መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው __

0
0

ወጣቱ የአንድን አርሶ አደር ቆንጆ ልጃገረግ ማግባት ፈልጓል፡፡ እናም ወደ አባቷ ቀርቦ ፍቃዳቸው ይሆን ዘንድ ጥያቄውን አቀረበ፡፡ አባት ልጁን ከእግር ጥፍሩ እስከ እራስ ፀጉሩ እየተመለከቱት አንድ ተግባር ሰጡት፡፡ “ናስኪ ልጄ! ሂድና እዛ እመስኩ መሐል ቁምና እነዚህን ሦስት ኮርማዎች ተራበተራ እለቃቸዋለሁ፡፡ ከሦስቱ ኮርማ ያንደኛውን ኮርማ ጅራት የያዝክ እንደሁ ልጄን እድርልሃለሁ፡፡ ታገባታለህ” አሉት፡፡ ወጣቱ በታዘዘው መሰረት ከግጦሹ ሜዳ ሁኖ መጠባበቅ ጀመረ፡፡ የኮርማዎቹ በረት እንደተከፈተ ትልቅ ኮርማ ከዚህ በፊት አይቶት የማያውቅ ሻኛ የተሸከመ ኮርማ ሲመጣ ተመለከተው፡፡ ወጣቱ “ይሄስ ይለፈኝ የቀጣዩን ኮርማ እይዘዋለሁ” ብሎ ወሰነና አስተላለፈው፡፡ ሁለተኛው ሲመጣ የሚያየውን ማመን አልቻለም፡፡ ከመጀመሪያው በላቀ ግዙፍ ሆነበት፡፡ “የሚቀጥለው ኮርማ (ሦስተኛው ማለቱ ነው፡፡) የፈለገውን ይሁን እሱን እይዘዋለሁ” በማለት ይሄኛውን ወደ ጥግ በመሸሽ አሳለፈው፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ የኮርማዎች በር ሲከፈት ወጣቱ ፈገግ አለ፡፡ ከበረቱ የወጣው ኮርማ ደከም ያለ ነበር፡፡ ወጣቱ የኮርማውን ጅራት ለመያዝ እንዲያመቸው አቋቋሙኝ አስተካክሎ ጠበቀው፡፡ ኮርማው እሱጋ ሲደርስ ዘሎ ወጣበት ነገር ግን የኮርማውን ጅራት መያዝ አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ኮርማው ጅራተ ቆራጣ ስለነበር ሙሉ ጅራት አልነበረውምና፡፡

ሕይወት በመልካም አጋጣሚዎች (Opportunities) የተሞላች ናት፡፡ አንዳንዱን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም ቀላል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ አስቸጋሪ ነው፡፡ ነገር ግን የተሻለ ይገኛል በማለት እጅ የገባን መልካም እድል ማሳለፍ የማይመጣን እንደመጠበቅ ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም ያመለጠ መልካም አጋጣሚ መልሶ እራሱ አይመጣም፡፡ ይህ ማለት ግን ሌላ መልካም አጋጣሚ የለም ማለት አይደለም፡፡ የከፋ ወይም የተሻለ ይኖራል፤ይመጣልም፡፡ እራሱ የበፊቱ ግን አይመጣም፡፡ አንዴ ካመለጠ መልሶ እንደማይገኝ ሲናገሩ መልካም አጋጣሚ ቁንጮ ነው ይሉታል፡፡ ቁንጮ ልጆች በአብዛኛው በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ፊት ለፊት ላይ ቁጢጥ አድርገው የሚተውት የፀጉር አቆራረጥ ነው፡፡ መልካም አጋጣሚም እንደመጣ ፊት ለፊት ካልይዙት ዘወር ካለ መላጣ ስለሆነ መያዝ አይቻልም ሲሉ ነው ቁንጮ ነው ያሉት፡፡ ስለሆነም ሁሌም ከፊትህ የመጣን መልካም አጋጣሚ ይዋል ይድር ሳትል ተጠቀምበት ነው መልዕክቱ፡፡

ምንጭ፡ NEVER MISS FIRST OPPORTUNITY!

(#ምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)

17-09-2007 ዓ.ምhttps://www.facebook.com/groups/bookforall/?fref=nf

Like
1
Search
Categories
Read More
Dance
How Does an Expanding Air Shaft Influence Roll Control?
In modern production environments, calm and controlled roll handling often determines how...
By Zanetruese Zanetruese 2025-12-18 02:33:06 0 0
Uncategorized
በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት ስራ ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶች ተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት ሊሰጡ ነው
በመዲናዋ በእርጅና ምክንያት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ አንበሳ አውቶቡሶችን ለተንቀሳቃሽ የንግድ አገልግሎት መስጫነት እያዘጋጃቸው መሆኑን የአዲስ አበባ...
By Dagmawisol 2017-12-22 09:06:30 0 0
Uncategorized
ከነጠላው ስር !!
(አሌክስ አብርሃም) የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ ሁሉ በግ መስሎን ተበላን ጓዶች !!እኛ ኢትዮጲዊያን በተለይ በዚህ ሰአት ‹‹ፈጠራ...
By Binid Dre 2017-11-26 06:32:11 0 0
Uncategorized
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ...
By Andualem Buketo 2017-11-12 15:13:23 0 0
Uncategorized
Macaafa Qulqulluu!!
Ergaa jireenya dhugaa fi Amantii.
By Milkias Meskele 2017-11-15 04:43:20 0 0