጅቱ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ በየነ ምክሩም ወደ ድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ዝቅ ብለው እንዲሰሩ መወሰኑን ድርጅቱ ለጣቢያችን በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ከዚህ ባለፈም የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወይዘሮ አዜብ መስፍንን ከስራ አስፈጻሚ አባልነታቸው እና ማዕከላዊ ኮሚቴው ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑንም ገልጿል።

ድርጅቱ ከዚህ በተጨማሪም ለሌሎች ሁለት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

እርምጃው ማዕከላዊ ኮሚቴው ያካሄደውን ጥልቅ ግምገማ ተከትሎ የተወሰደ ነው።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ባለፈው ሳምነት ባወጣው መግለጫ በአመራር ስትራቴጂካዊ ፖለቲካዊ ሁነቶች፣ ሁለንተናዊ የልማታዊ ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥ እና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ዙሪያ በጥልቅ በመገምገም ያሉትን መሰረታዊ ክፍተቶች በዝርዝር ማየቱን ገልፆ ነበር።

በትግልና በመርህ የተመሰረተ አንድነት አለመኖር፣ በመጠቃቃትና መከላከል ዝምድና ላይ መመስረት፣ የፀረ ዴሞክራሲ ጥልቅ አስተሳሰብና ተግባራት መኖራቸውን መገምገሙንም በመግለጫው ማስታወቁ ይታወሳል።

በተጨማሪም የወጣቱን ትውልድ እና የምሁሩን አቅም በመገንባት፣ በማሰለፍና ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ መሰረታዊ ጉድለቶች መኖራቸውን ገምግሞ ነበር።

በክልሉም ትራንስፎርሜሽን ከማረጋገጥ አኳያ መሰረታዊ ስትራቴጂካዊ የአመራር ችግር እንደነበረበት በመገምገም፥ ባለፉት አመታት በተደረገው እንቅስቃሴ በገጠርና ከተማ የተመዘገቡ የልማት ድሎች መኖራቸውን ያረጋገጠ ቢሆንም ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማሳካት አኳያ የህዝቡ ተጠቃሚነት ከፍላጎቱ ጋር ሲመዘን ግን መሰረታዊ ችግሮች እንደነበሩበት በመገምግም ማረጋገጡንም ነበር በመግለጫው የጠቀሰው።

ማእከላዊ ኮሚቴው በቀሪ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ላይ ጥልቅ ሂስና ግለ ሂስ የቀጠለ ሲሆን፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ የአመራር መልሶ ማደራጀት እንደሚያደርግ አስታውቋል ።


በሙሉጌታ አፅብሃ
 
 
ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)፡ፒስ ነው ጋይስ?!ቃሉን የማያጥፈው መንግስታችን "መጪው ዘመን የከፍታ ነው" ባለው መሰረት ከሰሞኑ ዶላሩን...
By andualem 2017-11-12 15:14:07 0 0
Uncategorized
ተዋናይ ዳንኤል ተገኝ ከ80 በላይ ለሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች መሉ አልባሳቱን ለገሰ
ETHIOPIA – ተዋናይ ዳንኤል ተገኝ ከ80 በላይ ለሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች መሉ አልባሳቱን ለገሰ አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ለአገር እና ለሕዝብ...
By binid 2017-11-12 15:07:32 0 0
Uncategorized
Selling
Product
By Hana 2017-11-25 17:05:20 0 0
Uncategorized
ብልጽግና
"3 And he shall be like a tree planted by the rivers of water, that bringeth forth his fruit in...
By Amanunegn 2017-12-03 13:00:45 0 0
Uncategorized
70 ሜትር ከፍታ ባለው ገመድ ላይ የተራመደው ግለሰብ አዲስ ክብረ ወሰን ይዟል
ከመሬት230 ጫማ ወይም 70 ሜትር ከፍታ ላይ በታሰረ ቀጭን ገመድ ላይ የተራመደው ግለሰብ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ይዟል። ናታን ፓውሊን የተባለው...
By Dawitda 2017-12-15 06:18:58 0 0