በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡

0
0

ተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር አያሌ ዜጐችን በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት ተምረው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ማስቻሉ በጥናት ተደርሶበታል፡፡
ይሁን እንጂ የተከታታይ ትምህርት አሰጣጡና ተመራቂዎች ጥራትና ውጤታማነት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ከትምህርት ተቋማቱ ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የሚደረግላቸው ክትትል ዝቅተኛ ነው፡፡

የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሩን ጥራት ከሚፈታተኑት ውስጥ የትምህርት መስኮች አግባብ ያለው ጥናት ሳይደረግባቸው መከፈትና ለሚሰጡ ትምህርቶች በቂ መርጃ መሣሪያዎች አለመኖራቸው ነው፡፡

ለተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ደግሞ በአብዛኛው ከሚፈለገው ደረጃ በታች የሆኑና በትርፍ ጊዜ የሚሰሩ መምህራንን መድቦ ማሰተማር በዋናነት ጥራቱን ጥያቄ ውስጥ የሚከቱት መሆኑን ነው ጥናቶች የሚያስረዱት፡፡

የፈተናና የነጥብ ወይንም ማርክ አሰጣጥ ስርዓቱም የላላ ነው ተብሏል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለው የትምህርት አሰጣጥ ጥራትን ለመቆጣጠር የሚያስችለውን መዋቅር አዘጋጅቶ ለትምህርት ሚኒስቴር ቢልክም ምላሹ እንደዘገየበት መናገሩን መዘገባችን ይታወሣል፡፡

የተከታታይ ትምህርት መርሃ ግብሩ በመደበኛው የትምህርት ጊዜ ለመማር እድል ያላገኙ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ይታወቃል፡፡

(በየነ ወልዴ)sheger fm

ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)፡ፒስ ነው ጋይስ?!ቃሉን የማያጥፈው መንግስታችን "መጪው ዘመን የከፍታ ነው" ባለው መሰረት ከሰሞኑ ዶላሩን...
By andualem 2017-11-12 15:14:07 0 0
Uncategorized
መርከቧ በባሕሩ ላይ፣ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ላይ?
(ዳንኤል ክብረት) ታዋቂው ሩሲያዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ባለሞያ ዶክተር ሰርጌይ ላቭሮቭ ‹Reformation in the...
By binid 2017-11-25 13:23:15 0 0
Uncategorized
አንዳንድ ቅዳሜዎች
አንዳንድ ቅዳሜዎች፡በጣም ጠፋሁ አይደል!!; አይ ኖው…. አይ ኖው….አይ ሚስ ዩ ቱ ጋይስ፡፡ያው መጥፋቴ የቢዴና ነገር ሆኖብኝ...
By andualem 2017-11-12 15:15:06 0 0
Uncategorized
በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ
በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው...
By Dawitda 2017-11-13 09:59:25 0 0
Uncategorized
ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
 ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __ ትንሹ ልጅ እናቱን “ማሚ ለምን ታለቅሻለሽ?” ሲል ጠየቃት “ምክንያቱም...
By Dawitda 2017-11-17 07:15:51 0 0