Addis Admas weekly Newspaper
Recent Updates
-
በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች አንዱ ተደርጎ ከሰሞኑ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እየተሰናዳ እንደሚገኝ የገለፀው የጎንደር ከተማ አስተዳደር፤ ኤርትራውያን በክብረ በዓሉ ላይ እንዲገኙለት ጋብዟል፡፡ ‹‹ለመላው ኤርትራውያን ይድረስልኝ›› በማለት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባሰራጨውና በኤርትራ ፕሬስ ላይ ከተዘገበው ደብዳቤ መረዳት እንደተቻለው፤ ግብዣው በዋናነት የኢትዮጵያንና የኤርትራን ሕዝብ ወዳጅነት ለማጠናከር የታቀደ ነው፡፡ ‹‹ካለን የባህል መተሳሰር፣ ጥብቅ ወዳጅነትና ወንድማማችነት የተነሳ፣ በጎንደር ጎዳናዎች እናንተን ማየት ያስደስተናል›› በማለት በጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ማስተዋል ስዩም፣ ለመላ ኤርትራውያን የተላከው የግብዣ ደብዳቤ፤ በኤርትራውያን ዘንድ በሙሉ ደስታና ተቀባይነት ማግኘቱን የኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ከጥር 10 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በሚከበረው የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ የክብር ተጋባዥ ከሆኑት ኤርትራውያን በተጨማሪ በርካታ የውጭ አገር ቱሪስቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች አንዱ ተደርጎ ከሰሞኑ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እየተሰናዳ እንደሚገኝ የገለፀው የጎንደር ከተማ አስተዳደር፤ ኤርትራውያን በክብረ በዓሉ ላይ እንዲገኙለት ጋብዟል፡፡ ‹‹ለመላው ኤርትራውያን ይድረስልኝ›› በማለት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባሰራጨውና በኤርትራ ፕሬስ ላይ ከተዘገበው ደብዳቤ መረዳት እንደተቻለው፤ ግብዣው በዋናነት የኢትዮጵያንና የኤርትራን ሕዝብ ወዳጅነት ለማጠናከር የታቀደ ነው፡፡ ‹‹ካለን የባህል መተሳሰር፣ ጥብቅ ወዳጅነትና ወንድማማችነት የተነሳ፣ በጎንደር ጎዳናዎች እናንተን ማየት ያስደስተናል›› በማለት በጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ም/ከንቲባ ማስተዋል ስዩም፣ ለመላ ኤርትራውያን የተላከው የግብዣ ደብዳቤ፤ በኤርትራውያን ዘንድ በሙሉ ደስታና ተቀባይነት ማግኘቱን የኤርትራ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ ከጥር 10 እስከ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በሚከበረው የዘንድሮው የጥምቀት በዓል ላይ የክብር ተጋባዥ ከሆኑት ኤርትራውያን በተጨማሪ በርካታ የውጭ አገር ቱሪስቶች፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMጎንደር ኤርትራውያንን ለጥምቀት በዓል በልዩ በክብር ጋብዛለች - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> በዩኔስኮ ከማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶች አንዱ ተደርጎ ከሰሞኑ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል በደማቅ ሁኔታ ለማክበር እየተሰናዳ እንደሚገኝ የገለፀው የጎንደር ከተማ...0 Comments 0 SharesPlease log in to like, share and comment!
-
ወላይታ ዞን ላይ የተጠናከረ የፀጥታ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ለወላይታ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ባሳለፍነው ሳምንት በነበሩ ተከታታይ ቀናት የአገር ሽማግሌዎች፣ ነጋዴዎች፣ ሴቶች፣ የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች፣ ወጣቶች በተናጠል በወላይታ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ የሰነበቱ ሲሆን ከረቡዕ ጀምሮ አካባቢው በተጠናከረ የኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ የነበሩት የወላይታ የክልልነት ጥያቄ በሕገ መንግስቱ መሰረት ለክልሉ ም/ቤት ከቀረበ 1 አመት መሙላቱን በማስመልከት መሆኑን በዋናነት የክልልነት ጥያቄውን በኮሚቴነት የሚያንቀሳቅሱ ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የወላይታ የክልልነት ጥያቄ ከቀረበ ትናንት ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም አንድ ዓመት ቢሞላውም ከየትኛውም አካል በጉዳዩ ላይ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ምላሽ አለመገኘቱን የገለፁት ምንጮች ይህም በሕገ መንግስቱ መሠረት ለጥያቄው ምላሽ የሚሆን ሕዝበ ውሳኔ እየተደራጀ አለመሆኑ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ሕገ መንግስቱ ‹‹ጥያቄው በቀረበ በ1 ዓመት ውስጥ ምላሽ ማግኘት አለበት ቢልም ምላሽ አለመገኘቱን ለአዲስ አድማስ ያስረዱት የእንቅስቃሴው መሪዎች በዚህ መነሻ ወላይታ ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ ከደቡብ ክልላዊ መንግስት ጋር ግንኙነት አይኖረውም ቀጥተኛ ግንኙነት የሚኖረው ከፌዴራሉ ጋር ይሆናል›› ብለዋል፡፡ የወላይታ የክልልነት ጥያቄ ሕግን የተከተለና በጨዋነት የተሞላ ነው ያሉት ምንጮች ከሁለት ሳምንት በፊት ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ሕዝቡን ወክለው ላደረጉት ውይይትም ጠ/ሚኒስትሩ የወላይታ ሕዝብ ክልል መሆን ከፈለገ የሚያግደው ነገር እንደሌለ ማስገንዘባቸውን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል:: ከሕዝቡ ጋር በተደረገ ውይይትም ጥያቄውን እስከ መጨረሻው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ለማቅረብ ቃል ኪዳን መታሰሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በአንጻሩ ሶዶ ከተማን ጨምሮ በዞኑ የተለያዩ ከተሞች ጠንካራ የኮማንድ ፖስት የፀጥታ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ሀሙስ ምሽት የተወሰኑ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችና ወጣቶች ታስረው የነበረ ቢሆንም ምክር ተሰጥቷቸው በርካቶቹ ትናንት መለቀቃቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የወላይታ የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ ሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ እንደተስማማና ሰፊ ውይይት እንደተደረገበት ለጠ/ሚኒስትሩ ገለጻ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች ሕዝቡ ክልል መሆንን የሚመርጥ ከሆነ ሕጋዊ ሂደትን ተከትሎ ነገሩ መቋጨት እንዳለበት ማስረዳታቸውንም በውይይቱ የተሳተፉ ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ማብራሪያ ለመጠየቅ ወደ ኮሚኒኬሽን ኃላፊዋ ሶሊያና ሽመልስ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ስልካቸው ባለመነሳቱና ስብሰባ ላይ ነን የሚል አጭር መልዕክት በመመለሳቸው ሊሳካልን አልቻለም፡፡ወላይታ ዞን ላይ የተጠናከረ የፀጥታ ቁጥጥር እየተደረገ ነው ለወላይታ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ ባሳለፍነው ሳምንት በነበሩ ተከታታይ ቀናት የአገር ሽማግሌዎች፣ ነጋዴዎች፣ ሴቶች፣ የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች፣ ወጣቶች በተናጠል በወላይታ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ የሰነበቱ ሲሆን ከረቡዕ ጀምሮ አካባቢው በተጠናከረ የኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር መዋሉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ እነዚህ ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ የነበሩት የወላይታ የክልልነት ጥያቄ በሕገ መንግስቱ መሰረት ለክልሉ ም/ቤት ከቀረበ 1 አመት መሙላቱን በማስመልከት መሆኑን በዋናነት የክልልነት ጥያቄውን በኮሚቴነት የሚያንቀሳቅሱ ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የወላይታ የክልልነት ጥያቄ ከቀረበ ትናንት ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም