• ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን የሚያመርተው የጣሊያኑ ቬሮና ፔር ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ

    ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን የሚያመርተው የጣሊያኑ ቬሮና ፔር ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ፡፡“ኩባንያው በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ የሚዘጋጁ አውደ ርዕዮችን አብረን እናሰናዳ የሚል ጥያቄ ለአዲሰ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አቅርቧል፤ ሥራው ለኢትዮጵያ የተሻለ ጥቅም ከሰጠ እንቅበለዋለን፤ ካልሆነ ግን ይቀራል ለማለት በጉዳዩ ላይ እየተመከረ ነው” ሲሉ የንግድ ትርዒት ኃላፊው አቶ ጋሻው አባተ ነግረውናል፡፡

    ቬሮና ፔር በመጪው ግንቦት 3 በሚጀምረውና ግንቦት 7 በሚጠናቀቀው 10ኛው የግብርና እና ምግብ አለም አቀፍ ኤግዚብሽን ላይ ይካፈላል ተብሏል፡፡በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በመሰል ሥራ የተሰማራው የግብፁ ሹማን ኩባንያም ምርትና አገልግሎቱን ይዞ ይመጣል፤ 11 የአልጄሪያ ኩባንያዎችም ተካፋይ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

    ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ በግብርናና በምግብ ሥራ የተሰማሩ 30 የቻይና ኩባንያዎችም በአውደ ርዕዩ ይታደማሉ፡፡እንዲህ ያሉ አለም አቀፍ አውደ ርዕዮች በመሰል ሥራ ላይ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ልምድ በማካፈል ጥቅማቸው የጐላ ነው ያሉት አቶ ጋሻው 30 ኢትዮጵያዊያን ኩባንያዎችም ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ይታደሙበታል የልምድ ልውውጥም ይካሄድበታል ሲሉ ነግረውናል፡፡

    ሸገር
    ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን የሚያመርተው የጣሊያኑ ቬሮና ፔር ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ ትራክተሮችንና የእርሻ መሣሪያዎችን የሚያመርተው የጣሊያኑ ቬሮና ፔር ኩባንያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር መሥራት እፈልጋለሁ አለ፡፡“ኩባንያው በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ የሚዘጋጁ አውደ ርዕዮችን አብረን እናሰናዳ የሚል ጥያቄ ለአዲሰ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አቅርቧል፤ ሥራው ለኢትዮጵያ የተሻለ ጥቅም ከሰጠ እንቅበለዋለን፤ ካልሆነ ግን ይቀራል ለማለት በጉዳዩ ላይ እየተመከረ ነው” ሲሉ የንግድ ትርዒት ኃላፊው አቶ ጋሻው አባተ ነግረውናል፡፡ ቬሮና ፔር በመጪው ግንቦት 3 በሚጀምረውና ግንቦት 7 በሚጠናቀቀው 10ኛው የግብርና እና ምግብ አለም አቀፍ ኤግዚብሽን ላይ ይካፈላል ተብሏል፡፡በዚህ አውደ ርዕይ ላይ በመሰል ሥራ የተሰማራው የግብፁ ሹማን ኩባንያም ምርትና አገልግሎቱን ይዞ ይመጣል፤ 11 የአልጄሪያ ኩባንያዎችም ተካፋይ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ ከአፍሪካ ውጭ ደግሞ በግብርናና በምግብ ሥራ የተሰማሩ 30 የቻይና ኩባንያዎችም በአውደ ርዕዩ ይታደማሉ፡፡እንዲህ ያሉ አለም አቀፍ አውደ ርዕዮች በመሰል ሥራ ላይ ላሉ ኢትዮጵያዊያን ልምድ በማካፈል ጥቅማቸው የጐላ ነው ያሉት አቶ ጋሻው 30 ኢትዮጵያዊያን ኩባንያዎችም ምርትና አገልግሎታቸውን ይዘው ይታደሙበታል የልምድ ልውውጥም ይካሄድበታል ሲሉ ነግረውናል፡፡ ሸገር
    0 Comments 0 Shares
  • ሻይን ተንቀሳቃሽ የደረቅ መኪና እጥበት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቅርቡ ወደ መኪና እጥበት ቢዝነስ የገባ ኢንተርፕራይዝ ሲሆን፣ መኪናን በግፊት ኃይል በሚሠሩ የመኪና ማጠቢያ ፕላስቲክ ማሽኖች ያለ ፈሳሽ ወይም በደረቅ የመወልወል አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 106 የሚሆኑ ወጣቶች ተቀጥረው የሚሠሩበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በሦስት ክፍለ ከተሞች በዋነኛነት በንግድ ማዕከል ሕንፃዎች እየሠሩ ነው፡፡ ስለ ማኅበሩ እንቅስቃሴ ምሕረተሥላሴ መኰንን የማኅበሩን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ይማም አነጋግራዋለች፡፡

    ሪፖርተር፡- ማኅበሩ ስለሚሰጠው የደረቅ መኪና እጥበት አገልግሎት ብታብራራልን?

