ተመልሰን ሻሸመኔ!?

0
0

ተመልሰን ሻሸመኔ!?

ይሉ ነበር የጓደኛዬ እናት፡፡ቡና እቤታቸው እየተፈላ እሳቸው አሪፍ ወሬ እያወሩልን ሰብበሰብ ብለን ከምናደምጠው መካከል አንዳችን የወሬው መጀመሪያ ላይ የተገለጸ ሀሳብ ድጋሚ ስንጠይቃቸው በስጨት ይሉና "ተ መ ል ሰ ን ሻ ሸ መኔ !?" ይላሉ ፡፡ እና የሳቸውን ንግግር ዛሬ ለምናወራው ወሬ ርእስ አድርጌዋለሁ፡፡ለምን? ምክንያቱን ከአራት ገጽ ንባብ በኋላ ታገኙታላችሁ…..ያዙ እንግዲህ

እሺ ጋይስ ዛሬ አውዳመቱ እንዴት ነበር!? ኢሬቻው በሰላም ስላለፈ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል..ፎቀቅ ለማይል ፖለቲካችን አንዲትም ነፍስ እንደዋዛ ማለፍ የለባትም የሚለው የሁል ግዜ መርሄ ነው፡፡ "ሰው ለምን አልሞተም?" የሚለውን እና "በአሉ እንዴት በሰላም ተጠናቀቀ?" የሚለውን ለመመለስ የባለፈውን አይነት "ሲምፕል ሎጂክ" መጠቀም ያሻል፡፡እንግዲህ በዘንድሮ እሬቻ እና በአምናው እሬቻ መካከል ያለው መሰረታዊ ልዩነት በዘንድሮው እሬቻ በስፍራው የታጠቁ የጸጥታ ሃይሎች እና የኦህዴድ ካድሬዎች አለመኖር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ሎጂክ መሰረት ለአምናው የሰው ህይወት መጥፋት በቀጥታ ተጠያቂ ማነው ማለት ነው?! ከዚህስ ነገር መንግስት ምን ይማራል!? "ምንም" ያላችሁ ትክክል ናችሁ፡፡እኛ ሀገር መንግስት ያስተምራል እንጂ አይማርም፡፡አንዲ ማኛ ዛሬ በበአሉ ላይ ስትታደም ደህንነቷ የተረጋገጠ እንዲሆን ሶስቱን የ"መ" ህጎች ተጠቅማለች… …. የመጀመሪያው "መ" ያው "መልበስ" ሲሆን በጥዋት ተነስቼ ባለፈው ለጓደኛዬ ሰርግ የገዛሁትን ምርጥ የኦሮሞ የባህል ልብስ ለበስኩ፡፡ሁለተኛው "መ" ደግሞ "መረጋጋት" ብዬ የሰየምኩት ስትራቴጂ ሲሆን ስትራቴጂው የሚያመላክተው አምና በተፈጠረውም ሆነ በሌሎች ተጓዳኝ ነገሮች ባለመረበሽ በአሉን ተረጋግቶ ማክበርን ነው፡፡በዚህኛው መርህ መሰረት ስሜቴ ሳይረበሽ በባህል ልብሴ ተውቤ አምሮብኝ ከቤቴ ወጥቼ መኪናዬ ውስጥ ገባሁ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ ሶስተኛው እና ለደህንነቴ ወሳኝ የሆነው "መ" ደግሞ በአጭሩ "መቅረት" ብዬ የሰየምኩት ስትራቴጂ ሲሆን መኪናዬ ሳሪስ ጋር ስትደርስ መሪ በመሸብለል ጓደኞቼ ያሉበትን ቦታ ጠይቄ ጃምቦዬን እየለጋሁ ጉዳዩን በፌቡ ስከታተል ውያለሁ፡፡ያለምንም ማወላወል በጀግንነት በአሉን በስፍራው ተገኝታችሁ ያከበራችሁ ወገኖቼ ለእኔ ጀግኖቼ ናችሁ ….ለማለት ነው አመሰግናለሁ፡፡
፡ 
