የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)

0
0

የአራዶች ወግ (ክፍል አንድ…..)
(ማስጠንቀቂያ….ይህ ጽሁፍ ልክ እንደ እሁድ ረዥም ስለሆነ ስራ ያለበት ሰው ከእሁድ ውጪ እንዲያነበው አይመከርም)

ሰላም ነው ጋይስ?! ዛሬ እና በተከታታይ በሚመጡት ቀናት ስለ አራዶች እንጫወታለን፡፡አቦ አራዳ ሳይ ደስ ይለኛል እኮ!
ግራጫ ቃጭሎች ላይ ያለው "መዝጌ" እንዴት አራዳ እንደሚወድ ትዝ አላችሁ?!…."እንግዲህ አራዳ ማን ነው?!" ነው ዋናው ጥያቄ መቼም!...
"አራዳ" ጥንታዊ የግእዝ ቃል ሲሆን በግርድፉ "የራሱን ጥቅም ለማስጠበቅ ቀጥ ብሎ የሚቆም" እንደማለት ሲሆን የቃሉም አመጣጥ እንስሳት ሁሉ አጎንብሰው ሲሄዱ በነበረበት በኋለኛው ዘመን መጀመሪያ ቀጥ ብላ ከሄደችው "አርዲ" ስም ሲወራራስ የመጣና ኋላ ላይ ኦሮሞዎች እንደልማዳቸው ግእዝኛውን አጣመውት ወደ አማርኛው "አራዳ" ያመጡት ቃል ነው፡፡*
*ምንጭ፡..አንዱአለም በውቀቱ ገዳ 1986 ፡የአራዳ ታሪክ ከየት ወዴት? አደስአበባ ዩኒቨርስቲ ያልታተመ(አዳም ረታ ስታይል)
እስቲ በክፍል 1. አንዳንድ አራዶችን እንይ፡፡
የመጀመሪያው አራዳ… በነገው እለት ስራ እለቃለሁ አሉ የተባሉት አቶ አባዱላ ገመዳ ናቸው፡፡

