ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __

ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
ትንሹ ልጅ እናቱን “ማሚ ለምን ታለቅሻለሽ?” ሲል ጠየቃት “ምክንያቱም ሴት ስለሆንኩ” ስትል መለሰችለት እናቱ፡፡ “አልተረዳሁሽም ማም” አለ መልሶ፡፡ እናቱ በዚህ ጊዜ እያቀፈችው “በፍጹም አይገባህም…ልትረዳው አይቻልህም ልጄ” አለችው፡፡ ከቆይታ በኋላ የአባቱን መምጣት ያስተዋለው ትንሹ ልጅ አባቱን ጠጋ ብሎ “አባ ለምንድ ነው እናቴ ያለ ምክንያት እንዲሁ የምታለቅስ?” ሲል ጠየቀው፡፡ “ሁሉም ሴቶች ያለ ምክንያት ነው የሚያለቅሱት” ሲል መለሰለት አባቱ፡፡
ትንሹ ልጅ አድጎ ትልቅ ሰው ቢሆንም ሴቶች ያለምክንያት ማልቀሳቸው እንቆቅልሹ ስላልተፈታለት እንዲነገረው ለፈጣሪ ጥያቄውን እንዲህ አቀረበ “አምላክ ሆይ ለምንድን ነው ሴቶች እንዲሁ በቀላሉ የሚያለቅሱት? ምክንያቱ ምን ይሆን?” ሲል አቀረበ “ሴትን ስፈጥራት ልዩ አድርጌ ነው፡፡ የሴትን ትከሻ አጠንክሬ ነው የሰራሁት፡፡ ይህም የሆነው የንሮን ሸክም ደግፎ እንዲይዝ እንዲያም ሁኖ የእናንተን ምቾት ለመስጠት ሳትታክት እየታተረች ነው፡፡ ይሄም ብቻ አደለም ውስጣዊ ጥንካሬንም አድያታለሁ፡፡ ስለሆነም ልጅን ወልዶ የማሳደግ ጽናትን በልጅ መገፋትንና ክፋነት ችላ ሁሉም ያበቃለት፣ የቆመ በመሰለበት ሰዓት እሷ በብርታት ስራዋን ትሰራለች፤ ያለምንም ቅሬታም ቤቷን ሸክፋና አሙቃ ትይዛለች፡፡ በሌላውም በኩል ስስ ስሜት ስለሰጠኋት በማንኛውምና በሁሉም ሁናቴ ለልጇ ያላት ፍቅር ይበልጥባታል፤ ልጇ ቢዘነጋትም ያልተገደበ ፍቅሯን አትነፍገውም፡፡ የባሏን ልብ ትጠብቅ ዘንድም ከጎን አጥንቱ ተፈጠረች፡፡ ጥሩ ባል ሚስቱን እንደማይጎዳም ታውቅበት ዘንድ ጥበብን ሰጥቻታለሁ፡፡ በነገሮች ባያስደስታትም በቁርጡ ሰዓት ከሱ ጎን ለመቆም ወደኋላ አትልም፡፡ በመጨረሻ የምታፈሰው እንባን ሰጠኋት ይሄም ባስፈላጊ ጊዜ የምትጠቀምበት ትልቅ ሃብቷ ነው፡፡”
“አየህ ልጄ ! የሴት ልጅ ውበት በለበሰችው ልብስ ማማር አይደለም፡፡ ወይም ደግሞ ፀጉሯን ባሳመረችበት የፀጉር አሰራር ሳይሆን የሴት ልጅ ውበት የሚታየው በዓይኗ ነው፡፡ ምክንያቱም የፍቅር ማረፊያ ወደ ሆነ ልቧ መዝለቂያ ጎዳናው ዓይኗ ነውና፡፡” ይኸን ጊዜ ሴት ልጅ የምታላቅሰው ከፍቅሯ ብዛት የተነሳ እንደሆነ ሚስጥሩ ገባው፡፡
ምንጭ፡ Why Women Cry?
(#ምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)
09-03-2008 ዓ.ም

- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes