ስድስተኛው ገፅ!

0
0

ስድስተኛው ገፅ!
«ዘውድአለም ታደሰ»

እንዴት ናችሁ ክቡራትና ክቡራን? እነሆ ሰአቱን ጠብቆ የማይከፈለው የፌስቡኩ ጥፎ አዳሪ “ሞአ አበሳ ዘእብነገደ ቄራ ሚስተር ዜዶ” ከች ብሏል! ለቀናት የተቦከመው የመፃፍ ሙዱም አብሮት ነውና ይከታተሉት ....!

(የላይኛዋ ማስታወቂያ ነች ጓዶች :) )

እህ ....ከተማው ላይ ምን አዲስ ነገር አለ? ሃገሪቷ ፒስ ነች? አይ ሆፕ እስካሁን አልሸጡንም! ለኛኮ አይነግሩንም! ምን ይታወቃል የዚህ መንግስት ነገር ጓዶች .. አንዱ የጠገበ ኢንቨስተር መጥቶ «ኢትዮጵያን መግዛት እፈልጋለሁ» ቢልኮ ልማታዊው መንግስታችን «ከነህዝቡ ነው ያለህዝቡ?» ብሎ ከመጠየቅ ወደኋላ አይልም! ለነገሩ መሸጥ ያባት ነው። ጅቡቲንስ ሸጠን አይደል ሿሿ የተሰራነው?
በቃ መሸጥ ነው! ነጋዴው እቃ ይሸጣል! ፓስተሩ ሆሊ ዋትር እያለ የታሸገ ውሃ ይሸጣል! ቄሱ መቁጠሪያ ይሸጣል! መንግስት መሬት ይሸጣል! በቃ መሸጥ መሸጥ መሸጥ ነው። መግዛት ኢንጅሩ!

እኔማ ምፈራው ድንገት ጠኋት ከንቅልፌ ስነሳ ለአንዱ ህንዳዊ ሽጠውኝ እንዳያድሩ ነው። ኢማጂን ጓድ ህንዱ «በሊዝ ስለገዛሁህ ሳልፈቅድልህ የትም እንዳትነቃነቅ» ምናምን ብሎ ኦርደር ሲሰጠህ ሃሃ የምር መንግስታችንኮ ሃይለኛ ነጋዴ ነው። ኢንቨስተር ራሱ ሲጠራ “ኑ ርካሽ መሬትና ርካሽ የሰው ጉልበት አለ” ብሎ ነው! መንግስት ያቀለለውን ማን ያከብረዋል? ማንም!

እና እየሰጋሁ ነው ! ትናንት መሬት የመንግስት ነው ያለ መንግስት ነገ ህዝቡም የመንግስት ነው ቢል የማን ያለህ ልል ነው? መሬቱ ሲያልቅ ያው ህዝብ በሽቦ ታጥሮ በሊዝ መቸብቸቡ አይቀርም! ሃሃ ጠርጥር ይላል ስድስተኛው ገፅ «ጠ ር ጥ ር» ስልህ!!

እና ሐገር አማን ነው ወይ? አረረረረ ዋናውን ወሬ ረስቼው .... ዶክተር አሸብር የዋና ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንቱ ዶክተር አሸብር፣ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንቱ ዶክተር አሸብር ፣ አሁን ደሞ ለፉትቦል ፌዴሬሽን ፕሬዘዳንትነት እየተወዳደሩ ነው አሉ። ካሸነፉ በስልጣን ሃትሪክ ይሰራሉ! ወይ ዶክተርር አሸብር! የኢትዮጵያ ፉትቦል ፌዴሬሽንን ለፊፋ ከስሰው ያስቀጡ መሬ ሼባ! ስምን መላክ ያወጣዋል እውነትም አሸብር! እኛ በቀን ሶስቴ መብላት አቅቶናል እሳቸው ለሶስተኛ ስልጣን ይባጠሳሉ ሃሃ ይመቻቸው አቦ!

በተያያዘ ወሬ ... ትግራይ ሎቆዳማይ ሎታጋይ ሎአቶ ሎቶክለወይኒ የሰጠችውን ውክልና አነሳች አሉ!! የትግራይ ሴቶች ሊግም ተሰብስቦ ሼባውን አወገዛቸው አሉ! ምፅ “የወደቀ ዛፍ መጥረቢያ ይበዛበታል” አለ ሮቤል ኪሮስ ምፅ ነገ ደግሞ የአገው ብሔረሰብ ሸማቾች ማህበር ተነስቶ እንዳያወግዛቸው ብቻ!

ግን የምር ስናወራ የሰውየው ጥፋት ምንድነው? ይሄን ፅሁፍ ከመፃፌ በፊት ብራዚል ውስጥ የሚገኝ የአንድ ሪዞርት ማስታወቂያ እያየሁ ነበር። ማስታወቂያው ላይ ብዙ ቺኮች በዋና ፓንት ሆነው «ኑ እየጠበቅናችሁ ነው» ይላሉ! ቺኮቹን ሳይ እኔ ራሱ ተነስተህ ሂድ ተነስተህ ሂድ ነው ያለኝ ! አይ ስዌርን :)

