አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 19 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው አስትሮ ፊዚስት ዶክተር ለገሰ ወትሮ በ67 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ዶክተር ለገሰ በቀድሞ አጠራር በአሩሲ ክፍለ ሀገር ስሬ ወረዳ በ1942 ዓ.ም ነበር የተወለዱት፡፡
የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ከቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩንቨርሲቲ ያገኙት ዶክተር ለገሰ፥ ከአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፊዚክስ ትምህርት አግኝተዋል፡፡
ከሼፊልድ ዩናይት በድጋሚ በፊዚክስ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፥ ሶስተኛ ዲግሪያቸውን ከኮሎምቢያ ስቴት ዩንቨርሲቲ በአስትሮ ፊዚክስ አግኝተዋል፡፡
በንፋስ ስልክ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለአራት ዓመታት ያስተማሩት ዶክተር ለገሰ፥ ለ40 ዓመታት ያህል በመምህርነትና በተመራማሪነት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ አገልግለዋል፡፡
ዶክተር ለገሰ ወትሮ በአስትሮ ፊዚክስ ምርምር የሚታወቁ እና አዳዲስ ጽንሰ ሃሳቦችን ያበረከቱ ታላቅ ሰው ነበሩ ብሏል አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ በመግለጫው፡፡
በተወለዱ በ67 ዓመታቸው ያረፉት ዶ/ር ለገሰ የአንድ ወንድና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡
የዶ/ር ለገሰ ወትሮ ስርዓተ ቀብር ነገ ሚያዚያ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በጴጥሮስ መካነ መቃብር እንደሚፈፀም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

0 Comments
0 Shares