ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችን በመበደል ከዓለም ቀዳሚ ሃገራት አንዷ ነች ተባለ

0
0

ኢትዮጵያ ከቻይና በመቀጠል ከሶሪያ እኩል የኢንተርኔት እና የሞባይል ተጠቃሚዎች ላይ ገደቦችን በመጣል በዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች ሲል ፍሪደም ሃውስ በሪፖርቱ ገልጿል።

ኢትዮቴሌኮም በበኩሉ ''የኢንተርኔትም ሆነ የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም'' ይላል።

የቻይና እና የሩሲያ መንግሥታት የረቀቁ መንገዶችን በመጠቀም የኢንተርኔት ላይ ውይይቶችን እና ተጠቃሚዎችን በመግታት የጀመሩት ተግባር አሁን በመላው ዓለም ተንሰራፍቷል ሲል ፍሪደም ሃውስ በሪፖርቱ ይገልጻል።

ኢትዮጵያ በፍሪደም ኦፍ ዘ ኔት (Freedom of the Net) ሪፖርት ''0=የኢንተርኔት ነጻነት ያለበት እንዲሁም 100=የኢንተርኔት ነጻነት የሌለበት'' በሚል መስፈርት ተመዝና 86 ነጥቦችን በማምጣት ከሶሪያ እኩል ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ከቻይና ቀጥላ ተቀምጣለች።

ሪፖርቱም ኢስቶኒያ እና አይስላንድ 6 ነጥብ በመያዝ በኢንተርኔት ነፃነት ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

ሪፖርቱ የተከናወነው በ65 ሃገራት ሲሆን ሰሜን ኮሪያ እና ኤርትራ በጥናቱ ውስጥ አልተካተቱም።

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎችንImage copyrightFREEDOM HOUSE

''የኢንተርኔትም ሆነ የሞባይል አገልግሎት በኢትዮጵያ ተዘግቶ አያውቅም። ከዚህ በፊት የ ኦቨር ዘ ቶፕ (Over The Top) የሚባለውን ፌስቡክ እና የመሳሰሉ የማሕበራዊ ሚዲያዎች መጠቀም የሚያስችለውን አገልግሎት ብሔራዊ ፈተና ሲኖር ለተወሰነ ጊዜ እናግዳለን እንጂ በሃገራችን ኢንተርኔት ተዘግቶ አያውቅም'' በማለት የኢትዮ-ቴሌኮም የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ አብዱራሂም ጨምረው እንደተናገሩት ፍሪደም ሃውስ የተሰኘው ድርጅት ከራሱ ፍላጎት ተነስቶ ያወጣው ሪፖርት ነው እንጂ እውነታውን የሚያሳይ አይደለም ብለዋል።

''ዓለም አቀፉ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ህብረት (ITU) እና አይሲቲ አፍሪካ (ICT Africa) የመሳሰሉ ተቋማት ናቸው የኛን መሰረተ ልማት የሚያውቁት እና ሊመዝኑን የሚችሉት እንጂ ይህ ሪፖርት ተዓማኒነት የለውም'' ሲሉ ተናግረዋል።

ፍሪደም ሃውስ ዓመታዊ ሪፖርቱን ''ማህበራዊ ሚዲያን በማዛባት ዲሞክራሲ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር'' በሚል ርዕስ ያወጣ ሲሆን በዋናነት ኢትዮጵያን በሚመለከት ካነሳቸው ነጥቦች መካከል፡

  • የኢትዮጵያ መንግሥት የመብት ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያ ክልል የሞባይል እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ይዘጋል
  • የማህበራዊ ሚዲያዎችን እና መተግበሪያዎች እንዳይሰሩ ያደርጋል
  • ፖለቲካዊ ይዘት ያለቸውን ድረ-ገጾች ዘግቶ ቆይቷል
ኢንተርኔት በኢትዮጵያ

ለአስር ወራት ያህል በስራ ላይ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማኅበራዊ ሚዲያ ተቃውሞ መደገፍን ጨምሮ ሌሎችንም መሰረታዊ የዜጎች መብቶች አፍኗል የሚለው ሪፖርቱ ራስን ሳንሱር የማድረግ እና ኃሳብን ከመግለፅ የመቆጠብ አዝማሚያዎች በአዋጁ ጊዜ ተጠናክረው ታይተዋል ሲል ይገልፃል፤ በርካቶች ኃሳባቸውን በኢንተርኔት መድረኮች ላይ በመግለፃቸው ታስረዋል፤ ሁለት ግለሰቦች ደግሞ ተከስሰው ተፈርዶባቸዋል በማለትም መንግስትን ይወነጅላል።

ሪፖርቱ ጨምሮም በ2008 ዓ.ም የወጣው የኮምፒውተር ወንጀሎች አዋጅ የመንግስትን በዜጎች ግንኙነት ጣልቃ የመግባት እና መረጃ የመሰብሰብ ስልጣን ማስፋቱን የኢንተርኔት ነፃነትን ከሚያዳክሙ ምክንያቶች አንዱ ነው ይላል።

