አይኔን በሌላ ሰው አይን ሳየው!
(አሌክስ አብርሃም)
ፍቅረኛየ በየቀኑ እንዲህ ትለኛለች“ አብርሽ ‹የ› ” በቃ ‹ የ› ከጨመረች ጥያቄዋ ምን እንደሆነ አውቀዋለሁ …ቢሆንም እንደአዲስ ነገር ለመስማት “ወይየ” እላለሁ“በናትህ ልጅ እንውለድ ” የሄው አላልኳችሁም ..አቤት ልጅ ስትወድ !“የኔ ማር ልጅ ምን ይሰራልሻል ?”“ልጅ እኮ በቃ…ምን ልበልህ …በቃ …..” ቃል ያጥራታል ትንፋሽ ሁሉ ያጥራታል የራሷን ጡቶች ጥብቅ አድርጋ አቅፋ አይኖቿን አንዴ ወደላይ አንዴ...