ከነጠላው ስር !!
(አሌክስ አብርሃም)
የበግ ለምድ የለበሰ ቀበሮ ሁሉ በግ መስሎን ተበላን ጓዶች !!እኛ ኢትዮጲዊያን በተለይ በዚህ ሰአት ‹‹ፈጠራ ማለት›› የሰውን ፈጠራ ነጠላ ማልበስ እየመሰለን መጥቷል !ነጠላና ጥበብ የለበሰው ሁሉ የእኛ ባህል የእኛ ፈጠራ ይመስለናል ! ምን አይነት በሽታ ነው ይሄ ? ምናይነትስ የአእምሮ መደፈን ነው ….ግርምኮ ነው የሚለው ! እንግዲህ ነጠላ እያለበስን ያስገባነውና ነጠላችንን አስጥሎ እርቃን ያስቀረንን ቀበሮ እንቁጠር ካልን ቁጥር ስፍር የለውም …
ሶሻሊዝም ነጠላ ለብሶ መጣ … እልል ብለን ተቀበልነው እርስ በእርስ...