ከነጠላው ስር !!

0
0

(አሌክስ አብርሃም)

የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ ሁሉ በግ መስሎን ተበላን ጓዶች !!እኛ ኢትዮጲዊያን በተለይ በዚህ ሰአት ‹‹ፈጠራ ማለት›› የሰውን ፈጠራ ነጠላ ማልበስ እየመሰለን መጥቷል !ነጠላና ጥበብ የለበሰው ሁሉ የእኛ ባህል የእኛ ፈጠራ ይመስለናል ! ምን አይነት በሽታ ነው ይሄ ? ምናይነትስ የአእምሮ መደፈን ነው ….ግርምኮ ነው የሚለው ! እንግዲህ ነጠላ እያለበስን ያስገባነውና ነጠላችንን አስጥሎ እርቃን ያስቀረንን ቀበሮ እንቁጠር ካልን ቁጥር ስፍር የለውም …

ሶሻሊዝም ነጠላ ለብሶ መጣ … እልል ብለን ተቀበልነው እርስ በእርስ አባልቶ ለዚች ሚስኪን አገር አለኝታ የነበሩ ስንት ጉምቱ ሊህቃንን ስንት ባለወርቅ አእምሮ ዜጎቻችንን በቆሻሻ የፖለቲካ እሳት አቃጥሎ አገራችንን ነጠላዋን ገፎ እርቃኗን አስቀራት !ለከፈን እንኳን አላስቀረላትም እርቃን!! ይሄው እስካሁን ብርድ ብርድ እያለ በትንሽ በትልቁ የሚያሰላት አገር አተረፍን ….ነጠላዋን ጣለቻ !!

ቀጠለ… የቻይና ተሞክሮ የዩጎዝላቪ ተሞክሮ የአልቤኒያ ተሞክሮ እያልን የኛኑ ነጠላ አከናንበን ያስገባነው አሰስ ገሰስ አገራችን እግሩ ከመርገጡ የአንድነት ጋቢያችንን ገፎ በዘር አባላን አፋጀን እርቃን አስቀረን ! ይሄው ይሄን ፅሁፍ እያነበብክና እያነበብሽ እንኳ ሚሊየኖች በየማጀታቸው ገጀራቸውን ስለው የአንድነት ነጠላቸውን በሽክተው እራፊ ይዘው ለመሄድ ይፎክራሉ ! ወጣቱን ተመልከት እርቃኑ ላይ የነጠላ እራፊ ጣል አድርጎ እርቃንነት ኢትዮጲዊ ነው ሊልህ ይዳዳዋል ! ሙዚቃው ፋሽኑ አኗኗሩ እምነቱ …..ነጣላ ለብሶ ይመጣል ነጣጥሎን ይሄዳል አልያም እድሜ ልኩን የሚያመረቀዝ ህመም ሁኖ ወስጣችን ይቀራል!!

ለመሆኑ ኢትዮጲ የምትባል አገር አሁን በዚች ሰዓት የራሴ የምትለው ባህል ምን ቀርቷታል …ባህሉ ይቅር ያልተቀላቀለ ማንነት የት ይሆን ያለው….‹‹እኔ›› ማለት እስኪያቅተን ምላሱን አርዝሞ ስለኢትዮጲ የሚዘባርቀው ማነው …ኢትዮጲዊ ያልሆነ ግን ኢትዮጲዊ ነጠላ ለብሶ የሚያምሰን ቅይጥ ሁሉ ነው ! ወይ ስጋው ወይ ነብሱ ኢትዮጲዊ ያልሆነ ግን ‹‹ኢትዮጲዊ›› ነጠላ ለብሶ ከኔም ወዲያ ለዚች አገር የሚል አለሁ ባይ !! አዎ የኛን ልብስ ለብሶ ያየነው ሁሉ ያምረናል …የእኛን አእምሮ የእኛን ስነልቦና የእኛን እምነትና መንፈስ የተካፈለ ይመስለናል ….ግን በዚች አጭር ጊዜ የገባኝ እውነት ማንም የቱንም ያህል ቢወደን በፍቅራችን ቢያብድ እኛን መሆን አይችልም ….እኛም ማንንም አንሆንም !!

ደግሞስ የሌላ አገር ዜጎች ልብሳችንን ቢለብሱ ቋንቋችንን ቢናገሩ ጭምር ምንድነው እልል የሚያስብለው ጉዳይ ….ከምር ምንድነው …ለምሳሌ በጣም የተገረምኩበት ነገር አሜሪካ ምድርን አንዳንዶቹ ስቴትማ ሙሉ በሙሉ ልትሉት ትንሽ በሚቀራችሁ ሁኔታ ያጥለቀለቃት ባህል ቋንቋና ምግብ የማን ይመስላችኋል ….የሜክሲኮ ! ሜክሲኮዋያን አሜሪካ ውስጥ ያን ያህል ተፅእኖ ስለፈጠሩ አገራቸው ምን ሆነች የት ደረሰች …ምንም አልሆነችም ….የትም አልደረሰችም ! እንደውም ዝምድናችሁም ጉርብትናችሁም ይቅርብን በሚል ቅሌት አገራቸውን ከአሜሪካ ለመለየት የግንብ አጥር ይገንባባቸው የተባሉ ህዝቦች ሆኑ !!

ማንነታችሁን ማወቅ እንጅ ማሳወቅ የመጀመሪያ ጉዳይ አይደለም ….ማንነታችን ለራሳችን ጠፍቶን ሌሎች ካላወቁን ብሎ ችክ ማለት ምን ይፈይዳል !! አንዳንዴ ከነጠላው ተነጥለን ልብሳችንን የለበሰልልንን ባእድ ሳይሆን እኛን እኛ ያደረገንን እውነት ወደማክበሩ እልፍ እንበል !! ከነጠላ እንነጠል !!

Search
Categories
Read More
Uncategorized
መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው __
ወጣቱ የአንድን አርሶ አደር ቆንጆ ልጃገረግ ማግባት ፈልጓል፡፡ እናም ወደ አባቷ ቀርቦ ፍቃዳቸው ይሆን ዘንድ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ አባት ልጁን ከእግር...
By Dawitda 2017-11-14 07:48:20 0 0
Other
HÀNG CHÍNH HÃNG: Xe Nâng Điện UNICARRIERS 1.5 Tấn J1B1L15 (FB15)
Bạn đang tìm kiếm một chiếc xe nâng điện mạnh mẽ, bền bỉ, hoạt động êm...
By xenangaz 2025-04-16 07:03:52 0 0
Uncategorized
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ...
By andualem 2017-11-12 15:13:23 0 0
Uncategorized
ብልጽግና
"3 And he shall be like a tree planted by the rivers of water, that bringeth forth his fruit in...
By Amanunegn 2017-12-03 13:00:45 0 0
Uncategorized
ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
 ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __ ትንሹ ልጅ እናቱን “ማሚ ለምን ታለቅሻለሽ?” ሲል ጠየቃት “ምክንያቱም...
By Dawitda 2017-11-17 07:15:51 0 0