በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች አንዱ ተደርጎ ከሰሞኑ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እየተሰናዳ እንደሚገኝ የገለፀው የጎንደር ከተማ አስተዳደር፤ ኤርትራውያን በክብረ በዓሉ ላይ እንዲገኙለት ጋብዟል፡፡ ‹‹ለመላው ኤርትራውያን ይድረስልኝ›› በማለት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባሰራጨውና በኤርትራ ፕሬስ ላይ ከተዘገበው ደብዳቤ መረዳት እንደተቻለው፤ ግብዣው በዋናነት የኢትዮጵያንና የኤርትራን ሕዝብ ወዳጅነት ለማጠናከር የታቀደ ነው፡፡ ‹‹ካለን የባህል መተሳሰር፣ ጥብቅ ወዳጅነትና ወንድማማችነት የተነሳ፣ በጎንደር ጎዳናዎች እናንተን ማየት ያስደስተናል›› በማለት በጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ማስተዋል ስዩም፣ ለመላ ኤርትራውያን የተላከው የግብዣ ደብዳቤ፤ በኤርትራውያን ዘንድ በሙሉ ደስታና ተቀባይነት ማግኘቱን የኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ከጥር 10 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በሚከበረው የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ የክብር ተጋባዥ ከሆኑት ኤርትራውያን በተጨማሪ በርካታ የውጭ አገር ቱሪስቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

0 Comments
0 Shares