    አቶ ጥላሁን፡- የደረቅ መኪና እጥበት መሬት ላይ ውኃ ሳይፈስ መኪናን በማራስ ብቻ የሚደረግ የእጥበት ዘዴ ነው፡፡ አገልግሎቱ በተለያዩ አገሮች ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ በአፍሪካ በደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያና በሌሎችም አገሮች ይሰጣል፡፡ ሐሳቡን ያመጣነው በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተን ላቫጆ ሥራ በጠየቅንበት ወቅት ነበር፡፡ የቦታ ችግር ስላለ በመንግሥት በኩል በተወሰነ ደረጃ ላቫጆ መስጠት የተከለከለበት ጊዜ አለ፡፡ ይህንን በማየት ኢንተርኔት ላይ ሌላ አማራጭ ፈለግን፡፡ የመኪና እጥበት ውጭ አገር በአዲስ ቴክኖሎጂ እንዴት እንደሚሠራ አየንና ጀመርን፡፡
    ሻይን ተንቀሳቃሽ የደረቅ መኪና እጥበት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቅርቡ ወደ መኪና እጥበት ቢዝነስ የገባ ኢንተርፕራይዝ ሲሆን፣ መኪናን በግፊት ኃይል በሚሠሩ የመኪና ማጠቢያ ፕላስቲክ ማሽኖች ያለ ፈሳሽ ወይም በደረቅ የመወልወል አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 106 የሚሆኑ ወጣቶች ተቀጥረው የሚሠሩበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በሦስት ክፍለ ከተሞች በዋነኛነት በንግድ ማዕከል ሕንፃዎች እየሠሩ ነው፡፡ ስለ ማኅበሩ እንቅስቃሴ ምሕረተሥላሴ መኰንን የማኅበሩን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ይማም አነጋግራዋለች፡፡ ሪፖርተር፡- ማኅበሩ ስለሚሰጠው የደረቅ መኪና እጥበት አገልግሎት ብታብራራልን? አቶ ጥላሁን፡- የደረቅ መኪና እጥበት መሬት ላይ ውኃ ሳይፈስ መኪናን በማራስ ብቻ የሚደረግ የእጥበት ዘዴ ነው፡፡ አገልግሎቱ በተለያዩ አገሮች ይሰጣል፡፡ ለምሳሌ በአፍሪካ በደቡብ አፍሪካ፣ በኬንያና በሌሎችም አገሮች ይሰጣል፡፡ ሐሳቡን ያመጣነው በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተን ላቫጆ ሥራ በጠየቅንበት ወቅት ነበር፡፡ የቦታ ችግር ስላለ በመንግሥት በኩል በተወሰነ ደረጃ ላቫጆ መስጠት የተከለከለበት ጊዜ አለ፡፡ ይህንን በማየት ኢንተርኔት ላይ ሌላ አማራጭ ፈለግን፡፡ የመኪና እጥበት ውጭ አገር በአዲስ ቴክኖሎጂ እንዴት እንደሚሠራ አየንና ጀመርን፡፡
    WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
    አዲሱ የደረቅ መኪና እጥበት
    ሻይን ተንቀሳቃሽ የደረቅ መኪና እጥበት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በቅርቡ ወደ መኪና እጥበት ቢዝነስ የገባ ኢንተርፕራይዝ ሲሆን፣ መኪናን በግፊት ኃይል በሚሠሩ የመኪና ማጠቢያ ፕላስቲክ ማሽኖች ያለ ፈሳሽ ወይም በደረቅ የመወልወል አገልግሎት ይሰጣል፡፡ 106 የሚሆኑ ወጣቶች ተቀጥረው የሚሠሩበት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በሦስት ክፍለ ከተሞች በዋነኛነት በንግድ ማዕከል ሕንፃዎች እየሠሩ ነው፡፡ ስለ ማኅበሩ እንቅስቃሴ ምሕረተሥላሴ መኰንን የማኅበሩን ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥላሁን ይማም አነጋግራዋለች፡፡   ሪፖርተር፡- ማኅበሩ ስለሚሰጠው የደረቅ መኪና እጥበት አገልግሎት ብታብራራልን?አቶ ጥላሁን፡- የደረቅ መኪና እጥበት መሬት ላይ ውኃ ሳይፈስ መኪናን
    0 Comments 0 Shares
  • የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ከ13 ዓመታት በኋላ ወባን ልታጠፋ ትችላለች ሲል፣ ስድስት የአፍሪካ አገሮች ደግሞ በሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚያጠፉት አስታውቋል፡፡

    እስከ 2012 ዓ.ም. ወባን ያጠፋሉ ተብለው የተቀመጡት አገሮች አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕቬርዴ፣ ኮሞሮስ፣ ደቡብ አፍሪካና ስዋዚላንድ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በ2022 ዓ.ም. ወባን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ተብሏል፡፡

    ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበረውን የዓለም ወባ ቀን ኢትዮጵያ ለ10ኛ ጊዜ ትላንት ያከበረች ሲሆን፣ ‹‹ወባን በጋራ ጨርሶ እናስወገድድ›› የሚለውን መሪ ቃል ከግምት በማስገባትም ወባን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ለማስወገድ እንዲቻል የተለያዩ ስልቶች ተግባራዊ እያደረገች መሆኑ ታውቋል፡፡

    በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ የወባ ኦፊሰር አቶ ደረጀ ድሉ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ እስካሁን ካካሄደቻቸው እንቅስቃሴዎች መካከል በአምስት ክልሎችና በአንድ የከተማ አስተዳደር በሚገኙና በተመረጡ 239 ወረዳዎች ውስጥ ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ወባን የማጥፋት ሥራ መከናወኑ ተጠቃሽ ነው፡፡
    የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ከ13 ዓመታት በኋላ ወባን ልታጠፋ ትችላለች ሲል፣ ስድስት የአፍሪካ አገሮች ደግሞ በሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚያጠፉት አስታውቋል፡፡ እስከ 2012 ዓ.ም. ወባን ያጠፋሉ ተብለው የተቀመጡት አገሮች አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕቬርዴ፣ ኮሞሮስ፣ ደቡብ አፍሪካና ስዋዚላንድ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በ2022 ዓ.ም. ወባን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ተብሏል፡፡ ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበረውን የዓለም ወባ ቀን ኢትዮጵያ ለ10ኛ ጊዜ ትላንት ያከበረች ሲሆን፣ ‹‹ወባን በጋራ ጨርሶ እናስወገድድ›› የሚለውን መሪ ቃል ከግምት በማስገባትም ወባን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ለማስወገድ እንዲቻል የተለያዩ ስልቶች ተግባራዊ እያደረገች መሆኑ ታውቋል፡፡ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከፍተኛ የወባ ኦፊሰር አቶ ደረጀ ድሉ እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ እስካሁን ካካሄደቻቸው እንቅስቃሴዎች መካከል በአምስት ክልሎችና በአንድ የከተማ አስተዳደር በሚገኙና በተመረጡ 239 ወረዳዎች ውስጥ ካለፈው መጋቢት ጀምሮ ወባን የማጥፋት ሥራ መከናወኑ ተጠቃሽ ነው፡፡
    WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
    ኢትዮጵያ ከ13 ዓመታት በኋላ ወባን ልታጠፋ ትችላለች
    ስድስት የአፍሪካ አገሮች ሦስት ዓመታት ይበቃቸዋል የዓለም ጤና ድርጅት ኢትዮጵያ ከ13 ዓመታት በኋላ ወባን ልታጠፋ ትችላለች ሲል፣ ስድስት የአፍሪካ አገሮች ደግሞ በሦስት ዓመታት ውስጥ እንደሚያጠፉት አስታውቋል፡፡እስከ 2012 ዓ.ም. ወባን ያጠፋሉ ተብለው የተቀመጡት አገሮች አልጄሪያ፣ ቦትስዋና፣ ኬፕቬርዴ፣ ኮሞሮስ፣ ደቡብ አፍሪካና ስዋዚላንድ ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ ደግሞ በ2022 ዓ.ም. ወባን ለማጥፋት ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ ላይ ትገኛለች ተብሏል፡፡ሚያዝያ 17 ቀን የሚከበረውን የዓለም ወባ ቀን ኢትዮጵያ ለ10ኛ ጊዜ ትላንት ያከበረች ሲሆን፣ ‹‹ወባን በጋራ ጨርሶ እናስወገድድ›› የሚለውን መሪ ቃል ከግምት በማስገባትም ወባን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ለማስወገድ እንዲቻል
    0 Comments 0 Shares
  • ብቁ ሐኪም ወይስ ጋዋን ለባሽ ማፍራት?

    21 Apr, 2017 By ምሕረት አስቻለው 0 Comments
    በሆስፒታሉ የተለያዩ ዋርዶች ላይ ከተገኙ በብዛት ወዲያ ወዲህ ሲሉ የሚመለከቱት መደበኛ ሐኪሞችን ሳይሆን በልምምድ ላይ ያሉትን ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ክሊኒካል አታችመንት (Clinical Attachment) ላይ ያሉ እንደ ሦስትና አራተኛ ዓመት ተማሪዎች በቡድን በቡድን ሆነው በዋና ሐኪም እየተመሩ ታማሚዎችን ሲጎበኙ ይስተዋላል፡፡ ይህ በየካቲት 12 ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን እንደ ጥቁር አንበሳ፣ ጳውሎስ፣ ዘውዲቱና ሌሎችም የመንግሥት ሆስፒታሎች የሚታይ ነው፡፡

    አገሪቱ ያለባትን የሐኪም እጥረት ችግር ለመፍታት ባለፉት የተወሰኑ ዓመታት የሕክምና ተማሪዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር መንግሥት እንደ መፍትሔ የወሰደው ዕርምጃ ነው፡፡ በርግጥ ይህ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ተማሪዎች ቁጥር መጨመር የታገዘ ዕርምጃም ነው፡፡ በዚህም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የመንግሥት ሆስፒታሎች እየተስፋፉና ማስተማሪያ ሆስፒታሎች (Teaching Hospitals) እየሆኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል የሕክምና ትምህርት መስጠት በግሉ ዘርፍም እየተስፋፋ መሆኑ የሕክምና ባለሙያዎችን ቁጥር የመጨመር ዕርምጃውን የሚያጠናክር ሌላው ነገር ነው፡፡

    የሕክምና ተማሪዎች ቁጥር መጨመር፣ እንዲሁም የሕክምና ትምህርት በመንግሥት በግሉም ዘርፍ መሰጠት አዎንታዊና ይበል የሚባል ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የዚህ አጠቃላይ ውጤት ወይም ተፅዕኖ መልካም ይሆን ዘንድ ሊታዩ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የሕክምና ተማሪዎች የተግባር ሥልጠና ወይም ልምምድ ከቁጥራቸው መብዛትና ልምምድ ከሚያደርጉባቸው ሆስፒታሎች አቅም ውስንነት አንፃር እንዴት ይታያል? በተደጋጋሚ በሕክምና ተማሪዎችና ለማጅ ሐኪሞች ከመጎብኘት አንፃር የበሽተኞች ድካምና ጫናስ? የሚሉና መሰል ጥያቄዎችም ይነሳሉ፡፡
    ...
    ብቁ ሐኪም ወይስ ጋዋን ለባሽ ማፍራት? 21 Apr, 2017 By ምሕረት አስቻለው 0 Comments በሆስፒታሉ የተለያዩ ዋርዶች ላይ ከተገኙ በብዛት ወዲያ ወዲህ ሲሉ የሚመለከቱት መደበኛ ሐኪሞችን ሳይሆን በልምምድ ላይ ያሉትን ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ክሊኒካል አታችመንት (Clinical Attachment) ላይ ያሉ እንደ ሦስትና አራተኛ ዓመት ተማሪዎች በቡድን በቡድን ሆነው በዋና ሐኪም እየተመሩ ታማሚዎችን ሲጎበኙ ይስተዋላል፡፡ ይህ በየካቲት 12 ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን እንደ ጥቁር አንበሳ፣ ጳውሎስ፣ ዘውዲቱና ሌሎችም የመንግሥት ሆስፒታሎች የሚታይ ነው፡፡ አገሪቱ ያለባትን የሐኪም እጥረት ችግር ለመፍታት ባለፉት የተወሰኑ ዓመታት የሕክምና ተማሪዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር መንግሥት እንደ መፍትሔ የወሰደው ዕርምጃ ነው፡፡ በርግጥ ይህ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ተማሪዎች ቁጥር መጨመር የታገዘ ዕርምጃም ነው፡፡ በዚህም ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የመንግሥት ሆስፒታሎች እየተስፋፉና ማስተማሪያ ሆስፒታሎች (Teaching Hospitals) እየሆኑ ነው፡፡ በሌላ በኩል የሕክምና ትምህርት መስጠት በግሉ ዘርፍም እየተስፋፋ መሆኑ የሕክምና ባለሙያዎችን ቁጥር የመጨመር ዕርምጃውን የሚያጠናክር ሌላው ነገር ነው፡፡ የሕክምና ተማሪዎች ቁጥር መጨመር፣ እንዲሁም የሕክምና ትምህርት በመንግሥት በግሉም ዘርፍ መሰጠት አዎንታዊና ይበል የሚባል ነገር ነው፡፡ ነገር ግን የዚህ አጠቃላይ ውጤት ወይም ተፅዕኖ መልካም ይሆን ዘንድ ሊታዩ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ ከዚህ አንፃር የሕክምና ተማሪዎች የተግባር ሥልጠና ወይም ልምምድ ከቁጥራቸው መብዛትና ልምምድ ከሚያደርጉባቸው ሆስፒታሎች አቅም ውስንነት አንፃር እንዴት ይታያል? በተደጋጋሚ በሕክምና ተማሪዎችና ለማጅ ሐኪሞች ከመጎብኘት አንፃር የበሽተኞች ድካምና ጫናስ? የሚሉና መሰል ጥያቄዎችም ይነሳሉ፡፡ ...
    WWW.ETHIOPIANREPORTER.COM
    ብቁ ሐኪም ወይስ ጋዋን ለባሽ ማፍራት?
    በሆስፒታሉ የተለያዩ ዋርዶች ላይ ከተገኙ በብዛት ወዲያ ወዲህ ሲሉ የሚመለከቱት መደበኛ ሐኪሞችን ሳይሆን በልምምድ ላይ ያሉትን ነው፡፡ ከዚህም ሌላ ክሊኒካል አታችመንት (Clinical Attachment) ላይ ያሉ እንደ ሦስትና አራተኛ ዓመት ተማሪዎች በቡድን በቡድን ሆነው በዋና ሐኪም እየተመሩ ታማሚዎችን ሲጎበኙ ይስተዋላል፡፡ ይህ በየካቲት 12 ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን እንደ ጥቁር አንበሳ፣ ጳውሎስ፣ ዘውዲቱና ሌሎችም የመንግሥት ሆስፒታሎች የሚታይ ነው፡፡  አገሪቱ ያለባትን የሐኪም እጥረት ችግር ለመፍታት ባለፉት የተወሰኑ ዓመታት የሕክምና ተማሪዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር መንግሥት  እንደ መፍትሔ የወሰደው ዕርምጃ ነው፡፡ በርግጥ ይህ በከፍተኛ
    0 Comments 0 Shares
  • ‹‹ራሴን በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሀል ላይ ያለ ድልድይ አድርጌ ነው የምወስደው››