እኚህ ሰው ለእኔ የገባቸው "አራዳ" ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ ገና ያኔ ወደ ኦህዴድ ፖለቲካ የፊት መስመር ሲመጡ (በ1993 አካባቢ ማለትም እነ ሀሰን አሊ ..እነ አልማዝ መኮ እነ ሱሌማን ደደፎ እነ ሂሩት ገቢሳ…አስራት ሃይሉ…አለማየሁ አቶምሳ..ደግፌ ቡላ …ዳባ ደበሌ ፣.ግርማ ብሩ ….ዶ/ር ነጋሶ…ወዘተ ዋና አክተር በነበሩበት የኦህዴድ የእንቅልፍ ዘመን …መሌ እንኳን "ኦህዴድ ኢዝ ኖት አ ዲማንድንግ ኦርጋናይዜሽን" ብሎ ሙድ በያዘባቸው ዘመን(የዛሬን አያድርገውና "አረ የዲማንድ ያለህ!?" ሁላ ተብለው ነበር እኮ) …እነ ሰለሞን ጢሞ ኦህዴድን በምግዚትነት በሚያስተዳድሩበት ዘመን ..ኦህዴድ እነ አብዲ ለሜሳ "ኦህ…ዴድ!" በነበረበት ዘመን )…እኚህ ያራዳ ልጅ(አቶ አባዱላ) ቀደም ብለው ከኦህዴድ በከፍተኛ ግምገማ ስንትና ስንት ግፍ የሰሩ እና የተባረሩ ብለውም የታሰሩ 189 ባለጌ እና ዋልጌ ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹን ከእስር በመፍታት ጭራሽም ወደ ስልጣን በመመለስ "አቦ የአራዳ ልጅ ከየት መጣ!?" የተባሉ ደግ የደግ መጨረሻ ነበሩ፡፡የምድር ጦር አዛዥ ሆነው ዶ/ር ነጋሶ "ስጣቸው" ተብለው የሰጧቸውን የሜጀር ጄነራልነት ማእረግ "አቦ ይቅርብኝ ስሜ ብቻውን ማእረግ ነው" ብለው የመለሱ("አባዱላ" በኦሮሚፋ የጦር ማእረግም መሆን ይችላል) አራዳም ናቸው፡፡ አባዱላ ማእረጋቸውን ብቻም ሳይሆን ሙስና ሊባል በሚችል መልኩ በእጃቸው ያስገቡትንም የቦሌ ቦታቸውን(ቤታቸውን) ኢሃዲግ ሰፈር ባልተለመደ መልኩ "ለትግል አልተመቸኝም" ብለው የመለሱ እና በተደጋጋሚ የተለያዩ ነገሮችን በመመለሳቸው ""መለስ" ማለትስ ይሄን ነበር!" የተባለላቸው አሁንም የፓርላማውን መዶሻ ለመመለስ ሃሳብ ያቀረቡ አራዳም ናቸው፡፡ 
እንግዲህ ከላይ በጠቀስኩት ጥናት ውስጥ እንደተገለጸው ከሆነ የአራዳ ልጅ የነገሮችን አካሄድ አይቶ እና ገምግሞ የሚጠቀም ከሆነ ቶሎ ይጠቀማል አልያም ነገሮች ካላማሩት "ተቄ" ይላል እንጂ ዝም ብሎ አይገግምም*
*አራዳ ከየት ወዴት..(ዝኒ ከማሁ)
……ምድርጦር ነበሩ …"አቦ ይሄ ነገር አይነፋም!" ብለው ኦሮሚያ መስተዳድር መጡ ..ይሄም ሰለቻቸው …(እንግዲህ እዚህ ጋር "ሰለቻቸው" ስል ስልቸታው የግላቸው ብቻ አለመሆኑን እና እዚህ ጋር አንድ ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልገውን ጠቅላይ ሚኒስቴር ስሜትንም ሊጨመር እንደሚችል አራዶች ታሳቢ እንደምታደርጉ አልጠራጠርም)…ከዛም ወደ አፈ ጉባኤነት መጡ….በአጋጣሚ እሳቸው በነበሩበት ፓርላማ አንድም ተቃዋሚ በመጥፋቱ ፓርላማው ወደ "ፔንሲዮንነት" ተቀይሮ አንዳንዶች በሃላል እንቅልፋቸውን ሲለጥጡ እና በመሃል እየነቁ አጠገባቸው ካለ ሰው ጋር "እስቲ ህልሜን ፍታልኝ" አይነት ጫወታ እየተጫወቱ ቢያስጎመጇቸውም (ያው የእሳቸው ቦታ ለእንቅልፍ የማይመች መሆኑ ውስጥ ውስጡን ሲያቃጥላቸው እንደኖረ ፊታቸው ላይ ያለው ማዲያትም ያስተውቃል) እንኳ ሰውየው ግን አንዴ አራዳ አድርጎ ፈጥሯቸዋልና አባላቱን ላለመረበሸ ህግ ሲጸድቅ እንኳ ጠረጴዛውን የሚመቱት በለሆሳስ ነበር፡፡ ታዲያ ዛሬ ምን ታይቷቸው ነው ስራ የሚለቁት?!
አንድ ግዜ ይቅርታ ኋላ ላይ እንመለስበታለን፡፡
አሁን የ7 ሰአቱን ዜና እያየሁ" ደህዴን/ኢሃዴግ የተመሰረተበትን 25 ኛ አመት በአል ምክንያት በማድረግ ለተመሰረተበት ቦታ (ታህታይ ቆራሮ የሚባል ትግራይ ውስጥ የሚገኝ) አንድ ባለ12 ሚሊዮን ብር ት/ቤት በስጦታ ሰርቶ ሰጥቷል" ይላል፡፡ ይመቸው ደህዴን! አራዳ ማለት እንደዚህ ነው፡፡ከደርግ ጋር ይደረግ የነበረው ጦርነት አስከፊ መሆኑን አየ…አንድ 16 አመት ዳር ይዞ ጠበቀ…ከዛ ማን እንደሚያሸንፍ በደንብ ካረጋገጠ በኋላ (የተቋቋመው ታህሳስ 1983 ነው) (ልክ አክሽን ፊልም ላይ አክተሩ ተቀጥቅጦ ተራው ደርሶ ጠላቱን ቀጥቅጦ ሲጥለው የፖሊስ መኪና በሚመጣበት ሰአት ላይ ዘሎ "የስምጥ ሸለቆ ታጋዮች" ምናምን ብሎ የጦርነት ሳይሆን የሆነ የአሳሽ (ሪሰርቸር) ቡድን ስም ይዞ ጆይን አደረገ፡፡አቦ ያራዳ ልጅ! ዜናው ላይ የሚታዩት አቶ ተስፋዬ በልጅጌ የደህዴን የሆነ ነገር ሃላፊ ስለ ልማት ሲያወሩ ሌሎች "ታጋዮች" ደግሞ በተሳተፉበት የአራት ወራት ውግያ እንዴት የደርግን እድሜ እንዳሳጠሩት ሲያወሩና ስለተሰዉ ጓዶቻቸው ሲያወጉ በእውነት ከዚህ በላይ የአራዳ ልጅ ከየት ሊመጣ ብዬ ፈገግ ብያለሁ፡፡ያኔ እኮ (ደህዴን ጆይን ሲያደርግ) ጦርነቱ ከመገባደዱና ሰራዊቱ ተስፋ ከመቁረጡ የተነሳ የደቡብን ባላውቅም በሰሜን እንዲህ ይባል ነበር……
"….እነ እንቁላል ቁርሱ…. እነ ብር ትራሱ
ሃሙሲት ሲተኮስ…… ባህርዳርን አልፈው ዳንግላ ደረሱ
ደህንነት በአህያ……… ኢሰፓ በፈረስ
እሽቅድድም………. ያዙ ማርቆስ ለመድረስ"
ሃሃሃ አንዲ ማኛ ያኔ እንደ መዝጌ(አዳም ረታ) ዳሸን ተራራ ጫፍ ላይ ቁጭ ብላ ዋልያዋን እየኮመኮመች("ዋልያ" ስል ያው ሊትራሊ ነው) የታሪክ "ጉቤ" ነበረች፡፡ስንቱን አራዳ አይታለች!….አራዳዋ መንጌ ነገሩ ሁሉ እንዳላማረ አውቃ ወደ ሀራሬ ላሽ ልትል ስትል ምንም ቢሆን አራዳ ናትና ጓደኖቿን የወጪ ማለት ፈልጋ ግንቦት 11 ቀን 1983 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ከሁለት አመት በፊት በእነ ጄነራል ደምሴ ቡልቶ የተደረገባትን መፈንቅለ መንግስት የከሸፈበት ሁለተኛ አመት ተጋበዙልኝ ብላ ቤተመንግስት ስታምነሸንሻቸው ከሁለት ቀን በኋላ በዳሽ ፋይፍ አይሮፕላን ወደ ሃራሬ እብስ ልትል እንዳሰበች ከታሪክ ጉቤዋ አንዲ ማኛና እና ከመንጌ ውጪ ማን ያውቅ ነበር?!……..
መቶ ፐርሰንት ኢሃዲግ በሆነ ፓርላማ ውስጥ አፈጉባኤ መኖሩ ምንም ጥቅም የለውም ተብሎ የስራ መደቡ ሊሰረዝ መሆኑን አስቀድመው በመስማታቸው ሳይቀድሙኝ ልቅደም ብለው ስፒከሩ መልቀቂያ ያስገቡ ቢሆንስ? ይህንንስ ከጉቤዋ አንዲና ከአባዱላ ውጭ ማን ያውቃል?!
በሉ መልካም ሰንበት
ሁላችሁም ይመቻችሁ

