በቅርብ የተከናወኑ
  • you can find cassation volume 20 easily in the link below
    https://lawethiopiacomment.wordpress.com/2017/05/23/cassation-volume-20/
    you can find cassation volume 20 easily in the link below https://lawethiopiacomment.wordpress.com/2017/05/23/cassation-volume-20/
    LAWETHIOPIACOMMENT.WORDPRESS.COM
    cassation volume 20
    you can find by my Facebook page Ethiopian Law……enjoy it!!!!!!
    0 Comments 0 Shares
  • በሰበር ውሳኔዋች ላይ የሚታዮ አንዳንድ ተደጋጋሚ ችግሮች
    የሰበር ሰሚ ችሎት በኢፌድሪ ህገ መንግሰት አንቀጽ 80(3) መሰረት እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 እና በተለየ በተቋቋመበት በኣዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት የተለያዩ ውሳኔዋችን እየሰጠ እና ጠቃሚ ናቸው ለህብረተሰቡ መዳርስ አለባቸው ያለውን በጥራዝ መልክ እያሳተመ ሲያወጣ እነሆ አሁን 20ኛው ቅፅ ላይ ደርሷል፡፡የተቋቋመበትንም አላማ ከሞላ ጎደል እየመታ ነው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ አላማዎቹ ባጭሩ በፃፊው እምነት የሚከተሉት ናቸው፡፡
    ወጥነት
    ተገማችነት
    ግልፅነት እና
    የሲቪል የህግ ስርአት ያለበትን ክፍተት መሙላት
    በተቃራነው የተለያዩ አስተያየቶች በሰበር ውሳኔዋች ላይ ይሰጣሉ ፡፡ የዘህ ፅሁፍ አላማ አሰቴየቶቹን መተንተን ሳይሆን አስተያየቶቹን እንደወረዱ በማቅረብ ጥናት እንዲደረግባቸው ለመጠቆም ነው፡፡ በሰበር ሰሚው ችሎት የተሰጡ ውሳኔዋች(የታተሙትንም ያልታተሙትንም ያጠቃልላል) ላይ ከሚሰነዘሩ ትችቶች መሀክል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ በህግ ትርጉም ሰም የህግ አውጪውን ስራ ያለስልጣኑ እየሰራ ነው ፣ የተሻሩትን እና ያልተሻሩትን ውሳኔዎች በግልፅ ለይቶ ማስቀመጥ አልቻለም፣ የመንግስት ፖሊሲ አስፈጻሚ ነው ከህግ ወደ ፖሊሲ ያደላል፣ ጉራማይሌ ቋንቋ የጠቀማል፣ የሃገር ውሰጥ ህጎች ብቻ ላይ ነው አተኩሮ የሚሰራው አለም አቀፍ ህጎች እና መሰረታዊ የህግ መርሆችን ( በተለይም ያዲሱን ትውልድ የህግ ፍልስፍና) በመጠቀም የሰጠው ውሳኔ በጣም አናሳ ወይም የሉም ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፣ ከተቋቋመበት አላማ ውጪ ማስረጃ ምዘና ውሰጥ እና ተጨማሪ ማስረጃ ምዘና ውሰጥ ይገባል ፣ ተፈጻሚነቱ በሀገሩ ሁሉ ሆኖ ሳለ ማንድ ቋንቋ ብቻ መታተሙ በሌላ ቋንቋ ተጠቃሚ ክልልሎች ዘንድ ችግሮችን ይፈጥራል፣ ችሎቱ እንደችሎተም ሆነ አገልግሎቱ እየተሰጠ ባለበት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍረድ ቤት አገልግሎቱ ከፋይል ማስከፈት አንስቶ በጣም አመቺነት የሌለው ፡ በጣም ወረፋ የበዛበት እና ለሙስና ተጋለጭ ነው፡ የሰው ሄል እጥረት በግልጽ እታየበት ካመት አመት ምንም መፍተሄ አልተሰጠውም በመሆኑም መሰረታዊ መብቶች ላ መዛባትን እየፈጠረ ይገኛል ፣ ቀጠረዎች በጣም የተንዛዙ ናቸው፣ ወዘተ…. የሚሉ ትችቶች ከተገልጋዮች እና ከህግ ባለሙያው ይነሳል፡፡ ከላይ የተነሱት እና ሌሎችም ችግሮች በችሎቱ ውሳኔዎች እና አሰራሮች ላይ የሰነዘራሉእያንዳንዳቸው እራሳቸውን ችለው የጥናት ርእስ መሆን የሚችሉ ናቸው፡፡ ስለዘህ ብዙ ሊባልበት ፣ ሊጻፍበት ፣ ሊጠና ይገባል ፡፡ ችሎቱ እና አስተዳደሩም በራቸውን በቀዳሚነት ክፍት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ይህ ገጽም የናንተው ነው፡፡ ልትጽፉበት፣ አስተያየታችሁን ልትሰጡበት፣ ልትከራከሩበት፣ ልትጠይቁበት ትችላላችሁ፡፡