    ገጣሚና ጸሐፊ ለምን ሲሳይ

    ትውልደ ኢትዮጵያ ብሪታንያዊው ለምን ሲሳይ ዕውቅ ገጣሚና ጸሐፊ ነው፡፡ በተለያዩ ጥበብ ተኮር ተቋማት እየሠራ ይገኛል፡፡ በሳውዝ ባንክ ማዕከል ተባባሪ አርቲስት፣ በሌተር ቦክስ ክለብ ድጋፍ ሰጪ፣ የቺልድረንስ ሪዲንግ ፈንድ አምባሳደር ሲሆን የክብር ዶክትሬት (ዶክተር ኦፍ ሌተርስ) ተሰጥቶታል፡፡ ለለንደን ኦሊምፒክ ግጥም የደረሰ፣ የበርካታ ተለጣጣቂ መጻሕፍት፣ መጣጥፎች፣ ሪከርዶች ወዘተ ጸሐፊ ነው፡፡ ከሰኔ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆኖ ለሰባት ዓመታት አገልግሎት ተመርጧል፡፡ ኢትዮጵያ ተወልዶ ብሪታኒያ በጉዲፈቻ ያደገው ለምን ሕይወቱን ከአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል ዓለማየሁ ጋር ያገናኘዋል፡፡ የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ አፅም ወደ አገሩ እንዲመለስ ምኞቱ መሆኑንም ይናገራል፡፡ መሰንበቻውን ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ያለውን ለምን ሲሳይን ዳዊት እንደሻው ስለ ዐውደ ሕይወቱ አውግቶታል፡፡

    ሪፖርተር፡- በቅድሚያ ስለነበረህ የአንድ ሳምንት ቆይታ እስኪ ግለጽልን፡፡

    ለምን፡- እስካሁን የነበረኝ ቆይታ በጣም አዝናኝና ፍሬያማ ነበር፡፡ ከብዙ ሰዎች ጋር የመገናኘቱን ዕድል አግኝቻለሁ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከሪታ ፓንክረስት ጋር የመገናኘቱን ክብር አግኝቻለሁ፡፡ በተጨማሪም አሉላ ፓንክረስት ጋር ተገናኝቼ ከማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት እንዴት የውጭ የትምህርት ዕድል ለኢትዮጵያውያን ማመቻቸት እንደምንችል መክረናል፡፡

    እሱ ብቻ አይደለም ከብሪትሽ ካውንስል አዲስ ዳይሬክተር ፒተር ብራውን ጋር ተገናኝተናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከአዲስ አበባና ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ከመጡ ምሁራን ጋርም የመገናኘቱን ዕድልም አግኝቼ ከውጭ የትምህርት ዕድሉ ጋር በተያያዘ እንዴት የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ከማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጋር እንዴት መሥራት እንደሚችሉ ተነጋግረናል፡፡ እንግዲህ እኔ ራሴን በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሀል ላይ ያለ ድልድይ አድርጌ ነው የምወስደው፡፡ አሁን አሁን ጊዜዎች ባለፉ ዕድሜያችንም በገፋ ቁጥር እኔ እዚህ ያለሁት ለምክንያት ነው የሚለው ሐሳብ ሁሌም ይመጣብኛል፡፡ ይኼ ደግሞ ለእኔ መባረክ ነው፡፡ በዚች ታላቅ አገር ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነትን ባገኘሁ ቁጥር በታወኩ ቁጥር ለእኔ ይሄ ትልቅ ነገር ነው፤ ስጦታ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን ከኢትዮጵያ መፈጠር ትልቅ ስጦታ ነው፡፡

    ሪፖርተር፡- እስኪ ደግሞ ወደ ልጅነት ታሪክህ እንመለስ ከኢትዮጵያ ቤተሰቦች ተወለድክ፣ ለእንግሊዛዊ ቤተሰቦች ተሰጠህ እንደገና ደግሞ ተላልፈህ የልጆች ማሳደጊያ ማዕከል ወስጥ አደግክ፡፡ እስኪ ይኼ የልጅነት ጊዜህ የአሁኑን ለምን ሲሳይን በምን መንገድ ቀርጿል?

    ለምን፡- ከምንም በላይ ብዙ አሉታዊ ነገሮች ቢያልፉም አሁን ያለሁበት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን ለምን በልጅነቱ በብዙ መጥፎ ነገሮች ስላለፈ በዚህም ምክንያት አሁን ያለበት ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት አይደለም፡፡ እርግጥ ነው በብዙ መጥፎ ነገሮች ውስጥ አልፌያለሁ ስለዚህ መጠየቅ ያለብኝ በዚህ ውስጥ እኔ ማን ነኝ? የሚለውን ነው በመጥፎ ነገሮች ውስጥ በማለፌ ንዴት ውስጥ ገባሁ፣ ሌሎችን ጎዳሁ ወይስ ራሴን አደጋ ላይ ጣልኩ? በተቃራኒው የእኔ መገፋት፣ ሕመምና ስቃይ የሌሎችን ሕመም እንድረዳ እንዲሁም የመዳንን ኃይል እንድረዳ አድርጎኛል፡፡ እንደ እኔ የመዳን ኃይል ከመሠረቴ ነው ሥር መሠረቴ ደግሞ ከዚሁ ከኢትዮጵያ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እንግሊዝ ስላደገ፣ ጥሩ ትምህርት ስለተማረ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላሉ ነገር ግን ጥሩ ትምህርት አልነበረኝም ነበር፣ ተጎድቼ ነበር፡፡ እኔ እማውቀው ይኼን ሁሉ አሽንፌ መምጣቴን ነው፡፡ ብዙዎቻችን በቤተሰበ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች ስናልፍ ብዙ መጥፎ ልምዶች ሊኖሩን ይችላሉ፣ ልንጎዳ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ጥያቄው የእኛ መጎዳት ሌሎችን እንድንጎዳ መብት ይሰጠናል ወይ? የእኛ መጎዳት ሌሎችን እንድንጎዳ በፍጹም መብት አይሰጠንም፡፡ በተቃራኒው የእኛ መጎዳት የሌሎችን ሕመም፣ መገፋት እንዲሁም መነጠልን እንድንረዳ ያደርገናል፡፡ ይረዳናል፡፡ ይኼን ያህል ካወቅኩ እኔ ላይ የሆነው ሌሎች ላይ እንዲደገም አልፈልግም፡፡ ማነህ አንተ? እንግሊዛዊ ነህ? አይሪሽ ነህ ወይስ ኤርትራዊ ወይስ ደግሞ ሶማሊያዊ … ለእኔ አንተ ማለት ወንድሜ ነህ እዚህ ላይ በመተማመን አብሮ መሥራት፣ መኖር ይቻላል፡፡

