አስገራሚ ቃለ ምልልስ -ሙጋቤ

0
0

”መቼም ሙጋቤ መልካም ሰው ነው” ይላል- መንግስቱ ሃይለማርያም የክፉ ቀን ደራሹን ማመስገን ሲጀምር።በርግጥ የሙጋቤን መልካምነት ሚያውቀው ስግጎ ማረፊያ ያደረገው መንግስቱ ነው።ለብዙዎች ግን ጥቁሩ ሰዉዬ ገራሚ መሪ ነው።የዚህን ገራሚ ሰው አስገራሚ ቃለ ምልልስ ዛሬ እናስታውስ እስኪ….
1. የዛሬ ዓመት ኣካባቢ ይመስለኛል ምርጫ ኣሸንፎ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ነው።ኣንድ ደቡብ ኣፍሪካዊ ጋዜጠኛ ጠየቀ።”እርስዎ በዘንድሮው ምርጫ ላይ ለምን የአውሮፓ ህብረትንና አሜሪካን እንዲታዘቡ ኣልጋበዙም??”
”እነሱ መቼ ጠርተውን ያውቃሉ?” የሙጋቤ መልስ ነበር።
2.ይሄው ምርጫ ከመካሄዱ በፊት ”መቼ ነው ከስልጣን የሚለቁት?” ሲል አንድ ምዕራባዊ ጋዜጠኛ ሙጋቤ ኣምርሮ ‘ሚጠላትን ጥያቄ ጠየቀ።”ህዝቡን ለማን ትቼ ነው ስልጣን ምለቀው?” ሲል ነበር- ኣወዛጋቢው ጥቁር ሰውዬ መልሶ የጠየቀው።
3.የሆነ ሰሞን ደግሞ ኡጋንዳ ተመሳሳይ ጋብቻ ከለከለች ተብሎ ምድረ ነጭ ተንጫጫ።ጭር ሲል አልወድም ኣይነት ባህሪ ያለው ሙጋቤም ”አሜሪካ በዚምባብዌ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ እንድፈቅድ ከፈለገች መጀመሪያ ኦባማ እኔን ያግባኝ” ሲል ተደመጠ።
4.በዚያው ሰሞን ገራሚውን ሰውዬ ለቃለመጠይቅ ከከበቡት ጋዜጠኞች ኣንድ እንግሊዛዊ ”እርስዎ እኮ እድሜዎትም ገፍቷል፤እና ስልጣን ለምን ኣይለቁም?” ሲል ጠየቀው ….
”ስልጣን በእድሜ ከሆነ ሂድና ንግስት ኤልሳበጥን አርጅተሻልና ንግስትነት ይብቃሽ በላት” ኣለው።ሃሃሃሃ……….. የሆነ አሽሙረኛ እኮ ነው!!
5.ሰሞኑን ደግሞ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነና ከማንዴላ አዳራሽ በር ላይ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን ሰበሰበ።ትንሽ ነገር ካወራ በሁዋላእድሉን ከፊቱ ለተኮለኮሉት ጋዜጠኞች ሰጠ።አንድ ፈረንሳዊ ጋዜጠኛ እጁን አወጣ።እድል ሰጠው።
”እርስዎ ዝምባብዌ ለሚገኝ ኣንድ ሚዲያ በሃገርዎ ሴቶችና ወንዶች እኩል እንዳይደሉ የሚገልጽ መረጃ ተናግረው ነበር፤ይሄ ከምን የመነጨ ነው ?”ጋዜጠኛው ጠየቀ።
”ኣዎ ብያለሁ…” ብሎ ጀመረ ጥቁሩ አወዛጋቢ ሰው ”…ብያለሁ! ሴትና ወንድ በተፈጥሮ የተለያዩ ናቸው።ወንድ ማድረግ ሚችለውን በሙሉ ፣ሴት አታደርገውም።ለምሳሌ አንድ ወንድ ልጅ ማጥባት አይችልም ጌይ ቢሆን እንኳ ልጅ ማጥባት ኣይችልም።” ሃሃሃ ሁሉም ሰው በሳቅና በሃፍረት ስሜት ውስጥ ነበር ።
ስለሙጋቤ የማይተኙት የምዕራቡ ዓለም ብዙሃን መገናኛዎች የሚተነፍሰውን ኣየር ሳይቀር ዜና መስራት ልማዳቸው ነው።ሽማግለውም የዋዛ አይደለም- ባገኘበት እነሱን ማሸማቀቅ ደስ ይለዋል።ሰሞኑንም ”ደረጃ ሲወርድ አዲሳባ ላይ ወደቀ!” ብለው አስገራሚ የፎቶና የካርቱን ዜና እየሰሩበት ነው።በተለይ እንደ ደይሊ ሜይል በዚህ ጉዳይ ሙጋቤን የቀለደበት የለም።ከነ ቢዮንሴ ኖውልስ ጋር… ከዝንጀሮ ጋር… ከሌሎችም አስቀያሚ ሁኔታዎች ጋር እያጀቡ ዜና ኣድርገውታል።
ምዕራቦቹ [በተለይ እንግሊዞች] ሙጋቤን ሚጠሉበት ምክንያት ግልጽ ነው።ከእንግሊዝ ከበርቴ ይልቅ የራሱን ድሃ ገበሬ መርጦ እነሱን ስላባረረ ነው።ከዚያም በሁዋላ ለፖሊሲያቸው ኣላጎበድ ድም ስላለ ነው።እውነት እናውራ ከተባለ የአፍሪካውያን የነጻነት ታጋይ ማንዴላ ሳይሆን ሙጋቤ ነው።ማንዴላ ስልጣን ይዞ ካቢኔውን ሲያዋቅር አብዛኞቹ ነጮች ነበሩ።[ጥቁር አፍሪካውያን በገዛ ኣገራቸው ግድያና መገለል የበረታባቸው ግን በነጮች ነው]።

ስልጣን ርስት አይደለም ፣ ስልጣን በሊዝ የያያዙ ለሚመስላቸው የአፍሪካ መሪዎች የማስጠንቀቂያ ደወል ነው

Search
Categories
Read More
Uncategorized
.me
About .ME Are you trying to find a way to take control of your online identity? Maybe trying to...
By Dawitda 2017-11-15 16:52:32 0 0
Uncategorized
‹‹ስጋን ማመን አርዶ ነው!››
‹‹ስጋን ማመን አርዶ ነው!››(አሳዬ ደርቤ)‹‹ምሳዬን የት...
By Assaye 2017-11-12 07:31:32 0 0
Networking
Cсылки для продвижения сайта в яндексе
На 2026-2027 год, купить ссылки для продвижения сайта в яндексе является стратегическим...
By haveyona23 2025-11-09 09:46:04 0 0
Uncategorized
_ ጥሩነት ለራስ ነው:: __
ሥራ ፈላጊው ለሥራ ውድድር የቃል መጠይቅ ፈተና ለመውሰድ መስሪያ ቤት ላይ ተገኝቷል፡፡ ኮሪደር ላይ ሆኖ የፈተና ጊዜውን ሲጠባበቅ ሳለ የወዳደቁ ቁርጥራጭ...
By Seller 2017-11-25 09:01:10 0 0
Uncategorized
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ...
By andualem 2017-11-12 15:13:23 0 0