በአሜሪካ የአየር ላይ ትርዒት ተሳታፊዎች በከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ሆስፒታል ገቡ
በአሜሪካ ኮሎራዶ በተካሄደው የአየር ላይ ትርዒት ተመልካቾች መካከል በአካባቢው በነበረው ከባድ ሙቀት ምክንያት አንድ መቶ የሚሆኑት አስቸኳይ ህክምና ሲፈልጉ አስር የሚሆኑት ደግሞ ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡
ትላንት ቅዳሜ በተጀመረውና ዛሬም በሚቀጥለው “ ፓይክስ ፒክ ሪጅናል ኤር ሾው” በመባል የሚታወቀው ይህ ትርዒት በታዋቂው የዩናይትድ ስቴትስ የባህር ኃይል “ ሰማያዊ መላእክት” በሚል ስም የሚታወቁት የበረራ ኤግዚቢሽን ቡድን ትርኢት የሚያሳዩበት እና የተለያዩ...