• አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል።

    ድጋፉ በተለይ ለአልሚ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ 277 ሺህ ህጻናት እና ሴቶች አስቸኳይ እርዳታዎችን ለመስጠት ያገዛል ተብሏል።

    በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ላ ይፋን በእርዳታ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት፥ ቻይና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር በመሆኗ የተቻላትን ድጋፍ እያደረገች ነው፡፡

    “በማደግ ላይ የምንገኝ ሀገር ብንሆንም በአለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ ማደረግ አለብን” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡

    የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን በተመለከተ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት አምባሳደሩ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቀነስ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል።

    በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጆን አይሊፍ በበኩላቸው፥ ቻይና በአንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ኢትዮጵውያን እያደረገች ያለችውን አስተዋጽኦ አድንቀው፥ በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ከ50 አመታት ወዲህ የከፋ መሆኑን ጠቁመዋል።

    የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ አቅም ደርቁን ለመቋቋም እና ለዜጎቹ በወቅቱ አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ መሆኑን ያደነቁት ዳይሬክተሩ፥ አለም አቀፉ ማህበረሰብም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

    በዚህ ወቅት ቻይና ያደረገችው እርዳታንም በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡

    የኢትዮጵያ መንግስት የአልሚ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ቁጥርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን የአለም ምግብ ፕሮገራም በደረ ገጹ የጠቀሰ ሲሆን፥ 40 በመቶ ከሚሆኑ ህጻናት ውስጥ 9 በመቶው የመቀጨር ችግር ያሉባቸው በመሆኑ ችግሩን ለመቀነስ ብርቱ ጥረት እንደሚጠይቅ ጠቁሟል፡፡

    ምንጭ ፦http://www.vanguardngr.com
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉ በተለይ ለአልሚ ምግብ እጥረት ለተጋለጡ 277 ሺህ ህጻናት እና ሴቶች አስቸኳይ እርዳታዎችን ለመስጠት ያገዛል ተብሏል። በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ላ ይፋን በእርዳታ ርክክቡ ወቅት እንዳሉት፥ ቻይና የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር በመሆኗ የተቻላትን ድጋፍ እያደረገች ነው፡፡ “በማደግ ላይ የምንገኝ ሀገር ብንሆንም በአለም ምግብ ድርጅት አማካኝነት ለሌሎች ሀገራት ድጋፍ ማደረግ አለብን” ብለዋል አምባሳደሩ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ዜጎችን በተመለከተ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት አምባሳደሩ፥ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትለውን የተፈጥሮ አደጋ ለመቀነስ በቁርጠኝነት መስራት ይኖርበታል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ጆን አይሊፍ በበኩላቸው፥ ቻይና በአንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ሳቢያ ለተጎዱ ኢትዮጵውያን እያደረገች ያለችውን አስተዋጽኦ አድንቀው፥ በአሁኑ ወቅት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ከ50 አመታት ወዲህ የከፋ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በራሱ አቅም ደርቁን ለመቋቋም እና ለዜጎቹ በወቅቱ አስቸኳይ እርዳታ እየሰጠ መሆኑን ያደነቁት ዳይሬክተሩ፥ አለም አቀፉ ማህበረሰብም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በዚህ ወቅት ቻይና ያደረገችው እርዳታንም በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የአልሚ ምግብ እጥረት ያለባቸው ህጻናት ቁጥርን በመቀነስ ረገድ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን የአለም ምግብ ፕሮገራም በደረ ገጹ የጠቀሰ ሲሆን፥ 40 በመቶ ከሚሆኑ ህጻናት ውስጥ 9 በመቶው የመቀጨር ችግር ያሉባቸው በመሆኑ ችግሩን ለመቀነስ ብርቱ ጥረት እንደሚጠይቅ ጠቁሟል፡፡ ምንጭ ፦http://www.vanguardngr.com
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ቻይና በኢትዮጵያ ለድርቅ ተጎጂዎች የሚውል 8 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የሰብአዊ ደጋፍ አደረገች
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና መንግስት የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት የሚያደርገውን ድጋፍ ለማጠናከር 8 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ግምት ያለው የሰብአዊ ድጋፍ...
    0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • 0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ።

    የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል።

    በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል።

    ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

    የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል።

    ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል።

    በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል።

    ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ።

    ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት።

    ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል።

    የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል።

    በስላባት ማናዬ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ከመጋቢት 21 ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ በሀገሪቱ የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸው የውጭ ሀገራት ዜጎች ለቀው እንዲወጡ ያወጀው የ90 ቀናት የምህረት አዋጅ መተግበር ከጀመረ ዛሬ 26 ቀናት ሆኖታል። በዚህ የምህረት አዋጅ ውስጥም የኢፌዴሪ መንግስት ኢዮጵያውያን እንግልት ሳይደርስባቸው በ90 ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ፥ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የሚከታተል ብሄራዊ ኮሚቴ አቋቁሟል። ዛሬም ይሄው ኮሚቴ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበዬሁ ሰብሳቢነት የእስካሁኑን እንቅስቃሴ ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ በስብሰባው ከሳዑዲ ዓረቢያ የሚመጡ ዜጎችን ለመቀበል የፌደራል ተቋማትና ክልሎች በትብብር እንዲሰሩ ተወስኗል። ከዚህ ባለፈም ክልሎች የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን እንደገና እንዲቋቋሙ እና ከክልል ከተሞች እስከ ወረዳ ከተሞች ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲያደርጉ የቀረበው ሀሳብም ፀድቋል። በዚህም አዲስ አበባ ቦሌ አየር መንገድ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ገቢወች እና ጉምሩክ፣ ፖሊስ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ አጠናክረው በመቀጠል እንግልት እንዳይደርስባቸው መስራት እንደሚገባቸውም ኮሚቴው አጽንኦት ሰጥቷል። ክልሎች ደግሞ ወደእነርሱ ለሚመጡ ዜጎች ትራንስፖርትን እንዲያመቻቹ ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል አቶ መለስ። ከሳዑዲ ዓረቢያ የምህረት አዋጁን ተጠቅመው ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ስራቸውን ትተው እንደመመለሳቸው መጠንም፥ አሁን ላይ እየተተገበረ ባለው የወጣቶች የስራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ነው ያሉት። ቃል አቀባዩ ሪያድ ያወጣችው አዋጅ አሁን ላይ 26 ቀናት እንደሆኑት ጠቅሰው፥ አዋጁ የሚመለከታቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከፍተኛ ከመሆኑ አኳያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባም አንስተዋል። የተመላሾች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፥ ካለፈው ቅዳሜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በየቀኑ በአማካይ 400 ሰዎች እየገቡ መሆኑን ጠቁመዋል። በስላባት ማናዬ
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ከሳዑዲ ተመላሾች ችግር እንዳያጋጥማቸው የፌደራል ተቋማት እና የክልል መንግስታት በቅንጅት እንዲሰሩ መመሪያ ተላለፈ
    አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 17 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፍቃድ የሌላቸውን የውጭ ሀገራት ዜጎች በዘጠና ቀናት ውስጥ እንዲወጡ ካዘዛ በኋላ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ችግር እን...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳሰበ።

    በዛሬው እለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከኤጀንሲዉ ጋር በመተባበር በፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ላይ የሚመክር ጉባኤ አካሂዷል።

    የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፥ ትክክለኛ የምዘና ስርዓት በመተግበር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተቋሙ እየሰራ ነው።

    ሆኖም በተማሪዎች ዘንድ በስፋት የሚስተዋለውን የኩረጃ ተግባር ለማስቀረት፥ ወላጆች፣ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

    የጉባኤዉ ተሳታፊዎቸ በበኩላቸው ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ፥ ጥብቅ የፈተና ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳሰበ። በዛሬው እለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከኤጀንሲዉ ጋር በመተባበር በፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ላይ የሚመክር ጉባኤ አካሂዷል። የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ገብረእግዚአብሄር በውይይቱ ወቅት እንደተናገሩት፥ ትክክለኛ የምዘና ስርዓት በመተግበር የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተቋሙ እየሰራ ነው። ሆኖም በተማሪዎች ዘንድ በስፋት የሚስተዋለውን የኩረጃ ተግባር ለማስቀረት፥ ወላጆች፣ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል። የጉባኤዉ ተሳታፊዎቸ በበኩላቸው ከታችኛው የክፍል ደረጃ ጀምሮ፥ ጥብቅ የፈተና ስርዓትን ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል፡፡
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኩረጃን የሚጸየፍ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም የህብረተሰበ ክፍል የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አሳሰበ። በዛሬው እለት ፋና ብሮድካስቲንግ ኮ...
    0 Comments 0 Shares
  • አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚገኙ ግለሰቦች ተናገሩ።

    አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት፥ ህገወጥ ዓሳ አስጋሪዎቹ ባልተገባ ሁኔታ ዓሳዎችን እንቁላል ሳይጥሉ ማስገራቸው የሀይቁ የዓሳ ሃብት እንዲቀንስ አድርጎታል።

    የማጥመድ ስራውም ማንኛውንም አሳ ለማጥመድ ከውጭ ሀገር በመጣ ማጥመጃ እያከናወኑ መሆኑም ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል።

    ይህ ደግሞ ትናንሽ አሳዎችን ከሀይቁ በማውጣት ተተኪ እንዳይኖር ያደርገዋል ነው የተባለው።

    የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሀይቁ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ እና ህገወጥ አስጋሪዎች፥ የሚያሰግሩበትን መንገድ እንዲያስተካክሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

    ዓሳ የሚያሰግሩበት ማስገሪያ በተቀመጠለት ደረጃ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ ሲሆን፥ እርምጃ ለመውሰድም ታቅዷል።

    ሀይቁ የኦሮሚያ ክፍል አዋሳኝ በምዕራብ አርሲ ዞን ከ300 በላይ ወጣቶች በማህበር የስራ እድል ተፈጥሮላቸው፥ በቢሻን ጉራቻ ሐይቅ ዳርቻ ተሰማርተው እየሰሩ ሲሆን፥ በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገሩም በእነሱ በኩልም እየተከናወነ ነው።

    የዞኑ የእንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ ሃላፊ ዶክተር አብዱላሂ ቤካ፥ የወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገር ችግር አምነው፥ ከፌደራልና ከደቡብ ክልል የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል።
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚገኙ ግለሰቦች ተናገሩ። አስተያየታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የሰጡ አስተያየት ሰጪዎች እንደተናገሩት፥ ህገወጥ ዓሳ አስጋሪዎቹ ባልተገባ ሁኔታ ዓሳዎችን እንቁላል ሳይጥሉ ማስገራቸው የሀይቁ የዓሳ ሃብት እንዲቀንስ አድርጎታል። የማጥመድ ስራውም ማንኛውንም አሳ ለማጥመድ ከውጭ ሀገር በመጣ ማጥመጃ እያከናወኑ መሆኑም ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተነግሯል። ይህ ደግሞ ትናንሽ አሳዎችን ከሀይቁ በማውጣት ተተኪ እንዳይኖር ያደርገዋል ነው የተባለው። የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ በሀይቁ ላይ የተሰማሩ ህጋዊ እና ህገወጥ አስጋሪዎች፥ የሚያሰግሩበትን መንገድ እንዲያስተካክሉ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል። ዓሳ የሚያሰግሩበት ማስገሪያ በተቀመጠለት ደረጃ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ ሲሆን፥ እርምጃ ለመውሰድም ታቅዷል። ሀይቁ የኦሮሚያ ክፍል አዋሳኝ በምዕራብ አርሲ ዞን ከ300 በላይ ወጣቶች በማህበር የስራ እድል ተፈጥሮላቸው፥ በቢሻን ጉራቻ ሐይቅ ዳርቻ ተሰማርተው እየሰሩ ሲሆን፥ በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገሩም በእነሱ በኩልም እየተከናወነ ነው። የዞኑ የእንስሳትና አሳ ሃብት መምሪያ ሃላፊ ዶክተር አብዱላሂ ቤካ፥ የወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ አሳ የማስገር ችግር አምነው፥ ከፌደራልና ከደቡብ ክልል የሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እርምጃ እየወሰድን ነው ብለዋል።
    WWW.FANABC.COM
    FBC - ህገወጥ አስጋሪዎች በሀዋሳ ሀይቅ የዓሳ ሀብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እየፈጠሩ ነው
    አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ሀይቅ ህገወጥ አሳ አስጋሪዎች ተገቢ ባልሆነ መረብ በማስገር በሀይቁ ዓሳ ሀብት ላይ ተጽእኖ እየፈጠሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎችና በሀይቁ ዙሪያ አገልግሎት በመስጠት እየተጠቀሙ የሚ...
    0 Comments 0 Shares