በተጨማሪ በሃገሪቱ ውስጥ ደካማ የቴሌኮም መሰረተልማት መኖሩ፣ የቴሌኮም አገልግሎት በመንግሥት ቁጥጥር ስር ብቻ መሆኑ እና የቴሌኮም ፖሊሲዎች ተጠቃሚዎችን የሚገደቡ ሌሎች ምክንያቶች ናቸው ሲል በዝርዝር ሪፖርቱ ያስቀምጣል።

በኢትዮጵያ ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት እና የመረጃ ነጻነት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራ ለነበረው አርቲክል 19 (ARTICLE 19) ተቀጣሪ የነበረው እና በኢትዮጵያ መንግሥት ከሃገር እንዲወጣ የተደረገው ፓትሪክ ሙታሂ በሪፖርቱ ላይ ይህን አስተያየት ሰጥቷል

''በኔ ግምገማ የፍሪደም ሃውስ ሪፖርት በኢትዮጵያ ያለውን ትክክለኛ ገጽታ ያሳያል።''

"ሰዎች ኢንተርኔትን እና የሞባይል ግንኙነትን ለመደራጀት፣ ሃሳባቸውን ለመግለጽ እና ለመቀስቀስ ይጠቀማሉ ይህም የኢትዮጵያን መንግሥት ስለሚያሳስበው የማይፈልጋቸውን ድረ-ገጾች፣ የኢንተርኔት እና የሞባይል አገልግሎቶችን ማቋረጥ የተለመደ ነገር አድርጎታል" በማለት ፓትሪክ ያብራራል።

የሰሞኑ የኢትዮ-ቴሌኮም ምዝገባ ነፃነትን ይገድብ ይሆን?

ኢትዮ-ቴሌኮም፡ አንድ ወደፊት ሁለት ወደኋላ?

ፍሪደም ሃውስ እአአ1941 በዩናይትድ ስቴትስ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን በሰብዓዊ መብቶች፣ በዲሞክራሲ እና በፖለቲካ ነጻነቶች ዙሪያ የመብት ስራዎችን እና ጥናቶችን ያከናውናል።

እ.ኤ.አ በ2011 ከ1 በመቶ ትንሽ ብቻ ከፍ ብሎ ይገኝ የነበረው የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስርገት መጠን በ2016 ወደ 15 በመቶ ከፍ ቢልም እንዲሁም በተመሳሳዩ ጊዜ የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭት ከ16 በመቶ ወደ 51 በመቶ ቢያድግም አገሪቷ አሁንም ከዓለማችን እጅግ በአነስተኛ ደረጃ በኢንተርኔት የተያያዙ አገራት መካከል መገኘቷ አልቀረም።

ሪፖርቱ የተለያዩ ጥናቶችን በማጣቀስ ኢንተርኔት በጣም ውድ ከሆኑባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ያወሳል።

አንድ ጥናት እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያዊያን በተንቀሳቃሽ ስልክም ሆነ በኮምፒውተር ላይ ኢንተርኔትን ለማግኘት በአማካይ በወር 85 የአሜሪካ ዶላር ያወጣሉ፤ የተሻለ የኢንተርኔት ስርጭት አለባቸው በሚባሉት ኬንያና ኡጋንዳ ግን ይህ ወጭ በአማካይ ከ30 የአሜሪካ ዶላር የማይበልጥ ነው።

ፍለጋ
Categories
Read More
Uncategorized
በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት ስራ ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶች ተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት ሊሰጡ ነው
በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶችን ለተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት መስጫነት እያዘጋጃቸው መሆኑን የአዲስ አበባ...
By Dawitda 2017-12-22 09:06:30 0 0
Uncategorized
አንጀሊና ጆሊ እና ሌሎችም 
(አሌክስ አብርሃም) ከሰሞኑ አንዲት አሜሪካ የምትኖር ጠንቋይ የሴቶችን ከንፈር በማየት ብቻ ስለባለከንፈሮቹ ህይዎት ዘክዝኬ እናገራለሁ ማለቷን ተከትሎ...
By binid 2017-11-26 06:31:13 0 0
Uncategorized
ዘውዲቱ ሆስፒታል 5 የኩላሊት እጥበት መስጫ መሳሪያዎችን በወቅቱ አለመግዛቱ ችግር ፈጥሮብናል
ዘውዲቱ ሆስፒታል 5 የኩላሊት እጥበት መስጫ መሳሪያዎችን በወቅቱ አለመግዛቱ ችግር ፈጥሮብናል-ታካሚዎች ዘውዲቱ ሆስፒታል ከአንድ ዓመት በፊት ለአምስት...
By binid 2017-11-26 06:52:11 0 0
Other
ĐỜI CAO GIÁ TỐT: Xe Nâng Điện 1 Tấn NICHIYU FBRM10N-80 năm sx 2021
Nâng cao hiệu suất làm việc, giảm thiểu chi phí vận hành và bảo...
By xenangaz 2025-04-17 07:39:51 0 0
Other
MINI: Xe Nâng Điện UNICARRIERS J1B1L09 (FB9) 900Kg nhỏ gọn tiện dụng
Bạn đang tìm kiếm một chiếc xe nâng điện mạnh mẽ, linh hoạt và...
By xenangaz 2025-04-16 07:05:21 0 0