    ሪፖርተር፡- እስኪ ከወላጅ እናትህ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ስትግናኙ ስለነበረው ነገር ንገረኝ?

    ለምን፡- የሚገርም ስሜት ነበር፡፡ የማርሸት ሲሳይ ወላጅ እናቴ በጣም የምትገርምና ጠንካራ ሴት ነች፡፡ እንደ አብዛኛው 1950ዎቹ 60ዎች ትውልድ ለትምህርት ወደ ውጭ የመሄድ ዕድል አግኝታ ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ ለትምህርት ወደ ውጭ የሄዱት የእናቴ ዓይነት ወጣቶች በዚያን ጊዜ የነበረውን የኢትዮጵያ መንፈስ ይዘው ዓለምን ዞረዋል፡፡ በጊዜው እናቴ እኔን አረገዘች ከዚያ ለጉዲፈቻ ሰጠችኝ፡፡ ብዙ ሰው የማያውቀው እናቴ ተመልሳ እኔን ለማግኘት ሞክራ እንደነበር ነው፡፡ እኔ ለሕፃናት ማዕከሉ በጻፈችው ደብዳቤ ልጇን እንደምትፈልግ፣ ልጇ በአገሩ እንዲያድግ እንደምትፈልግና በሰው አገር መገለል እንዳይደርስበት ገልጻ ነበር፡፡ በጊዜው እናቴ 21 ዓመቷ ነበር፡፡ እናቴ የሚቻላትን አድርጋ ነበር ግን እንግሊዞቹ መልሰው እኔን ሊሰጧት አልፈለጉም፡፡

    ሪፖርተር፡- ለእናትህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል?

    ለምን፡- በጣም እንጂ ማሰቡ ራሱ ይከብዳል፡፡ ከዚያ እናቴ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች፣ መመለስም ነበረባት ምክንያቱም በጊዜው አባቷ ታመው ነበር ከዚያም አቶ አሸናፊ ሽፈራውን አገባች፡፡ ከዚያም ከአምስት ዓመት በኋላ ደርግ ሥልጣን ያዘ፣ ባሏ ታሰረ፡፡ ስለዚህ ለሕይወቷ ስትል አገሩን ለቃ መሄድ ነበረባት፡፡ ጠንካራ ሴት ነበረች፡፡ ከብዙ ዓመት በኋላ 21 ዓመት ሲሆነኝ እናቴን አገኘሁ፡፡ ቀላል አልነበረም በእውነቱ፣ በጊዜው እሷን ማግኘት ውብ ነበር፡፡ እሷን ማግኘት ወደ ቤት እንደመመለስ ነበር ወደ ኢትዮጵያ፡፡

    ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልጄ፣ አድጌ ቢሆን ብለህ ታውቃለህ?

    ለምን፡- እሱንማ በምን ዕድሌ፡፡ ሁሌም የምፈልገው ነው ግን ደግሞ ማግኘት ያልቻልኩት ነው፡፡ ስለዚህ ያለኝን መቀበልና ባለኝ ነገር መኖር ነው፡፡ እውነቱን ለመቀበል በልጅነቴ የሚያውቁኝ እናት፣ አባት እንዲሁም እህትና ወንድም የለኝመ፡፡ ትልቁን የሕይወት ዘመኔን ሕልምና ምኞት ልንገርህ? የልዑል ዓለማየሁ አፅም ወደ አገሩ ሲመለስ ማየት ለእኔ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሕይወቱ ከእኔ ጋር ይገናኛል ብዬ አስባለሁ፡፡

    ሪፖርተር፡- ስለዚህ የእሱ ሕይወት ከአንተ ጋር ይገናኛል ብለህ ታስባለህ ማለት ነው?

    ለምን፡- በእንግሊዞች ከአገሩ ተወስዷል፡፡ አሥራ ስምንት ዓመት እስኪሞላው በካፒቴን ስፒዲ ሥር ሆኖ አድጓል፣ ከዚያም ሊድስ ወደ ተባለ ሰሜን ኢንግላንድ ወሰዱት፡፡ ከዚያም በዓመት ውስጥ ሞተ፡፡ እንደሚሉት ሞቱ የተፈጥሮ ሞት ነው ይላሉ፡፡ ለእኔ ይኼ አይዋጥልኝም፡፡ የሆነ ነገር ነበር የሆነ! ብዙ መጠናት ያለባቸው ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ እኔ ወደ አገሬ እንደተመለስኩ እሱም እንዲመለስ እፈልጋለሁ፡፡

    ሪፖርተር፡- ራስህን ማን ነኝ የምትለው?

    ለምን፡- ኢትዮጵያዊ፣ እንግሊዛዊ፣ የዓለም ዜጋ፣ የሞሎኪሎች የመንፈሶች ስብስብ፡፡

    ሪፖርተር፡- ስለራስህ ስናነሳ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ እንግሊዝኛ ማንበብም ሆነ መረዳት አይችሉም ሥራህን ለመተርጎም ያሰብከው ነገር አለ?

    ለምን፡- የተወጠኑ ነገሮች አሉ እስካሁን ባይሳኩም፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ከኤፍሬም ሥዩም ጋር አብረን እየሠራን ነው፡፡ ጥሩ የቋንቋ ችሎታ ያለው የጥበብ ሰው ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ገጣሚዎች ኤፍሬምን እንዲሁም የበውቀቱ ስዩምን ሥራዎች አደንቃለሁ፡፡ ትልቅ የሥነ ግጥም ሀብት ያለበት አገር ነው፡፡

    ሪፖርተር፡- ብዙ ጊዜ ስለ መነሳሳት ወይም መነቃቃት ትናገራለህ፡፡ በአንዱም ንግግር የአንተ ዓላማ በሰዎች መነሳት ወይም ደግሞ ሰዎችን ማነሳሳት (Inspire) ማድረግ ነው ብለህ ነበር፡፡ አንተን በጠዋት አንቅቶ ግጥም እንድትጽፍ የሚያደርግህ ምንድን ነው?

