• Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • www.zekariasn.wordpress.com
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታ እስካሁን ድረስ ግን ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት አልጀመረም።

    በአፍሪካ የመጀመሪያው ነው የተባለለት ረጲ የደረቅ ቆሻሻ የኃይል ማመንጫ ግንባታው የተጀመረው ከአምስት ዓመት በፊት ነበር።

    የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀ፥ ፕሮጀክቱ ሰኔ ወር 2009 ዓመተ ምህረት ነበር ግንባታው ተጠናቆ ስራ መጀመር የነበረበት ብለዋል።

    የፕሮጀክቱ መጓተት ምክንያቶችን አስመልክተው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ምስክር ነጋሽ እንደሚሉት፥ ወደ ግንባታው በሚገባበት ጊዜ በወቅቱ የኮንትራት ድርድር የተራዘመበት ሁኔታ መኖሩ በአንደኛነት አንስተዋል።

    በሁለተኛ ደረጃም ከግንባታ ቦታ ላይ የነበሩ የአዲስ አበባ መስተዳድር ንብረቶች የሆኑ በወቅቱ ባለመነሳታቸው እነሱ እስኪነሱ ድረስ የወሰደው ጊዜ እንደነበር ተናግረዋል።

    እንዲሁም ለማመንጫ የሚያገለግሉ እቃዎች ከውጭ አገር ተገዝተው የመጡ ከመሆናቸው አንፃር ግንባታው ስፍራ እስኪደርሱ ጊዜ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።

    እነዚህን እና ሌሎችንም መሰል ችግሮች አልፎ አሁን አፈጻጸሙ በመቶኛ ዘጠናዎቹ ውስጥ ገብቷል ከተባለ በኋላም ቢሆን በቅርቡ ይጠናቀቃል እየተባለ የ2010 ጥር ወር ላይ ደርሷል።

    ከዚህስ በኋላ መቼ ነው ይህ የሀይል ማመንጫ ግንባታው ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀምረው ለሚለው ጣቢያችን ላነሳው ጥያቄ፥ “በጋራ የተነጋገርነው ጊዜው ሲደርስ እናሳውቃለን የሚል ነው” ሲሉ አቶ ምስክር ነግረዉናል።

    ይህ ፕሮጀክት ግንባታው ከመጀመሩ በፊትም ቢሆን በጥናት ሶስት ዓመታትን አሳልፏል፤ በድምሩ ስምንት ዓመታት መሆኑ ነው።

    ኢንጂነር አዜብ አስናቀ፥ ስራው ከ95 በመቶ የተጠናቀቀ ቢሆንም የተተከሉት ነገሮች በትክክል ይሰራሉ ወይስ አይሰሩም የሚለው ፍተሻ እና ሙከራ መደረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

    ይሁን እንጂ በኮሪደሩ ውስጥ ነዋሪዎች እያሉ ሙከራ ለማድረግ የሚያስችል ሃይል መልቀቅ አይቻልም ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ፥ ምክንያቱም አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ አብራርተዋል።

    የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው እንደሚሉት፥ አሁን ባለው መረጃ በመስመሩ ሁለት የልማት ተነሺዎች ብቻ የቀሩ ሲሆን እነዚህ ለማንሳት በፍጥነት እንፈፅመዋለን ብለዋል።

    አቶ አባተ እንደሚናገሩት፥ የዚህ ፕሮጀክት መጠናቀቅ ምናልባትም ከሌሎቹም ባለድርሻ አካላት በላይ ከተማ አስተዳደሩ አጥብቆ ይፈልገዋል።

    ምክንያቱም ፕሮጀክቱ ለመዲናዋ ፅዳት እና ውበት ትልቅ ፋይዳ ስላለው እኛ ሃላፊነት ወስደን በአጭር ጊዜ የልማት ተነሺዎች ጉዳይን እናስተካክላለን ብለዋል።

    ፕሮጀክቱ እንደ ሃገር ከሚያመነጨው እና ወደ ብሄራዊ ቋት ከሚያስገባው ተጨማሪ የ50 ሜጋ ዋት ኃይል በላይ በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ለሚገኘው የከተማዋ ንፅህና የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

    ፕሮጀክቱ እንደተወራለት ከሆነ እጅግ ዘመናዊ በመሆኑ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ቀድሞ የደረቅ ቆሻሻ መጣያ የነበረው ስፍራ ሙሉ ለሙሉ ስለሚዘጋ በአካባቢው ነዋሪ ላይ ሲፈጥር የነበረውን መጥፎ ጠረን ያለው ጢስ እና ሽታ ማስቀረት ያስችላል።

