መርከቧ በባሕሩ ላይ፣ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ላይ?
(ዳንኤል ክብረት)
ታዋቂው ሩሲያዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ባለሞያ ዶክተር ሰርጌይ ላቭሮቭ ‹Reformation in the Orthodox Perspective> በተሰኘውና እኤአ በ1998 ባወጣው መጽሐፉ ላይ በሕንድ፣ በጆርጅያና በዩክሬይን የተደረገውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ባጠናበት መጽሐፉ ላይ ‹በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውስጥ ዋናው ጥያቄ - መርከቧ በባሕሩ ላይ ትሂድ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ውስጥ ይሂድ የሚለው ነው› ይላል፡፡ ለዚህ ሐሳብ መነሻ ያደረገው በሦስቱ ሲኖፕቲክ ወንጌሎች ላይ በማቴ.8፥23፤ሉቃ. 8፥22 እና በማር. 4፥35 የተጻፈውን ታሪክ ነው፡፡ ...