    ለምን፡- ሁሌም ከእንቅልፌ ስነቃ ግጥሞችን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ እለቃለሁ ይኼን ደግሞ እስክሞት የምቀጥለው ነገር ነው፡፡ ….. ፈጠራ ሙሉ በሙሉ በአርቲስቶች ቁጥጥር የተያዘ አይደለም፡፡ ሁሉም ሰው በራሱ መንገድ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ሥራ መነቃቃትን ወይም ሰዎችን ማንቃት መፈለግ ነው፡፡ መማር እና ማስተማር፡፡

    ሪፖርተር፡- መቼ ነው ግጥም መጻፍ እንደምትችል ያወቅከው?

    ለምን፡- ለምን የሚለው ስሜ መሆኑን ከማወቄ በፊት መግጠም ጀምሬ ነበር፡፡ ለምን የሚለውን ስም ይዤ እንዴት ገጣሚ መሆን አልችልም፡፡ እንግሊዞቹ የሰጡኝን ስም ይዤ እገጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ገጣሚ ሆኜ ነው የተወለድኩት ማለት ይቻላል፡፡

    ሪፖርተር፡- እስካሁን ያለህ የቻንስለርነት ቆይታ ምንይመስላል?

    ለምን፡- ጥሩ ነው፡፡ ለተማሪዎቼ የተስፋ ምንጭ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ፡፡

    ሪፖርተር፡- የራስህ ቤተሰብ የመመሥረት ሐሳብ አለህ?

