70 ሜትር ከፍታ ባለው ገመድ ላይ የተራመደው ግለሰብ አዲስ ክብረ ወሰን ይዟል
ከመሬት230 ጫማ ወይም 70 ሜትር ከፍታ ላይ በታሰረ ቀጭን ገመድ ላይ የተራመደው ግለሰብ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ይዟል።
ናታን ፓውሊን የተባለው የ23 ዓመት ወጣት ነው ክብረ ወሰኑን በእጁ ያስገባው።
ናታን ክበረ ወሰኑን በፈረንሳይ ፓሪስ ያስመዘገበ ሲሆን፥ ከታሪስ ትሮካዴሮ አደባባ እስከ ኤፍል ታወር የተዘረጋው ገመድ ላይ ነው ሚዛኑን ጠብቆ የተጓዘው።
የ23 ዓመቱ ወጣት 700 ሜትር ገደማ ርዝመት ባለውና በሴይን ወንዝ ላይ የተዘረጋው ገመድ ላይ በመጓዝ ነው ክብረ ወሰኑን በእጁ ያስገባው።
ናታን ፓውሊን በዚህ ተግባሩም ከዚህ ቀደም በራሱ ይዞት የነበረውን ክብረወ ሰን ነው ያሻሻለው ተብሏል።
በገመዱ ላይ በመጓዝ ላይ እያለ ወድቆ በገመዱ ላይ ተንጠልጥሎ የተረፈው ናታን፥ አጠቃላይ በገመዱ ላይ ሆኖ ርቀቱን ለማቋረጥ 30 ደቂቃ ያክል ፈጅቶበታል።
ናታን ፓውሊን እንዲህ አይነት ተግባር የፈፀመውም ለበጎ አድራጎት ስራ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ አንደሆነም ተነግሯል።
Search
Categories
- Home
- Wellness
- Theater
- Sports
- Shopping
- Religion
- Party
- Other
- Networking
- Music
- Literature
- Art
- Health
- Gardening
- Games
- Food
- Fitness
- Film
- Drinks
- Dance
- Crafts
- Causes
Read More
የዚምባብዌ ጦር ገዢው ፓርቲ ላይ በሚደረገው ጣልቃ ገብነት ላይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ
ብዙም ያልተለመደው የጣልቃ ገብነት ጉዳይ የተከሰተው ሃገሪቱ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ምክትላቸው ኤመርሰን ምናንጋግዋን ከስራ ካሰናበቱ በኋላ ነው። ከ90...
‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ››
አሌክስ አብርሃም‹‹ እፎፎፎፎይ አሉ እቴጌ ጣይቱ››(ከድድ አድማስ ኋላ)
እዚህ አራዳ ህንፃ የሚባለው አንደኛ...
ወርቃማው ደብዳቤ !
(አሌክስ አብረሃም)
እንዴት ናት ኢትዮጲያ እንዴት ነው አፈሩ ጤናቸው እንዴት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ?ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህናናቸው...
ልክ የዛሬ 21 ዓመት ይህ ሆኗል
በደቡብ ምስራቅ አፍሪካ የምትገኘው የኮሞሮስ ደሴት ተመራጭ የጎብኚዎች መዳረሻ ስፍራ ነች።
በህንድ ውቅያኖስ ዳርቻ ሲዝናኑ የነበሩ ጎብኚዎች እና...