‹‹በህልም የተፈጠረ መወስለት ከሐጢያት ይቆጠር ይሆን?››
‹‹በህልም የተፈጠረ መወስለት ከሐጢያት ይቆጠር ይሆን?››(አሳዬ ደርቤ)እንዴት ዋላችሁ ምዕመናን? እኔ ባሳለፍነው ሌሊት ከስንት መንጠራራትና ማዛጋት በኋላ የወሰደኝ እንቅልፍ ያልሆነ ህልም ውስጥ አስገብቶ ሲያዳክረኝ ካደረ በኋላ እንዱንም ሳልቋጨው አስበርግጎ ስለለቀቀኝ ቀኔን ያሳለፍኩት በጸጸትና በንደት መሃከል ስወዛገብ ነው፡፡ከሁሉ አስቀድሜ መናገር የምፈልገው ነገር… ስተውንበት ያደርኩት ህልም እናት አገራችን ያለችበትን አስከፊ ሁኔታ ያላገናዘበና አንድ ታማኝ ባለትዳርን ያባለገ በመሆኑ በተባበረ ክንዳችሁ ብታወግዙት ቅር አይለኝም፡፡በእውነቱ የልቤን ጥንካሬ...