    ለምን፡- ምን አልባት ወደ ፊት፡፡

    ሪፖርተር
    ‹‹ራሴን በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሀል ላይ ያለ ድልድይ አድርጌ ነው የምወስደው›› ገጣሚና ጸሐፊ ለምን ሲሳይ ትውልደ ኢትዮጵያ ብሪታንያዊው ለምን ሲሳይ ዕውቅ ገጣሚና ጸሐፊ ነው፡፡ በተለያዩ ጥበብ ተኮር ተቋማት እየሠራ ይገኛል፡፡ በሳውዝ ባንክ ማዕከል ተባባሪ አርቲስት፣ በሌተር ቦክስ ክለብ ድጋፍ ሰጪ፣ የቺልድረንስ ሪዲንግ ፈንድ አምባሳደር ሲሆን የክብር ዶክትሬት (ዶክተር ኦፍ ሌተርስ) ተሰጥቶታል፡፡ ለለንደን ኦሊምፒክ ግጥም የደረሰ፣ የበርካታ ተለጣጣቂ መጻሕፍት፣ መጣጥፎች፣ ሪከርዶች ወዘተ ጸሐፊ ነው፡፡ ከሰኔ 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ሆኖ ለሰባት ዓመታት አገልግሎት ተመርጧል፡፡ ኢትዮጵያ ተወልዶ ብሪታኒያ በጉዲፈቻ ያደገው ለምን ሕይወቱን ከአፄ ቴዎድሮስ ልጅ ልዑል ዓለማየሁ ጋር ያገናኘዋል፡፡ የልዑል ዓለማየሁ ቴዎድሮስ አፅም ወደ አገሩ እንዲመለስ ምኞቱ መሆኑንም ይናገራል፡፡ መሰንበቻውን ወደ ኢትዮጵያ ጎራ ያለውን ለምን ሲሳይን ዳዊት እንደሻው ስለ ዐውደ ሕይወቱ አውግቶታል፡፡ ሪፖርተር፡- በቅድሚያ ስለነበረህ የአንድ ሳምንት ቆይታ እስኪ ግለጽልን፡፡ ለምን፡- እስካሁን የነበረኝ ቆይታ በጣም አዝናኝና ፍሬያማ ነበር፡፡ ከብዙ ሰዎች ጋር የመገናኘቱን ዕድል አግኝቻለሁ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከሪታ ፓንክረስት ጋር የመገናኘቱን ክብር አግኝቻለሁ፡፡ በተጨማሪም አሉላ ፓንክረስት ጋር ተገናኝቼ ከማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት እንዴት የውጭ የትምህርት ዕድል ለኢትዮጵያውያን ማመቻቸት እንደምንችል መክረናል፡፡ እሱ ብቻ አይደለም ከብሪትሽ ካውንስል አዲስ ዳይሬክተር ፒተር ብራውን ጋር ተገናኝተናል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከአዲስ አበባና ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ከመጡ ምሁራን ጋርም የመገናኘቱን ዕድልም አግኝቼ ከውጭ የትምህርት ዕድሉ ጋር በተያያዘ እንዴት የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ከማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ጋር እንዴት መሥራት እንደሚችሉ ተነጋግረናል፡፡ እንግዲህ እኔ ራሴን በእንግሊዝና በኢትዮጵያ መሀል ላይ ያለ ድልድይ አድርጌ ነው የምወስደው፡፡ አሁን አሁን ጊዜዎች ባለፉ ዕድሜያችንም በገፋ ቁጥር እኔ እዚህ ያለሁት ለምክንያት ነው የሚለው ሐሳብ ሁሌም ይመጣብኛል፡፡ ይኼ ደግሞ ለእኔ መባረክ ነው፡፡ በዚች ታላቅ አገር ውስጥ በሚኖሩ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ተቀባይነትን ባገኘሁ ቁጥር በታወኩ ቁጥር ለእኔ ይሄ ትልቅ ነገር ነው፤ ስጦታ ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ መሆን ከኢትዮጵያ መፈጠር ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ ሪፖርተር፡- እስኪ ደግሞ ወደ ልጅነት ታሪክህ እንመለስ ከኢትዮጵያ ቤተሰቦች ተወለድክ፣ ለእንግሊዛዊ ቤተሰቦች ተሰጠህ እንደገና ደግሞ ተላልፈህ የልጆች ማሳደጊያ ማዕከል ወስጥ አደግክ፡፡ እስኪ ይኼ የልጅነት ጊዜህ የአሁኑን ለምን ሲሳይን በምን መንገድ ቀርጿል? ለምን፡- ከምንም በላይ ብዙ አሉታዊ ነገሮች ቢያልፉም አሁን ያለሁበት ላይ ደርሻለሁ፡፡ ይህ ማለት ግን ለምን በልጅነቱ በብዙ መጥፎ ነገሮች ስላለፈ በዚህም ምክንያት አሁን ያለበት ጥሩ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት አይደለም፡፡ እርግጥ ነው በብዙ መጥፎ ነገሮች ውስጥ አልፌያለሁ ስለዚህ መጠየቅ ያለብኝ በዚህ ውስጥ እኔ ማን ነኝ? የሚለውን ነው በመጥፎ ነገሮች ውስጥ በማለፌ ንዴት ውስጥ ገባሁ፣ ሌሎችን ጎዳሁ ወይስ ራሴን አደጋ ላይ ጣልኩ? በተቃራኒው የእኔ መገፋት፣ ሕመምና ስቃይ የሌሎችን ሕመም እንድረዳ እንዲሁም የመዳንን ኃይል እንድረዳ አድርጎኛል፡፡ እንደ እኔ የመዳን ኃይል ከመሠረቴ ነው ሥር መሠረቴ ደግሞ ከዚሁ ከኢትዮጵያ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እንግሊዝ ስላደገ፣ ጥሩ ትምህርት ስለተማረ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላሉ ነገር ግን ጥሩ ትምህርት አልነበረኝም ነበር፣ ተጎድቼ ነበር፡፡ እኔ እማውቀው ይኼን ሁሉ አሽንፌ መምጣቴን ነው፡፡ ብዙዎቻችን በቤተሰበ፣ በማኅበረሰብ ውስጥ እንዲሁም በተለያዩ ነገሮች ስናልፍ ብዙ መጥፎ ልምዶች ሊኖሩን ይችላሉ፣ ልንጎዳ እንችላለን፡፡ ነገር ግን ጥያቄው የእኛ መጎዳት ሌሎችን እንድንጎዳ መብት ይሰጠናል ወይ? የእኛ መጎዳት ሌሎችን እንድንጎዳ በፍጹም መብት አይሰጠንም፡፡ በተቃራኒው የእኛ መጎዳት የሌሎችን ሕመም፣ መገፋት እንዲሁም መነጠልን እንድንረዳ ያደርገናል፡፡ ይረዳናል፡፡ ይኼን ያህል ካወቅኩ እኔ ላይ የሆነው ሌሎች ላይ እንዲደገም አልፈልግም፡፡ ማነህ አንተ? እንግሊዛዊ ነህ? አይሪሽ ነህ ወይስ ኤርትራዊ ወይስ ደግሞ ሶማሊያዊ … ለእኔ አንተ ማለት ወንድሜ ነህ እዚህ ላይ በመተማመን አብሮ መሥራት፣ መኖር ይቻላል፡፡ ሪፖርተር፡- እስኪ ከወላጅ እናትህ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ስትግናኙ ስለነበረው ነገር ንገረኝ? ለምን፡- የሚገርም ስሜት ነበር፡፡ የማርሸት ሲሳይ ወላጅ እናቴ በጣም የምትገርምና ጠንካራ ሴት ነች፡፡ እንደ አብዛኛው 1950ዎቹ 60ዎች ትውልድ ለትምህርት ወደ ውጭ የመሄድ ዕድል አግኝታ ነበር፡፡ በዚያ ጊዜ ለትምህርት ወደ ውጭ የሄዱት የእናቴ ዓይነት ወጣቶች በዚያን ጊዜ የነበረውን የኢትዮጵያ መንፈስ ይዘው ዓለምን ዞረዋል፡፡ በጊዜው እናቴ እኔን አረገዘች ከዚያ ለጉዲፈቻ ሰጠችኝ፡፡ ብዙ ሰው የማያውቀው እናቴ ተመልሳ እኔን ለማግኘት ሞክራ እንደነበር ነው፡፡ እኔ ለሕፃናት ማዕከሉ በጻፈችው ደብዳቤ ልጇን እንደምትፈልግ፣ ልጇ በአገሩ እንዲያድግ እንደምትፈልግና በሰው አገር መገለል እንዳይደርስበት ገልጻ ነበር፡፡ በጊዜው እናቴ 21 ዓመቷ ነበር፡፡ እናቴ የሚቻላትን አድርጋ ነበር ግን እንግሊዞቹ መልሰው እኔን ሊሰጧት አልፈለጉም፡፡ ሪፖርተር፡- ለእናትህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር ማለት ይቻላል? ለምን፡- በጣም እንጂ ማሰቡ ራሱ ይከብዳል፡፡ ከዚያ እናቴ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰች፣ መመለስም ነበረባት ምክንያቱም በጊዜው አባቷ ታመው ነበር ከዚያም አቶ አሸናፊ ሽፈራውን አገባች፡፡ ከዚያም ከአምስት ዓመት በኋላ ደርግ ሥልጣን ያዘ፣ ባሏ ታሰረ፡፡ ስለዚህ ለሕይወቷ ስትል አገሩን ለቃ መሄድ ነበረባት፡፡ ጠንካራ ሴት ነበረች፡፡ ከብዙ ዓመት በኋላ 21 ዓመት ሲሆነኝ እናቴን አገኘሁ፡፡ ቀላል አልነበረም በእውነቱ፣ በጊዜው እሷን ማግኘት ውብ ነበር፡፡ እሷን ማግኘት ወደ ቤት እንደመመለስ ነበር ወደ ኢትዮጵያ፡፡ ሪፖርተር፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልጄ፣ አድጌ ቢሆን ብለህ ታውቃለህ? ለምን፡- እሱንማ በምን ዕድሌ፡፡ ሁሌም የምፈልገው ነው ግን ደግሞ ማግኘት ያልቻልኩት ነው፡፡ ስለዚህ ያለኝን መቀበልና ባለኝ ነገር መኖር ነው፡፡ እውነቱን ለመቀበል በልጅነቴ የሚያውቁኝ እናት፣ አባት እንዲሁም እህትና ወንድም የለኝመ፡፡ ትልቁን የሕይወት ዘመኔን ሕልምና ምኞት ልንገርህ? የልዑል ዓለማየሁ አፅም ወደ አገሩ ሲመለስ ማየት ለእኔ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ሕይወቱ ከእኔ ጋር ይገናኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ ሪፖርተር፡- ስለዚህ የእሱ ሕይወት ከአንተ ጋር ይገናኛል ብለህ ታስባለህ ማለት ነው? ለምን፡- በእንግሊዞች ከአገሩ ተወስዷል፡፡ አሥራ ስምንት ዓመት እስኪሞላው በካፒቴን ስፒዲ ሥር ሆኖ አድጓል፣ ከዚያም ሊድስ ወደ ተባለ ሰሜን ኢንግላንድ ወሰዱት፡፡ ከዚያም በዓመት ውስጥ ሞተ፡፡ እንደሚሉት ሞቱ የተፈጥሮ ሞት ነው ይላሉ፡፡ ለእኔ ይኼ አይዋጥልኝም፡፡ የሆነ ነገር ነበር የሆነ! ብዙ መጠናት ያለባቸው ብዙ የማናውቃቸው ነገሮች አሉ፡፡ እኔ ወደ አገሬ እንደተመለስኩ እሱም እንዲመለስ እፈልጋለሁ፡፡ ሪፖርተር፡- ራስህን ማን ነኝ የምትለው? ለምን፡- ኢትዮጵያዊ፣ እንግሊዛዊ፣ የዓለም ዜጋ፣ የሞሎኪሎች የመንፈሶች ስብስብ፡፡ ሪፖርተር፡- ስለራስህ ስናነሳ ብዙ ሰዎች በኢትዮጵያ እንግሊዝኛ ማንበብም ሆነ መረዳት አይችሉም ሥራህን ለመተርጎም ያሰብከው ነገር አለ? ለምን፡- የተወጠኑ ነገሮች አሉ እስካሁን ባይሳኩም፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ከኤፍሬም ሥዩም ጋር አብረን እየሠራን ነው፡፡ ጥሩ የቋንቋ ችሎታ ያለው የጥበብ ሰው ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ገጣሚዎች ኤፍሬምን እንዲሁም የበውቀቱ ስዩምን ሥራዎች አደንቃለሁ፡፡ ትልቅ የሥነ ግጥም ሀብት ያለበት አገር ነው፡፡ ሪፖርተር፡- ብዙ ጊዜ ስለ መነሳሳት ወይም መነቃቃት ትናገራለህ፡፡ በአንዱም ንግግር የአንተ ዓላማ በሰዎች መነሳት ወይም ደግሞ ሰዎችን ማነሳሳት (Inspire) ማድረግ ነው ብለህ ነበር፡፡ አንተን በጠዋት አንቅቶ ግጥም እንድትጽፍ የሚያደርግህ ምንድን ነው? ለምን፡- ሁሌም ከእንቅልፌ ስነቃ ግጥሞችን በማኅበራዊ ድረ ገጾች ላይ እለቃለሁ ይኼን ደግሞ እስክሞት የምቀጥለው ነገር ነው፡፡ ….. ፈጠራ ሙሉ በሙሉ በአርቲስቶች ቁጥጥር የተያዘ አይደለም፡፡ ሁሉም ሰው በራሱ መንገድ ፈጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ የእኔ ሥራ መነቃቃትን ወይም ሰዎችን ማንቃት መፈለግ ነው፡፡ መማር እና ማስተማር፡፡ ሪፖርተር፡- መቼ ነው ግጥም መጻፍ እንደምትችል ያወቅከው? ለምን፡- ለምን የሚለው ስሜ መሆኑን ከማወቄ በፊት መግጠም ጀምሬ ነበር፡፡ ለምን የሚለውን ስም ይዤ እንዴት ገጣሚ መሆን አልችልም፡፡ እንግሊዞቹ የሰጡኝን ስም ይዤ እገጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ገጣሚ ሆኜ ነው የተወለድኩት ማለት ይቻላል፡፡ ሪፖርተር፡- እስካሁን ያለህ የቻንስለርነት ቆይታ ምንይመስላል? ለምን፡- ጥሩ ነው፡፡ ለተማሪዎቼ የተስፋ ምንጭ በመሆኔ ደስተኛ ነኝ፡፡ ሪፖርተር፡- የራስህ ቤተሰብ የመመሥረት ሐሳብ አለህ? ለምን፡- ምን አልባት ወደ ፊት፡፡ ሪፖርተር
    0 Comments 0 Shares
  • Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • April 29 2017, 9:00 AM: Addis Farm Fest 2017, Laphto Mall
    Addis Farm Fest Organizer Eyovent Events invites all interested vendors to rent a booth/s and promote your business and services as well as to be a part of this great event to be held at Laphto Mall on Saturday and Sunday April 29-30, 2017.
    Fruit and vegetable farms, meat, fish and pottery, water, wine, beer companies fast food service givers. Coffee and Tea suppliers companies. farm wear and tools suppliers shops. wood and cotton handcraft shops and others. You all are invited to this great event and use this golden opportunity to be visible in the eyes of thousands farmers products loving families!!!!!! buy locally and eat healthy !!! get your space on time and be a part of Addis Farm Fest 2017 history. Come and enjoy the event!!!! For registration use the following contact numbers:(phone) 0966204945,0911760603,0911992684