አቶ ተክለወይኒኮ ሂዱና ዘሙቱ አላሉም! በቃ ቀሽት ቀሽት ቺኮች አሉን ነው ያሉት። የዚን ህዝብ ሳይኮ በልተውታላ! አሁን ማን ይሙት ይሄ ወጣት ለአክሱምና ላሊበላ ደንታ አለው? ሶፍ ኦመር ዋሻን ተመልከት ብትለው ይሰማሃል? መቀሌ ላይ ያለው የዩሃንስን ቤተመንግስት ወይም ደሳለኝ የሚባለውን አህያ ሃውልት ጎብኝ ብትለው በጄ ይላል? ማንም አወገዘ አላወገዘ ካቶ ተክለወይኒ ደፋር ማስታወቂያ በኋላ ህዝቤ ወደመቀሌ እንደሚጎርፍ የታወቀ ነው። ፕሮሞሽኑ ኢሞራል ነው ምናምን ለማለትኮ የሆነ ሁሉንም የሚያግባባ የሞራል ግራውንድ ሊኖር ይገባል! ቆንጆ ነገር ማየት ማይፈልግ ማን ነው? እነሳምሶን ማሞ ለሳሙና ማስታወቂያ ልብስ አጥባ ማታውቅ ያበደች ሞዴል ሚያሳዩንኮ ህዝባችንን ስለሚያቅቁት ነው። የቲቪ ማስታወቂያዎቻችን በቆነጃጅት የተሞሉት ለምንድነው? ... መልሱ ግልፅ ነው። ሁላችንም ቆንጆ ሴቶች ማየት እንወዳለን! ይሄን የተሸፋፈነ የማህበረሰብ ስነልቦና ነው እንግዲህ አቶ ተክለወይኒ በይፋ የተናገሩት!

ኤኒ ሃው ...ምንም አልክ ምን ከአቶ ተከለወይኒ ፀዴ ፕሮሞሽን በኋላ መቐለን የማየት ጉጉቴ 11 በመቶ ጨምሯል ነው ምልህ ዘመዴ!
ውበት የነሳቸው ፣ ባል የጠረረባቸው የሴት ሊጎች ተደራጅተው ተንጫጩ አልተንጫጩ ሁ ኬርስ? ይህን ሁሉ ውበት መቐለ ላይ ያፈሰሰው ጀሊሉን እያመሰገንን ቀዝቃዛ ቢራችንን እየተጎነጨን እኔና ተጋዳላይ ተክለወይኒ ፈታ እንላለን! ቅፅል በይ ምድረ ሉቅማፅ ሃሃ :)

ለማንኛውም መፅሃፈ ጥበብ ስድስተኛው ገፅ ላይ ያለውን ምክር ነግሬህ ላምልጥ ..

«ልጄ ሆይ ... ዝም ብለህ አትማረር፣ በሆነ ባልሆነው አታለቃቅስ ... ጠጉርህን አትንጭ፣ ላይፍ ኢዝ ቱ ሾርት ሞር ዛን ዩር ኢማጂኔሽን!
ፈታ በል ዩ አር ናት ካህን ፣ ዩ አር ናት ኤንጅል ፣ አንተ ጋር የሌለን ቅድስና ከሌላው አትጠብቅ፣ በጓዳህ ምታወራውን በአደባባይ ሲነግሩህ ቫንዳም ቫንዳም አትጫወት፣ ተክለወይኒንም ተፋታው!
ማይ ዲር ሰን ... ራስህን በአቡነ ጳውሎስ ሂሳብ ነው እንዴ ምታየው? ታዲያ ዝም ብለህ ሰውን ሁሉ ምታወግዘው ምንሼ ነው? በኢንቦክስ የቺክ ፎቶ እያስላክ ማስተርቤት ስትጠበጥብ እንደምታድር እኔና ዙከርበርክ አናውቅም እንዴ? ጎግል ላይ "sex" የሚለውን ቃል ሰርች በማድረግ ከአለም አንደኛ የሆነ ማህበረሰብ አባል መሆንህን አታውቅም እንዴ? አታውቅም ወይ?
ታዲያ አንድ አዛውንት ላይ ምትፈነዳው ምናባህ ሆነህ ነው? በመብረቅ ልምታህን? ኤሊኖ የሚባለውን ድርቅ ልላክብህን? በሲኖትራክ ላስገጭህን? ልጄ ሆይ ተጋዳላይ ተክለወይኒን ተፋታው ብዬሃለሁ ተፋታው!»

ስድስተኛው ገፅ ለዘላለም ይኑር :)

Like
2
Search
Categories
Read More
Uncategorized
ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
 ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __ ትንሹ ልጅ እናቱን “ማሚ ለምን ታለቅሻለሽ?” ሲል ጠየቃት “ምክንያቱም...
By Dawitda 2017-11-17 07:15:51 0 0
Uncategorized
.me
About .ME Are you trying to find a way to take control of your online identity? Maybe trying to...
By Dawitda 2017-11-15 16:52:32 0 0
Uncategorized
እስፖርት ጀምረናል
እስፖርት ጀምረናል! «ዘውድአለም ታደሰ» ዛሬ ለምን እንደሁ እንጃ እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ስገላበጥ አላሁ አክበር አለ! ቢቸግረኝ...
By Zewdalem 2017-11-15 05:22:44 0 0
Uncategorized
Macaafa Qulqulluu!!
Ergaa jireenya dhugaa fi Amantii.
By T002 2017-11-15 04:43:20 0 0
Uncategorized
_ ጥሩነት ለራስ ነው:: __
ሥራ ፈላጊው ለሥራ ውድድር የቃል መጠይቅ ፈተና ለመውሰድ መስሪያ ቤት ላይ ተገኝቷል፡፡ ኮሪደር ላይ ሆኖ የፈተና ጊዜውን ሲጠባበቅ ሳለ የወዳደቁ ቁርጥራጭ...
By Seller 2017-11-25 09:01:10 0 0