እሺ ምን አዲስ ነገር አለ ጋይስ!? "ኢቲቪ ለምን እሬቻን ከስፍራው አልዘገበውም !?"የሚሉ ቅሬታዎችን እዚህም እዛም እየተመለከትን ነው፡፡እንግዲህ ኢቲቪን ከእኔ በላይ የሚከታተለው ሰው መቼም የለም!..ሎል….ከልምድ በመነሳት ኢቲቪ ለጉዳዩ ትኩረት ያልሰጠው ከተሳታፊዎች ቁጥር አንጻር ነው እንዳንል እንኳን በሚሊዮኖች የሚሳተፉበትን በአል ይቅርና ከዚህ በፊት ከ500 የማይበልጡ ሰዎች የተሳተፉበትን የፊልም ምርቃት በቀጥታ ከብሄራዊ ትያትር ሲያስተላልፍ እናውቀዋለን…."ከእንትን አንጻር ነው" እንዳንል ..ከዚህ ቀደም "እንትን በሆነበት" ሁኔታ "እንትን ሲል እናውቀዋለን"…ስለዚህ ምንድነው!?....አንዱ ፖሲቢሊቲ "ዳውን ዳውን ወያኔ" የሚሉ ድምጾች ከህዝቡ ሊመጡ ስለሚችሉ ይሄን በቲቪ ላለማስተላለፍ ነው የሚለው ነው፡፡ይህም ቢሆን በአደጉት ሀገራት እንደ "fuc*you" አይነት የብልግና ቃላት በቴሌቪዥን ሊሰሙ ሲሉ "ቢኢኢጵ " የሚል ድምጽ በማስተላለፍ ሃሳቡ እንዳይሰማ እንደሚያደርጉት ይሄንኑ ዘዴ "ዳውን ዳውን ወያኔ" የሚለው ቃል ለማፈን መጠቀም ይቻል ነበር፡፡በእርግጥ ይህን ዘዴ ኢቲቪ ልጠቀም ብሎ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ከእሬቻ በቲቪ የሚተላለፈው ፕሮግራም ከጥዋት እስከ ምሳ ሰአት ድረስ ይሆን የነበረው ቢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢጵ..አንድ ሰከንድ አርፎ ቢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢጵ….ከሁለት ሰከንድ በኋላም ቢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢኢአጵ ……ሎል…. ጀለሶች የኢቲቪንም ችግር ተረዱት እንጂ! …እሺ "ቢኢኢጱ" ቢቀር እና ቀጥታ የኢሬቻው በአል ቢተላላፍ ኢቲቪ ለግማሽ ቀን OMN ሆኖ ሊውል መሆኑን አጥታችሁት ነው?!...éረ የአራዳ ልጆች ላሽ በሉት…...!
ሌላ ወሬ ፍለጋ እዚሁ ሰፈር (ፌቡ) በየጉራንጉሩ ስሽሎከለክ ያጋጠመኝ የዞን ናይኑ በፍቄ ያነሳው ሃሳብ ያስነሳው አዋራ ነው፡፡የበፍቄን ሃሳብ የሚመጥን ሃሳብ ለማንሳት እና አንጻር በአንጻር ሃሳቡን ቻሌንጅ ለማድረግ ከስሜት ባሻገር በርካታ መጽሃፍቶችን ማገላበጥ ስለሚያስፈልግ ዛሬም ሰንበት እና አውዳአመት በመሆኑም ጭምር በፍቄ ካነሳቸው ሃሳቦች በአንደኛዋ ቀላል ሃሳብ ብቻ ፈታ እንበል…..የበፍቄን ፖስት ላላነበባችሁ እንድታነቡት እየጋበዝኩ በፖስቱ ያነሳቸው ሃሳቦች ምን ምን መሰላችሁ"…ለመሆኑ አማራ የሚባል ብሄር አለ ወይ?" "አማርኛ ቋንቋስ ከየት መጣ!?" "የአማራ ብሄርተኝነትስ ምንድነው? የትስ ይደርሳል!?"…..ወዘተ ናቸው…. አንድ ሁለት ምሁራንንም ጠቅሳ በፍቄ "አማርኛ ከ13ኛው ክ/ዘመን በፊት ያልነበረ ቋንቋ ነው" የሚል መደምደሚያ የሰጠች ሲሆን እንደውም ደፈር ብላ "አማርኛ ቋንቋ የተፈጠረው ኦሮሞዎች በወቅቱ ወሳኝ ቋንቋ የነበረውን ግእዝኛ ለማውራት ሲውተረተሩ በተፈጠረ ስህተት ነው" ብላለች፡፡ ይህ ድምዳሜዋ ነው እንግዲህ ከአማራው ወገን ብዙ ትችት ያስከተለባት፡፡ (አብዛኛው ኮሜንት ዘለፋ ቢሆንም ቀላል የማይባሉም በእውቀት እንዲሞግቱት ምክንያት ሆኗል)….."