ጀግና እወዳለሁ!

0
0

ጀግና እወዳለሁ!

«ዘውድአለም ታደሰ»

ጀግና እወዳለሁ ተኳሽም አልጠላ
ሲደክመኝ አርፋለሁ ከጎፈሬው ጥላ!

ብላለች የሃገሬ ገጣሚ! ጀግና እወዳለሁ .... አላማ ያለው፣ የሞትን ፍርሃት አሸንፎ ቀና ብሎ የሚኖር ፣ በፈተና የማያጎነብስ ፣ መከራ ወኔውን የማይሰልበው ፣ እስከመጨረሻዋ እስትንፋሱ የሚታገል ፣ ጀግና እወዳለሁ!

ኢብራሂም አቡ ዙሪያ አለማችን ካፈራቻቸው ጀግኖች አንዱ ነው! አለም ስለጀግንነቱ ባይዘምርለትም የፓለስታይን ህዝብ ስሙን ዘልአለም የሚያወድሰው ፣ ለሐገር የሚከፈለውን የመጨረሻውን ፅዋ ጨልጦ ለብዙዎች የሞራል ስንቅ ሆኖ ያለፈ የፅናት ተምሳሌት ነው የነፃነት አርበኛው ኢብራሂም ኡቡ ዙሪያ!!

ሁለት እግሮቹን ያጣው ከእስራኤል ታጣቂ ወታደሮች ጋር ለነፃነቱ ሲታገል ነው! ነገር ግን ጥይቱ እግሩን እንጂ ወኔውን አላስጣለውም ነበር። ሁሉን ነገር እርግፍ አርጎ ትቶ ለልመናም እጁን አልዘረጋም! ቤተሰቡን መኪና በማጠብ እያስተዳደረ ጎን ለጎን ደግሞ ከወገኖቹ ጋር ትግሉን ቀጠለ!
ሮጦ ማምለጥ ባይችልም ጥይት እንደዝናብ የሚወርድበት ቅልጥ ያለ ጦርነት ውስጥ ይቀላቀላል ፣ በእጁ እየዳኸ በእሳት መሃል እየተሽሎከለከ ፣ ዊልቸሩን እየጎተተ ከታጠቁ ወታደሮች ጋር ይተናነቃል! የሃገር ፍቅር ልክፍት እንዲህ ነዋ! የአላማ ፅናት ይሄ ነዋ! የጀግና ተግባር ይሄ ነዋ!

ኢብራሂም ትናንት ከእስራኤል ወታደሮች በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ወደቀ!! ፓለስታይን በሃዘን አነባች ፣ ለሚሊየኖች የፅናት ምልክት የሆነው ሃያል ሰው ወደቀ! መከራና ፈተና ፣ የአካል መጉደልና ችግር ሊጥለው ያልቻለው ፅኑእ ታጋይ ወደቀ! ትናንት አካሉን ፣ ዛሬ ደግሞ ነፍሱን ለሃገሩ ሰጥቶ በየክፍለዘመኑ አንዴ የሚፈጠረው ኢብራሂም አቡ ዙሪያ የሚወዳት ሃገሩ ላይ ዳግም ላይመለስ .... ወደቀ!!

ጀግና እወዳለሁ !

Search
Categories
Read More
Uncategorized
Ardale Face Of Harari
http://www.ethio.me/pages/Ardaleharari
By shagiz 2017-11-14 09:41:26 0 0
Uncategorized
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር አያሌ ዜጐችን በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት ተምረው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ማስቻሉ በጥናት...
By Seller 2017-11-15 07:31:38 0 0
Uncategorized
ልክ የዛሬ 21 ዓመት ይህ ሆኗል
በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኘው የኮሞሮስ ደሴት ተመራጭ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራ ነች። በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ሲዝናኑ የነበሩ ጎብኚዎች እና...
By Dawitda 2017-11-23 06:15:19 1 0
Uncategorized
ሀገራዊ ዕብደት
(ዳንኤል ክብረት) ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ በቤታችን ደኅና መጥፋቱ ነወይ የሚል የበገና ዘለሰኛ አለ፡፡ አሁን ያለችውን ሀገራችንን ቀድሞ ያየ...
By binid 2017-11-25 13:24:18 0 0
Uncategorized
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)
የከፍታው ዘመን ተጀመረ! (ሃፒ በርዝ ዴይ)፡ፒስ ነው ጋይስ?!ቃሉን የማያጥፈው መንግስታችን "መጪው ዘመን የከፍታ ነው" ባለው መሰረት ከሰሞኑ ዶላሩን...
By andualem 2017-11-12 15:14:07 0 0