ወርቃማው ደብዳቤ !

0
0

(አሌክስ አብረሃም)

እንዴት ናት ኢትዮጲያ እንዴት ነው አፈሩ 
ጤናቸው እንዴት ነው ጠቅላይ ሚንስትሩ ?
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደህናናቸው መቸም 
እንደሰፌድ ቆሎ ባበጣሪው መንግስት እየተንጓለሉ 
ዛሬም ለፓርላማው ህልም እያነበቡ በዛው የጉድ ወንበር በዛው ስላቅ አሉ !

አሁን በቀደምለት ማንትስ ወረዳ ምንትስ ክልል 
‹‹ሰፌድ ይዞ ወርዶ ወርቅ ያበጥር ህዝቡ›› 
የሚል ማስታወቂያ ለህዝቡ አነበቡ 
ይህንን ሰምቸ ወደናቴ ማጀት ዘልየ ብገባ 
የንጀራ ሰፌዱን ጥቀርሻ ወርሶታል 
እንኳን ‹‹የሰማይ ላም›› ድሮ ያበጥረው ቆሎ እንኳ ናፍቆታል !!

ተመስገን ነው መቸም ….
እኒህ ጠቅላያችን በዚህ ከቀጠሉ 
በቀጣይ ስብሰባ ጀሪካ ይዛችሁ 
ምንትስ ክልል ነዳጅ ቅዱ ቢሉ
ያው የሳቸው ነገር ምኑ ይታወቃል 
በሚል ጥርጣሬ….ወርቁ ያመለጠው 
በርሚል አዘጋጅቶ ድፍድፍ ይጠብቃል !

አንዳንድ ነዋሪዎች ‹‹ለዜና ምንጫችን›› እንዳሉት ከሆነ 
ህዝባችን በሙሉ እንደሳጋቱራ ወርቅ ከዘገነ 
ስስታም ሸቃጮች እንጀራ ሚሸጡ 
ሳጋቱራ ትተው የጤፍ እንጀራ ላይ ወርቅ እንዳይቀይጡ 
የፌዴራል ፖሊስ የወርቅ ጠመንጃ ከወርቅ ዱላ ጋ ለትጥቅ አሰርቶ
ይከታተልንን የገቡበት ገብቶ !! 
ሲሉ አሳስበዋል!!

ሌላ ከታማኝ ምንጭ የወጣ መረጃ 
እጣው የዘገየው የጋራ መኖሪያ የብረት ደረጃ 
በወርቅ እስኪለበጥ ነው የሚሉም አሉ 
እኔ ምን አውቃለሁ …. ብቻ የሰማሁትን ይሄው እፅፋለሁ!

እና ውድ ወዳጀ አሌክስ የትላንቱ
ድፍን አገራችን ድፍን ብናኝ ወርቅ ተሞልቶ 
ያስነጥሰን ይዟል በምኞት አፍንጫ ሳንፈቅድለት ገብቶ

በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ፖስታውን ስትከፍት 
ድንገት ቢቦንብህ የወርቅ አቧራ 
ያው ፖስታ ቤታችን ባለመፀዳቱ ሊሆን ስለሚችል 
‹‹ለመልካም ገፅታ›› ለማንም አታውራ !
አደራ !
አደራ !

Search
Categories
Read More
Uncategorized
እንቆቅልሽ የሆነው የወተት ምርት
ኢትዮጵያ በቀንድ ከብቶች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚውን ሥፍራ፣ በዓለም ከ10 አገሮች መካከል አንዷ ብትሆንም ከወተት ሀብቷ ማግኘት የሚገባትን ያህል ጥቅም...
By Seller 2017-12-22 07:02:06 1 0
Uncategorized
ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣን እንደማይለቁ ገለፁ
በራሳቸው ፍቃድ ከፕሬዚዳንትነታቸው እንዲወርዱ ጫና እየተደረገባቸው ያሉት የዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ትናንት በሰጡት መግለጫ ስልጣን እንደማይለቁ...
By Dawitda 2017-11-20 07:15:43 0 0
Uncategorized
Ethiopia might have the world’s finest cuisine for vegans (and any foodie).
Confession: I chose to travel to Ethiopia because I’ve been in love with Ethiopian cuisine...
By mahi 2017-11-26 07:01:32 0 0
Uncategorized
ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __
 ሴቶች ለምን እንዲሁ ያለቅሳሉ __ ትንሹ ልጅ እናቱን “ማሚ ለምን ታለቅሻለሽ?” ሲል ጠየቃት “ምክንያቱም...
By Dawitda 2017-11-17 07:15:51 0 0
Uncategorized
ስድስተኛው ገፅ!
ስድስተኛው ገፅ!«ዘውድአለም ታደሰ» እንዴት ናችሁ ክቡራትና ክቡራን? እነሆ ሰአቱን ጠብቆ የማይከፈለው የፌስቡኩ ጥፎ አዳሪ...
By Zewdalem 2017-11-14 04:03:16 0 0