ተመልሰን ሻሸመኔ!?
ተመልሰን ሻሸመኔ!?፡ይሉ ነበር የጓደኛዬ እናት፡፡ቡና እቤታቸው እየተፈላ እሳቸው አሪፍ ወሬ እያወሩልን ሰብበሰብ ብለን ከምናደምጠው መካከል አንዳችን የወሬው መጀመሪያ ላይ የተገለጸ ሀሳብ ድጋሚ ስንጠይቃቸው በስጨት ይሉና "ተ መ ል ሰ ን ሻ ሸ መኔ !?" ይላሉ ፡፡ እና የሳቸውን ንግግር ዛሬ ለምናወራው ወሬ ርእስ አድርጌዋለሁ፡፡ለምን? ምክንያቱን ከአራት ገጽ ንባብ በኋላ ታገኙታላችሁ…..ያዙ እንግዲህ፡እሺ ጋይስ ዛሬ አውዳመቱ እንዴት ነበር!? ኢሬቻው በሰላም ስላለፈ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል..ፎቀቅ ለማይል ፖለቲካችን አንዲትም ነፍስ እንደዋዛ ማለፍ የለባትም የሚለው የሁል ግዜ መርሄ ነው፡፡ "ሰው ለምን...