የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር በዋሽንግተን ስለ ጋዛና ሊባኖስ ይመክራሉ
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በጋዛ ጦርነት እና ግጭቱ እንዳይስፋፋ ስጋት ባሳደረው በሊባኖስ ድንበር በኩል ባለው የተኩስ ልውውጥ ጉዳይ ለመወያየት ዛሬ እሁድ ወደ ዋሽንግተን መጥተዋል።
የጋዛ ጦርነት ከጀመረበት ከስምንት ወራት በፊት አንስቶ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ለማድረግ በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላ ከእስራኤል ጋር ተኩስ እየተለዋወጠ ነው።
ጋላንት እስራኤል በጋዛ፣ ሊባኖስ እና ሌሎች አካባቢዎች ርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቷን በሰጡት መግለጫ...