ስንት ታሪክ ያለው አማርኛችንን እንዴት አሮሞ ግእዝ ሲያወራ አጣሞ የፈጠረው ነው ትላለህ?" እየተባለ በፍቄ ሲነረት ወገኖቼ አሮሞዎች ግን ዳር ላይ ሆነው ሙድ መያዝ መርጠዋል….ቆይ ግን እኛ ኦሮሞዎችስ ቢሆን ይሄን ሃሳብ መቀበል አለብን እንዴ ጋይስ? ….."ተመልሰን ሻሸመኔ" የሚያስብለው እንግዲህ ይሄ ነው…ማለት ትላንት ስለ ኢትዮጲያ አንድነት ሲሰብክ የነበረው አንዲ ማኛ ተመልሶ ስለ ብሄር ሲወያይ ስታዩት "አይ ሰው! ተመልሶ እዛው ጭቃ ውስጥ ገባ?" ማለታችሁ አይቀርም…..….. ዛሬ እሬቻም ማይደል! ….በተፈጠረብኝ የብሄር መነቃቃት ትንሽ ብሄሬን ወክዬ ልርመጥመጥ እና ልቀየስ…. እሺ! ለጨዋታ ነው !ፈታ በሉዋ ጋይስ….. !
አንግዲህ በፍቄ እንዳለው በ13ኛው ክ/ዘመን ኦሮሞዎች ኦሮምኛችንን ትተን ግእዝ ለማውራት ቋመጥን እንበል……የግእዝ ተናጋሪዎች እርስ በእርሳቸው "ሰላም ለከ አ ኁ የ…" ሲባባሉ አየን/ሰማን "ወንድሜ ሰላም ላንተ ይሁን" እንደማለት ነው፡፡በራሳችን "አካም ጅርታ ኦቦሌሳ" ነበር የምንባባለው…..እንግዲህ "አካም ጅርታ እና ሰላም ለከ" ተደባልቀው ነው "ሰላም ላንተ ይሁን" የሚል አማርኛ የተፈጠረው ማለት ነው፡፡
ሰፈራችን አንድ ጸጉረ ልውጥ ሰው ሲመጣ "ኤሳ ዱፍታ?!" የምንል ኦሮሞዎች ግእዝ ተናገሪዎች "እ ም አ ይቴ መጻ እ ከ?" ሲሉ ሰምተን ይሄንን ከራሳችን ቋንቋ አደባልቀን "ከየት መጣህ ?"የሚል የአማርኛ ቋንቋ እንዴት ፈጠርን?....... "ወ መኑ ስ መ አ ቡከ?" የሚለውን ጥያቄ "መቃን አባ ኬቲ ኤኙ?" ከሚለው ኦሮምኛችን ጋር አምታተን "የአባትህ ስም ማነው?!" የሚል አማርኛ ስንፈጥር ላየ በእውነት አሮሞዎች ችግራችን የቋንቋ ሳይሆን የጆሮ/የመስማት ነው ያስብላል፡፡
"አንተ ገመቺስ ያ የበቀደሙ ጓደኛህ የት ሄደ?!" ብለው በግእዝኛ ሲጠይቁን ለወትሮው "ከራ አምቦ ዴሜ " ብለን በኦሮምኛ የምንመልሰው ሰዎች በግእዝኛ "ዝንቲ ብ ሲ ሖረ ኀበ አምቦ " ማለት አምሮን ስንንተባተብ "ሰውዬው ወደ አምቦ ሄደ" የሚል አማርኛ ፈጥረን ቁጭ!?…".ዌር ዊ ክሬዚ ኦር ሰምቲንግ ……?ኦር ኮሌክቲቭሊ ድራንክ? ሁላ ያስብላል...ሎል …..በፍቄ ወዳጄ አንዳንዴ እነ ዶናልድ ሌቪን ያለ ሃሳብ የሚለደፉትን ክራፕ ከነነፍሱ ከመቀበል እንታቀብ ለማለት ያህል ነው….በተረፈ የማይደፈሩ ሃሳቦችን አንስተህ ለማወያየት ለምታደርገው ጥረት የምንግዜም አድናቂህ ነኝ ለማለት እፈልጋለሁ..ኢማችሽ ብሮ(ይመችሽ ብሮ እላለሁ ብዬ ነው …ሎል) …እንግደህ ዚስ ኢዝ ፌስ ቡክ ስድቡንም ሆነ ትችቱን ቻል ማድረግ ነው…….ከመለያየታችን በፊት እኔም አንድ ግዜ ከ"ፕሮፌሰር እንዳሻህ ተናገር" መጻፍ ያነበብኩትን ታሪክ ጣል አድርጌብሽ ልሸብለል….ፕሮፌሰሩ በመጻፋቸው ገጽ 51 ላይ ቁልጭ አድርገው እንዳስቀመጡት..