Search
Categories
Read More
Shopping
Exquisite Hand Work Sherwani: Timeless Craftsmanship and Elegance
An exquisite hand work sherwani is a masterpiece that captures the essence of...
By Stylish12 2024-10-31 10:46:00 0 0
Uncategorized
ዳይ እየተሰዳደብን ...
«ዘውድአለም ታደሰ» ሰው ሁሉ የፖለቲካ ተንታኝ ሆኖልኛል። ጭራሽ እየሩሳሌምን ለእስራኤል አሳልፈን አንሰጥም! አንሰጥም!...
By Zewdalem 2017-12-07 12:34:35 0 0
Uncategorized
መርከቧ በባሕሩ ላይ፣ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ላይ?
(ዳንኤል ክብረት) ታዋቂው ሩሲያዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ባለሞያ ዶክተር ሰርጌይ ላቭሮቭ ‹Reformation in the...
By binid 2017-11-25 13:23:15 0 0
Uncategorized
_ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር
__ከምድር ሁሉ ሃብታሙ ስፍራ……..መቃብር “The graveyard is the richest place on earth,...
By Seller 2017-12-01 08:05:09 0 0
Uncategorized
የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ ወሰደ
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ በድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።በዚህ መሰረት የድርጅቱ ሊቀ...
By Seller 2017-11-28 08:05:40 0 0