አንዱ ለፍቅረኛዉ የ 100 ብር ካርድ መላክ ይፈልግና
በአንድ ቁጥር ስህተት ለማያዉቀዉ ሰዉ የካርዱን ቁጥር
ቴክስት ያደርጋል:: ቆየት ብሎም መሸወዱን ሲያዉቅ
የተበላዉ ገንዘብ ንድድ አደረገዉ:: በሌላ ቁጥር ደዉሎ
የስልኩ ባለቤት ወንድ እንደሆነ ሲያዉቅ ለማስመለስ መላ
ይዘይዳል:: እናም እንዲህ የሚል ቴክስት ላከለት...
' ሰላም ወዳጄ የጨለማዉ ማህበር መሪ ነኝ: ደህና
እንደሆንክ አዉቃለሁ:: ከትንሽ ደቂቃ በፊት የመቶ ብር
ካርድ ልኬልህ ነበር:: ካርዱ የላኩልህ ዛሬ ከሌሊቱ ዘጠኝ
ሰአት ላይ "የሰይጣን መንፈስ አቀባበልና ልዩ የጨለማዉን
ንጉስ የማወደስ" ስነስርአት በምስጢር ይካሄዳል::
በቅድሚያ ለዚህ እድል በመታጨትህ እንኳን ደስ ያለህ
ልልህ እወዳለሁ::
የተላከልህ ካርድ በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ እንድትገኝ
ለትራንስፖርት ይሆንሀል:: የካርድ ቁጥሩን ሽጠዉና
በነገርኩህ ሰአት እንጦጦ ጫካ እንድትመጣ ይሁን::
ወደ ሀብት ጉዞህ አልጋ በአልጋ ይሆናል:: መኪና ቤት እና
ሱቅ ወዲያዉ ይሰጥሀል የአባልነት ዉል በደምህ ነዉ
የምትፈፅመዉ:: ቃል ኪዳኑን ስትገባ የቅርብ አንድ ሰዉ
ይሞታል::
እንደዉ ምን አልባት ግን በሀሳቡ ካልተስማማህ አሁኑኑ
የተላከዉን መቶ ብር መልስ አለበለዛ ትቀሰፋለህ!"
ብሎ ይልካል... ትንሽ ቆይቶ ስልኩ ጢጢዉ አለና
የመጣለትን መልእክት ቢከፍተዉ::
" እንኳን አብሮ ደስ ያለን!
እዉነት ለመናገር ለዚህ በመታጨቴ ክብር ተሰምቶኛል::
አሁን ባለዉ ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ላይ እንዲህ ያለ
እድል ሲመጣ አይን አይታሽም:: እባክህን ጓደኛዬም አብሮ
መምጣት ይፈልጋልና ፍቀድለት..."
አንዱ ለፍቅረኛዉ የ 100 ብር ካርድ መላክ ይፈልግና በአንድ ቁጥር ስህተት ለማያዉቀዉ ሰዉ የካርዱን ቁጥር ቴክስት ያደርጋል:: ቆየት ብሎም መሸወዱን ሲያዉቅ የተበላዉ ገንዘብ ንድድ አደረገዉ:: በሌላ ቁጥር ደዉሎ የስልኩ ባለቤት ወንድ እንደሆነ ሲያዉቅ ለማስመለስ መላ ይዘይዳል:: እናም እንዲህ የሚል ቴክስት ላከለት... ' ሰላም ወዳጄ የጨለማዉ ማህበር መሪ ነኝ: ደህና እንደሆንክ አዉቃለሁ:: ከትንሽ ደቂቃ በፊት የመቶ ብር ካርድ ልኬልህ ነበር:: ካርዱ የላኩልህ ዛሬ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰአት ላይ "የሰይጣን መንፈስ አቀባበልና ልዩ የጨለማዉን ንጉስ የማወደስ" ስነስርአት በምስጢር ይካሄዳል:: በቅድሚያ ለዚህ እድል በመታጨትህ እንኳን ደስ ያለህ ልልህ እወዳለሁ:: የተላከልህ ካርድ በዚህ ልዩ ዝግጅት ላይ እንድትገኝ ለትራንስፖርት ይሆንሀል:: የካርድ ቁጥሩን ሽጠዉና በነገርኩህ ሰአት እንጦጦ ጫካ እንድትመጣ ይሁን:: ወደ ሀብት ጉዞህ አልጋ በአልጋ ይሆናል:: መኪና ቤት እና ሱቅ ወዲያዉ ይሰጥሀል የአባልነት ዉል በደምህ ነዉ የምትፈፅመዉ:: ቃል ኪዳኑን ስትገባ የቅርብ አንድ ሰዉ ይሞታል:: እንደዉ ምን አልባት ግን በሀሳቡ ካልተስማማህ አሁኑኑ የተላከዉን መቶ ብር መልስ አለበለዛ ትቀሰፋለህ!" ብሎ ይልካል... ትንሽ ቆይቶ ስልኩ ጢጢዉ አለና የመጣለትን መልእክት ቢከፍተዉ:: " እንኳን አብሮ ደስ ያለን! እዉነት ለመናገር ለዚህ በመታጨቴ ክብር ተሰምቶኛል:: አሁን ባለዉ ወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ላይ እንዲህ ያለ እድል ሲመጣ አይን አይታሽም:: እባክህን ጓደኛዬም አብሮ መምጣት ይፈልጋልና ፍቀድለት..."
0 Comments 0 Shares