አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሩዋንዳ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምስራቃዊ ግዛት በሩዋማጋና የሚገኘውን ኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ሞዴል መንደሩ በሀገሪቱ በገጠራማ ስፍራ የሚገኙ አነስተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች በአንድ ላይ በማስፈር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ተናግረዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ በ2008 የተጀመረው የኢንቴቤ የተቀናጀ ሞዴል መንደር ልማት ከ2009 ጀምሮ ነዋሪዎችን ማስተናገድ ጀምሯል፤ በአሁኑ ወቅትም ከ204 በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦችን ይዟል።
መንደሮቹ የተለያዩ ማህበረሰቦች በግብርና እና ሌሎች መስኮች በመስራት በጋራ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
በእነዚህ መንደሮች የሚኖሩ ሰዎች የትምህርት፣ የውሃ እና ፅዳጅ፣ የጤና፣ የኤሌክትሪክ እና ሌሎች አገልግሎቶችን በጋራ ያገኛሉ።
የሀገሪቱ መንግስት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 70 በመቶ የገጠሩን ህዝብ በእነዚህ ሞዴል መንደሮች ለማስፈር አቅዷል፡፡

0 Comments
0 Shares