    አሁን ቆሻሻ የተከመረበት ቦታም ተስተካክሎ አፈር ከተሞላ በኋላ በአረንጓዴ ተክሎች ተሸፍኖ ወደ መናፈሻ ስፍራነት ይለወጣል።

    ይህ ብቻ አይደለም፤ ቆሻሻው የኤሌክትሪክ ኃይል ካመነጨ በኋላ ተጨምቆ የሚወጣው ውኃ አትክልቶችን ለማልማት፣ በተረፈ ምርትነት የሚወጣው አመድም ለብሎኬት ማምረቻነት ይውላል።

    አቶ አባተ እንደሚሉት እነዚህ እና መሰል ጥቅሞቹ ተደማምረው ነው ከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ ከሁሉም በላይ በጉጉት እንዲጠብቀው እና በባለቤትነት ስሜትም እንዲሰራ ያደረጉት።

    ይሁን እና ምክትል ከንቲባው ፕሮጀክቱ ሲጀመር አካባቢ የካሳ ክፍያው ተጓቶ ስለነበር የልማት ተነሺዎችን በፍጥነት ከቦታው ከማንሳት ጋር በተያያዘ ችግሮች ነበሩ።

    የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አዜብ አስናቀም በበኩላቸው፥ የከተማ አስተዳደሩ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አንስተውልናል።

    በአጠቃላይ ቦታው ከሰዎችና ከቤቶች ነጻ ከተደረገ በኋላም ቢሆን ምናልባትም ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና ውጪ ብዙ አካባቢዎች ላይ እንደምናየው ዓይነት ቤቶችን ሰርተው በድጋሚ መኖር የጀመሩ ሰዎች ካሉ ከተማ አስተዳደሩ ማረጋገጥ እና አካባቢውን ነጻ ማድረግ ይጠበቅበታል።
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • www.zekariasn.wordpress.com
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚያም ሊገነባ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚስቴር ተናገረ
    የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚያም ሊገነባ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚስቴር ተናገረ፡፡ሚንስትሯ ዶ/ር ሒሩት ወ/ማርያም የመስሪያ ቤታቸውን የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ሲያቀርቡ እንዳሉት የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚገነባው በአድዋ ከተማ ነው፡፡

    ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር የሙዚየሙን የግንባታ ፕሮጀክት መነሻ ጥናት አጠናቋል ተብሏል፡፡የአድዋ ከተማ አስተዳደር ለአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚሆን ቦታ ማዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡

    ለግንባታው በአሜሪካ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ ሊያደርጉልን ቃል ገብተዋል ብለዋል ሚኒስትሯ፡፡በተያያዘ ከ13 አመት በፊት ከሮም የተመለሰውን እና በብረት ድጋፍ የቆመውን ቁጥር ሶስት የአክሱም ሐውልት የብረት ድጋፉን አንስቶ ለሐውልቶቹ ዘላቂ የመሰረት ጥገና ለማድረግ ከጣሊያን ድርጅት ጋር ውል መፈረሙን ሰምተናል፡፡

    የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሯ እንዳሉት ኢትዮጵያ በዩኔስኮ ካስመዘገባባቸውና የአለም ቅርስ ከሆኑ መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዱ ሲሆን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች ገጥመውታል፡፡መላ ለመፈለግም በኢትዮጵያ በቅርስ ጥገና ላይ የተሻለ እውቀት ያላቸው ምሁራን እንዲያጠኑት ተደርጓል ብለዋል፡፡

    ቅርሱን ለመታደግ በመጪው ጊዜ ስለሚወሰዱ እርምጃዎች የዩኔስኮ ፍቃድና ድጋፍ ለማረጋገጥ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል ያሉት ሚንስትሯ በጀመርነው የጥር ወር አጋማሽ ከዩኔስኮ፣ አይኮምስ እና ኢክሮም ጥምር የቴክኒክ ኮሚቴ በላሊበላ በአካል ተገኝተው ስለ ጉዳዩ ለመምከር ቀጠሮ ተይዟል፡፡

    የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ለመጠገን ሰማንያ ሚሊየን ዶላር ያስፈልጋል፡፡ ኢትዮጵያ የበርካታ ቅርሶች ባለቤት ብትሆንም ብዙዎቹ እርጅና ተጭኗቸው የመፍረስ አደጋ እያንዣበበባቸው ነው ተብሏል፡፡

    አገሪቱ እነዚህን ቅርሶች የሚጠግን የሰው ሀይል አለማፍራቷና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚመደበው በጀት ቅርሶቹን ለመጠገን በቂ አለመሆኑ ፈተና ሆኖብናል ብለዋል ዶ/ር ሒሩት፡፡የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ እያካሄደ ባለው የሶስተኛ አመት የስራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማን ለመደንገግ እንዲሁም የህግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩን ለማቋቋም የቀረቡ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • www.zekariasn.wordpress.com
    Like
    1
    0 Comments 0 Shares
  • www.zekariasn.wordpress.com
    www.zekariasn.wordpress.com
    Like
    4
    1 Comments 6 Shares
  • 0 Comments 0 Shares