Recent Updates
-
የተቀነጨበውን አንብበው እስኪ
• • • • •
". . . መቼም ዋናው ፍቅር ነው እንዳትለኝ! ሃ ሃ ሃ ተው አታስቀኝ! ጀለሴ የፍቅር concept ሰመመን መጽሃፍ ላይ Save ተደርጎልሃል፤ ሂድና አንብበው፤ ያውም ካገኘኸው፡፡ . . . የድሮ ሰው ፍቅር ይይዘው ነበር አሉ፡፡ የዱሮ ሰው የፍቅር ደብዳቤ ይጽፍ ነበር አሉ፡፡ የደጉ ዘመን ሰው አፈቀርኩ ብሎ ይከሳ ይመነምን ነበር አሉ፡፡ የዱሮ ወጣት ፎንቃ ጠልፎት የአስቴር አወቀን ካሴት እያዳመጠ ስቅስቅ ብሎ ያለቅስ ነበር አሉ፡፡"
✿ ✿ ✿
" . . . ባል፣ ጓደኛ፣ መልክ፣ ወጣትነት፣ ፈገግታ፣ ወግ፣ አመል፣ Femininity፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ሰላም፣ ፈላጊ፣ ለካፊ፣ አሽኮርማሚ፣ ሞካሪ፣ አፍቃሪ ካጡ፤ ተናዳፊ ጊንጥ የመሰሉ ብስጩ ፌሚኒስቶች ጋራ ገጠመች፡፡ የግሩፓቸው አባል ሆነች፡፡ ወንድ የባሰ ጠላች!"
✿ ✿ ✿
" . . . የዘውድ አገዛዝ፤ የደርግ ፋሺዝም፣ መደራጀት፣ ዴሞክራሲያ፣ መሥዋዕትነት፣ጆሊ-ጃኪዝም፣ ትጥቅ ትግል፣ ስር-ነቀል ለውጥ፣ ላብ አደር፣ ኢምፔሪያሊዝም፣ መሣፍንታዊው ስርዐት፣ ጭሰኛ፣ ንቅናቄ፣ ሠፊው ሕዝብ፣ ቅራኔ፣ ሃይሌ ፊዳ፣ መደብ፣ ዴሞክራሲያ፣ እድገት በኀብረት፣ መኢሶን፣ ሰርጎ-ገብ፣ አፈና፣ ነጭ ሽብር. . . የሚሉ ቃላቶችና ሃረጎች አእምሮው ላይ የሚመላለሱበት ጎረምሳ ዓይን፡፡ በህቡዕ የተደራጀ፣ በሴል የተዋቀረ፣ በህቡዕ በራሪ-ወረቀት የበተነ፣ የከለላ ሽፋን የሰጠ፤ ምናልባትም ከሴሉ አመራር በወረደለት ትዕዛዝ መሰረት በፋሺስቱ ስርዓት አገልጋዮች ላይ የግድያ እርምጃን የፈጸመ ቆራጥ አብዮታዊ ወጣት ዓይን፡፡"
✿ ✿ ✿
" . . . ደሞዝ የማይበቃቸው፤ ኑሮ ያካለባቸው አራት የኢቲቪና የአዲስ ዘመን ጋዜጠኞች ዳጎስ ያለ ውሎ አበል ተከፍሏቸው ይመጡና ነገርየውን እንደ ትልቅ ልማታዊ ዜና አካብደው ይዘግቡታል፡፡ መጨረሻ ላይ 47 ገጽ የሚሞላው Evaluation Report በExternal Consultant ተረቅቆ፤ “በዚህ ቦኖ መሰራት ሳቢያ ሆዱን የሚያመው አበሻ በ16% ቀነሰ፤ ሴቶች ታጥበው ቀሉ፤ ወደ ጅረት ወርደው ውሃ የሚቀዱበት ሰዓት ስላጠረላቸው ጤና ጣብያ ሄደው መውለድ ጀመሩ፤ ህጻናት ወፈሩ፤ Climate Changeን ለመከላከል በተዘዋዋሪ ተጽእኖ ፈጠረ . . .”ምናምን የሚል ጆካ ሪፖርት ተጽፎ፤ ሴቶችና ህጻናት ውሃ ጠጥተው ፈገግ ሲሉ የተነሱት ፎቶ ተጨምሮበት ለፈረንጅ ይላካል፡፡"
✿ ✿ ✿
". . . ህምም . . . ‘እሺ አይለውም’"0 Comments 0 SharesPlease log in to like, share and comment! -
-
More Stories