    For more info, Download Events Ethiopia App

    Android App, --> https://goo.gl/ctXPBA
    iPhone App, --> https://goo.gl/m15nNB
    April 29 2017, 9:00 AM: Addis Farm Fest 2017, Laphto Mall Addis Farm Fest Organizer Eyovent Events invites all interested vendors to rent a booth/s and promote your business and services as well as to be a part of this great event to be held at Laphto Mall on Saturday and Sunday April 29-30, 2017. Fruit and vegetable farms, meat, fish and pottery, water, wine, beer companies fast food service givers. Coffee and Tea suppliers companies. farm wear and tools suppliers shops. wood and cotton handcraft shops and others. You all are invited to this great event and use this golden opportunity to be visible in the eyes of thousands farmers products loving families!!!!!! buy locally and eat healthy !!! get your space on time and be a part of Addis Farm Fest 2017 history. Come and enjoy the event!!!! For registration use the following contact numbers:(phone) 0966204945,0911760603,0911992684 For more info, Download Events Ethiopia App Android App, --> https://goo.gl/ctXPBA iPhone App, --> https://goo.gl/m15nNB
    0 Comments 0 Shares
  • A Plus Events and Promotions is proud to present Davido Live in Addis Concert featuring the one and only Sami-Dan with special appearance by Abush Zeleke and Amanuel Yemane on the 20th of May, at the Millenium Hall. SAVE THE DATE!!! Enterance Presales Tickets (Limited) 400 Birr, Regular 500 Birr, VIP 1000 Birr. #TeamAplus
    A Plus Events and Promotions is proud to present Davido Live in Addis Concert featuring the one and only Sami-Dan with special appearance by Abush Zeleke and Amanuel Yemane on the 20th of May, at the Millenium Hall. SAVE THE DATE!!! Enterance Presales Tickets (Limited) 400 Birr, Regular 500 Birr, VIP 1000 Birr. #TeamAplus
    0 Comments 0 Shares