ሰርጋቸው ደማቅ ስለነበር ለምን ይፋታሉ?
(አሌክስ አብርሃም)
እንዴት ናችሁ ጓዶች ….ከሰሞኑ የፍች ወሬ በርከት ብሎ ሰነበተ ፌስቡክ ላይ? … ይች ፌስቡክ መቸም ፍች ስትወድ በስመአብ !! እውነቴንኮ ነው ….እንትናና እንትና ተጋቡ የሚል ፖስት ያውም ሙሽራው ሱፍ ለብሶ ወገቡን ይዞ አንዴ እንደበረኛ ተወርውሮ ተኝቶ …አንዴ ፈረስ ላይ ነብስና ስጋው እየተሟገተ ፊቱ ‹‹አቫተር ›› መስሎ …. የተነሳውን ፎቶ ሁሉ ለጥፎ ሶስት ላይክና አራት ኮሜንት ብቻ ታያላችሁ ….‹‹ ተፋቱ ›› ሲባል ስምንት መቶ ላይክ አራት ሽ...