ሀገራዊ ዕብደት
(ዳንኤል ክብረት) ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ በቤታችን ደኅና መጥፋቱ ነወይ የሚል የበገና ዘለሰኛ አለ፡፡ አሁን ያለችውን ሀገራችንን ቀድሞ ያየ ደራሲ መሆን አለበት የገጠመው፡፡ በሀገሪቱ ውስጥ ጤነኛ አካል የጠፋ ይመስላል፡፡ የገዛ ወገኑን አባርሮ የሚፎክር ወገን፣ ሕዝብ እንዳይሰደድ የሚያደርግ አሠራርና አስተዳደር መዘርጋት ሲገባው ሲያባብስ ኖሮ ሕዝብ ሲሰደድ መጠለያ ድረስ ሄዶ የሚጎበኝ ባለ ሥልጣን፣ የሀገሩን ሀብትና ንብረት አቃጥሎ በኩራት የሚደነፋ ጎረምሳ፤ ሕዝብን እያዋረደና እየተሳደበ መግለጫ የሚሰጥ የክልል ሹም፤ ነገሩ ሁሉ እንዳይሆን እንዳይሆን ሲበላሽ እያየ መንገዱን ለመመርመር የማይፈልግ መንግሥት፤ ሀገር...
0 Comments 0 Shares