በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ትኩረት ሊደረግባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር አያሌ ዜጐችን በማታ፣ በክረምትና በእረፍት ቀናት ተምረው በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ማስቻሉ በጥናት ተደርሶበታል፡፡ይሁን እንጂ የተከታታይ ትምህርት አሰጣጡና ተመራቂዎች ጥራትና ውጤታማነት ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች ይነሣሉ፡፡
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሮች ከትምህርት ተቋማቱ ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴርም ሆነ በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ የሚደረግላቸው ክትትል ዝቅተኛ ነው፡፡
የተከታታይ ትምህርት መርሃ-ግብሩን ጥራት ከሚፈታተኑት ውስጥ የትምህርት መስኮች አግባብ ያለው ጥናት ሳይደረግባቸው መከፈትና ለሚሰጡ ትምህርቶች በቂ መርጃ...