    የመንስኤው መንስኤ የውጤቱ መንስኤ ነው፡፡
    ዳንኤል ፍቃዱ(ጠበቃ እና የህግ መምህር)©
    በሰበር ውሳኔዋች ላይ የሚታዮ አንዳንድ ተደጋጋሚ ችግሮች የሰበር ሰሚ ችሎት በኢፌድሪ ህገ መንግሰት አንቀጽ 80(3) መሰረት እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 እና በተለየ በተቋቋመበት በኣዋጅ ቁጥር 454/97 መሰረት የተለያዩ ውሳኔዋችን እየሰጠ እና ጠቃሚ ናቸው ለህብረተሰቡ መዳርስ አለባቸው ያለውን በጥራዝ መልክ እያሳተመ ሲያወጣ እነሆ አሁን 20ኛው ቅፅ ላይ ደርሷል፡፡የተቋቋመበትንም አላማ ከሞላ ጎደል እየመታ ነው ብሎ መናገር ይቻላል፡፡ አላማዎቹ ባጭሩ በፃፊው እምነት የሚከተሉት ናቸው፡፡ ወጥነት ተገማችነት ግልፅነት እና የሲቪል የህግ ስርአት ያለበትን ክፍተት መሙላት በተቃራነው የተለያዩ አስተያየቶች በሰበር ውሳኔዋች ላይ ይሰጣሉ ፡፡ የዘህ ፅሁፍ አላማ አሰቴየቶቹን መተንተን ሳይሆን አስተያየቶቹን እንደወረዱ በማቅረብ ጥናት እንዲደረግባቸው ለመጠቆም ነው፡፡ በሰበር ሰሚው ችሎት የተሰጡ ውሳኔዋች(የታተሙትንም ያልታተሙትንም ያጠቃልላል) ላይ ከሚሰነዘሩ ትችቶች መሀክል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡ በህግ ትርጉም ሰም የህግ አውጪውን ስራ ያለስልጣኑ እየሰራ ነው ፣ የተሻሩትን እና ያልተሻሩትን ውሳኔዎች በግልፅ ለይቶ ማስቀመጥ አልቻለም፣ የመንግስት ፖሊሲ አስፈጻሚ ነው ከህግ ወደ ፖሊሲ ያደላል፣ ጉራማይሌ ቋንቋ የጠቀማል፣ የሃገር ውሰጥ ህጎች ብቻ ላይ ነው አተኩሮ የሚሰራው አለም አቀፍ ህጎች እና መሰረታዊ የህግ መርሆችን ( በተለይም ያዲሱን ትውልድ የህግ ፍልስፍና) በመጠቀም የሰጠው ውሳኔ በጣም አናሳ ወይም የሉም ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፣ ከተቋቋመበት አላማ ውጪ ማስረጃ ምዘና ውሰጥ እና ተጨማሪ ማስረጃ ምዘና ውሰጥ ይገባል ፣ ተፈጻሚነቱ በሀገሩ ሁሉ ሆኖ ሳለ ማንድ ቋንቋ ብቻ መታተሙ በሌላ ቋንቋ ተጠቃሚ ክልልሎች ዘንድ ችግሮችን ይፈጥራል፣ ችሎቱ እንደችሎተም ሆነ አገልግሎቱ እየተሰጠ ባለበት የፌደራሉ ጠቅላይ ፍረድ ቤት አገልግሎቱ ከፋይል ማስከፈት አንስቶ በጣም አመቺነት የሌለው ፡ በጣም ወረፋ የበዛበት እና ለሙስና ተጋለጭ ነው፡ የሰው ሄል እጥረት በግልጽ እታየበት ካመት አመት ምንም መፍተሄ አልተሰጠውም በመሆኑም መሰረታዊ መብቶች ላ መዛባትን እየፈጠረ ይገኛል ፣ ቀጠረዎች በጣም የተንዛዙ ናቸው፣ ወዘተ…. የሚሉ ትችቶች ከተገልጋዮች እና ከህግ ባለሙያው ይነሳል፡፡ ከላይ የተነሱት እና ሌሎችም ችግሮች በችሎቱ ውሳኔዎች እና አሰራሮች ላይ የሰነዘራሉእያንዳንዳቸው እራሳቸውን ችለው የጥናት ርእስ መሆን የሚችሉ ናቸው፡፡ ስለዘህ ብዙ ሊባልበት ፣ ሊጻፍበት ፣ ሊጠና ይገባል ፡፡ ችሎቱ እና አስተዳደሩም በራቸውን በቀዳሚነት ክፍት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ይህ ገጽም የናንተው ነው፡፡ ልትጽፉበት፣ አስተያየታችሁን ልትሰጡበት፣ ልትከራከሩበት፣ ልትጠይቁበት ትችላላችሁ፡፡ የመንስኤው መንስኤ የውጤቱ መንስኤ ነው፡፡ ዳንኤል ፍቃዱ(ጠበቃ እና የህግ መምህር)©
    0 Comments 0 Shares
More Stories