ቀደም ብሎ በኢትዮጲያ ውስጥ የነበረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ለአማርኛ ቋንቋ መፈጠር ካደረገው አስተዋጽኦ በተጨማሪ ለብዙ ሀገራት ስያሜም መነሻ ሆኗል…ለምሳሌ ጃንሆይ በ19ኛው ክ/ዘመን ወደ ካናዳ የላኳቸው የኦሮሞ ልኡካን ቡድን አባላት በሀገሪቱ እና ህዝቡ ባህል በመደመም በኦሮምኛ አስር ግዜ "ከን አዳ" (ይህ ባህል) ሲሉ የሰማው የሀገሬው ህዝብ ከዚህ በመነሳት ሀገሪቷን "ካናዳ" ብሎ እንደሰየማት ይታወቃል፡፡ይህ የልኡካን ቡድን ተልእኮውን ፈጽሞ በቀጥታ ወደ ኖርዌይ ያመራ ሲሆን በጊዜው የቡድኑ አባላት ከመርከብ እንደወረዱ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ እና ሀገሪቷ በጣም በመቀዝቀዟ የተገረሙት ኦሮሞ ልኡካን "በዚህ ቅዝቃዜ ሰው ችሎ ኖረ ወይ?" ሲሉ የሰማ አካባቢው ኗሪ ከአፋቸው ላይ ለቀም አድርጎ ሀገሪቷን "ኖርዌይ" ብሎ እንደሰየማት ተረጋግጧል፡፡ በእርግጥ በተመሳሳይ ጊዜ ለተመሳሳይ አላማ ወደ ፈረንሳይ ዋና ከተማ የተጓዘው የአማራ ልኡክም በወንዶቹ ጺም እና ሪዝ በመገረም አስሬ "ፐ ሪዝ" ሲል የሀገሬው ህዝብ በመስማቱ "ፓሪስ" የአሁን ስሟን እዳገኘችም ተያይዞ ይነገራል፡፡
አቦ ታሪክ ይለምልም!
ሌሎቻችሁ ደግሞ
ይመቻችሁ

Search
Categories
Read More
Shopping
Exquisite Hand Work Sherwani: Timeless Craftsmanship and Elegance
An exquisite hand work sherwani is a masterpiece that captures the essence of...
By Stylish12 2024-10-31 10:46:00 0 0
Other
HÀNG CHÍNH HÃNG: Xe Nâng Điện UNICARRIERS 1.5 Tấn J1B1L15 (FB15)
Bạn đang tìm kiếm một chiếc xe nâng điện mạnh mẽ, bền bỉ, hoạt động êm...
By xenangaz 2025-04-16 07:03:52 0 0
Other
HÀNG BÃI NHẬT: Xe Nâng Điện KOMATSU FB10-12 Bảo hành dài hạn, Giao hàng tận nơi
Bạn đang tìm kiếm một chiếc xe nâng điện mạnh mẽ, tiết kiệm, linh hoạt và an...
By xenangaz 2025-04-17 07:38:45 0 0
Uncategorized
አስገራሚ ቃለ ምልልስ -ሙጋቤ
”መቼም ሙጋቤ መልካም ሰው ነው” ይላል- መንግስቱ ሃይለማርያም የክፉ ቀን ደራሹን ማመስገን ሲጀምር።በርግጥ የሙጋቤን መልካምነት...
By binid 2017-11-26 06:36:34 0 0
Uncategorized
Great Ethiopian Concert
new great ethiopian  Concert 
By Dawitda 2017-11-14 06:25:05 0 0