አንድ ዓመት ቢሞላውም ከየትኛውም አካል በጉዳዩ ላይ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ምላሽ አለመገኘቱን የገለፁት ምንጮች ይህም በሕገ መንግስቱ መሠረት ለጥያቄው ምላሽ የሚሆን ሕዝበ ውሳኔ እየተደራጀ አለመሆኑ በሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ሕገ መንግስቱ ‹‹ጥያቄው በቀረበ በ1 ዓመት ውስጥ ምላሽ ማግኘት አለበት ቢልም ምላሽ አለመገኘቱን ለአዲስ አድማስ ያስረዱት የእንቅስቃሴው መሪዎች በዚህ መነሻ ወላይታ ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ ከደቡብ ክልላዊ መንግስት ጋር ግንኙነት አይኖረውም ቀጥተኛ ግንኙነት የሚኖረው ከፌዴራሉ ጋር ይሆናል›› ብለዋል፡፡ የወላይታ የክልልነት ጥያቄ ሕግን የተከተለና በጨዋነት የተሞላ ነው ያሉት ምንጮች ከሁለት ሳምንት በፊት ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ሕዝቡን ወክለው ላደረጉት ውይይትም ጠ/ሚኒስትሩ የወላይታ ሕዝብ ክልል መሆን ከፈለገ የሚያግደው ነገር እንደሌለ ማስገንዘባቸውን ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል:: ከሕዝቡ ጋር በተደረገ ውይይትም ጥያቄውን እስከ መጨረሻው በሰላማዊ መንገድ ብቻ ለማቅረብ ቃል ኪዳን መታሰሩን ምንጮች አስረድተዋል፡፡ በአንጻሩ ሶዶ ከተማን ጨምሮ በዞኑ የተለያዩ ከተሞች ጠንካራ የኮማንድ ፖስት የፀጥታ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ሀሙስ ምሽት የተወሰኑ የፖለቲካ ድርጅት አመራሮችና ወጣቶች ታስረው የነበረ ቢሆንም ምክር ተሰጥቷቸው በርካቶቹ ትናንት መለቀቃቸውን ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ የወላይታ የክልልነት ጥያቄን አስመልክቶ ሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ እንደተስማማና ሰፊ ውይይት እንደተደረገበት ለጠ/ሚኒስትሩ ገለጻ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች ሕዝቡ ክልል መሆንን የሚመርጥ ከሆነ ሕጋዊ ሂደትን ተከትሎ ነገሩ መቋጨት እንዳለበት ማስረዳታቸውንም በውይይቱ የተሳተፉ ምንጮች ለአዲስ አድማስ አስረድተዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ማብራሪያ ለመጠየቅ ወደ ኮሚኒኬሽን ኃላፊዋ ሶሊያና ሽመልስ ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ስልካቸው ባለመነሳቱና ስብሰባ ላይ ነን የሚል አጭር መልዕክት በመመለሳቸው ሊሳካልን አልቻለም፡፡ADDISADMASSNEWS.COMየወላይታ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ የሚጠይቁ ሰልፎች በሳምንቱ ሲካሄዱ ሰንብተዋል - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"><br /> ወላይታ ዞን ላይ የተጠናከረ የፀጥታ ቁጥጥር እየተደረገ ነው<br /><br /> ለወላይታ የክልልነት ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጥ...0 Comments 0 Shares
-
ፓርላማው በቅርቡ ያፀድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን የሚመለከተው ረቂቅ ሕግ ያለ በቂ ጥናት የተዘጋጀ በመሆኑ በአገሪቱ የመናገር ነፃነትን ያፍናል የሚል ስጋት እንዳላቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ገልፀዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በአገሪቱ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የሚተላለፉ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር የወጣ እንደመሆኑ፣ አንዳንድ በውስጡ የተካተቱ ድንጋጌዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት የዜጎችን የመናገር ነፃነት ለማፈን እንዲጠቀሙበት እድል የሚሰጥ ነው - ብሏል ሂውማን ራይትስ ዎች በወጣው ሪፖርት፡፡ ረቂቅ አዋጁ በዋናነት የጥላቻ ንግግርን የተረጎመበት መንገድ ከአለማቀፍ የመናገር ነፃነት ድንጋጌዎች ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው ያለው ተቋሙ፤ ድንጋጌው ለአሻሚ ትርጉሞችም የተጋለጠ ነው ብሏል፡፡ባለሥልጣናት ሕጉን በፈለጉት አግባብ ተርጉመው ለማጥቂያነት ሊጠቀሙት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለው በመግለጽም፤ አሻሚ ብያኔዎች ትርጉሞች፣ አገላለፆችና አንቀፆችን ያካተተው፤ ሕጉ በድጋሚ እንዲፈተሽ ጠይቋል፡፡ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የጥላቻ ንግግርና፣ ስድብን የሚከለክልበት ጠንካራ ድንጋጌ እንዳለው ጠቅሶ የተለየ ሕግ ማውጣት በራሱ አስፈላጊ አይደለም ብሏል - ተቋሙ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም፤ በረቂቅ ሕጉ ላይ ውይይት ሲያደርግ ተጨማሪ የመጨቆኛ መሳሪያ እንዳይሆን ማጤን እንዳለበት ያሳሰበው ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ አቃቤ ሕጎች፣ ጠበቆች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የሚዲያ ባለሙያዎች በጥልቀት ሊወያዩበት ይገባል ብሏል፡፡ በተመሳሳይ፤ የተባበሩት መንግሥታት የንግግር ነፃነት ከፍተኛ ባለሙያ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት፤ ረቂቅ ሕጉ አለማቀፍ መስፈርቶችን የማያሟላና የመናገር ነፃነትን የሚገድብ ነው ሲሉ መተቸታቸው ተዘግቧል፡፡ፓርላማው በቅርቡ ያፀድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን የሚመለከተው ረቂቅ ሕግ ያለ በቂ ጥናት የተዘጋጀ በመሆኑ በአገሪቱ የመናገር ነፃነትን ያፍናል የሚል ስጋት እንዳላቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ገልፀዋል፡፡ ረቂቅ አዋጁ በአገሪቱ ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የሚተላለፉ መልዕክቶችን ለመቆጣጠር የወጣ እንደመሆኑ፣ አንዳንድ በውስጡ የተካተቱ ድንጋጌዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት የዜጎችን የመናገር ነፃነት ለማፈን እንዲጠቀሙበት እድል የሚሰጥ ነው - ብሏል ሂውማን ራይትስ ዎች በወጣው ሪፖርት፡፡ ረቂቅ አዋጁ በዋናነት የጥላቻ ንግግርን የተረጎመበት መንገድ ከአለማቀፍ የመናገር ነፃነት ድንጋጌዎች ጋር በእጅጉ የሚቃረን ነው ያለው ተቋሙ፤ ድንጋጌው ለአሻሚ ትርጉሞችም የተጋለጠ ነው ብሏል፡፡ባለሥልጣናት ሕጉን በፈለጉት አግባብ ተርጉመው ለማጥቂያነት ሊጠቀሙት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳለው በመግለጽም፤ አሻሚ ብያኔዎች ትርጉሞች፣ አገላለፆችና አንቀፆችን ያካተተው፤ ሕጉ በድጋሚ እንዲፈተሽ ጠይቋል፡፡ የኢትዮጵያ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የጥላቻ ንግግርና፣ ስድብን የሚከለክልበት ጠንካራ ድንጋጌ እንዳለው ጠቅሶ የተለየ ሕግ ማውጣት በራሱ አስፈላጊ አይደለም ብሏል - ተቋሙ፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም፤ በረቂቅ ሕጉ ላይ ውይይት ሲያደርግ ተጨማሪ የመጨቆኛ መሳሪያ እንዳይሆን ማጤን እንዳለበት ያሳሰበው ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ አቃቤ ሕጎች፣ ጠበቆች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የሚዲያ ባለሙያዎች በጥልቀት ሊወያዩበት ይገባል ብሏል፡፡ በተመሳሳይ፤ የተባበሩት መንግሥታት የንግግር ነፃነት ከፍተኛ ባለሙያ ባለፈው ሳምንት ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት፤ ረቂቅ ሕጉ አለማቀፍ መስፈርቶችን የማያሟላና የመናገር ነፃነትን የሚገድብ ነው ሲሉ መተቸታቸው ተዘግቧል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMየፀረ ጥላቻና የሀሰተኛ መረጃ ረቂቅ አዋጅ በድጋሚ እንዲጤን አለማቀፍ ተቋማት ጠየቁ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> ፓርላማው በቅርቡ ያፀድቀዋል ተብሎ የሚጠበቀው የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃን የሚመለከተው ረቂቅ ሕግ ያለ በቂ ጥናት የተዘጋጀ በመሆኑ በአገሪቱ የመናገር ነፃነ...0 Comments 0 Shares
-
አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል እንድትሆን የኢትዮጵያውያን አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ጠየቀ፡፡ ድርጅቱ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫው፤ በፓርቲነት ከተቋቋመበት 1992 ዓ.ም ጀምሮ በዋናነት የአዲስ አበባን ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጥያቄ እስከ ክልል መሆን እንቅስቃሴ ሲራምድ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፤ በፖለቲካው በኢኮኖሚውና ማህበራዊው ዘርፍ እድገቷ እንዲፋጠን፤ የተወላጁና ነዋሪው የእኩልነት መብታቸው በእኩል እንዲጠበቅ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል መሆን አለባት ብሏል - ድርጅቱ፡፡ ይሄንኑ ጥያቄውንም ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ማቅረቡን ገልጿል፡፡ አዲስ አበባ የ89 ብሄር ብሄረሰቦች ክልል እንዲሁም የፌደራል መንግስቱ ርዕሰ ከተማ እንደሆነች ያወሳል፡፡ በሕዝብ ብዛትም ከሁሉም ክልሎች በ3ኛ ደረጃ መቀመጧን የገለፀው ድርጅቱ፤ ከሕዝብ ብዛቷም ሆነ ማህበራዊ መስተጋብሯ አንፃር ራሷን የቻለች ክልል መሆን ይገባታል ብሏል፡፡ አዲስ አበባ ራስ ገዝ ሆነ የራሷን ክልላዊ መንግስት እንድታቋቁም፣ የራሷን ክልል ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንድትወጣ፣ የራሷን ሃብትና መሬት በራሷ እንድታስተዳድር እንዲሁም ራሷን በራሷ የማስተዳደር አላማን መሰረት ያደረገ ክልላዊ መስተዳድር እንዲዋቀርላት ድርጅቱ በደብዳቤው ጠይቋል፡፡ አዲስ አበባ የራሷን ግብር ለራሷ የምትሰብስብ፣ ፀጥታና ሰላሟን በራሷ ፀጥታ ሀይል የምትመራ፣ በፌደሬሽን ም/ቤት ውስጥ የራሷ ተወካይ ያላት እንድትሆንም የጠየቀው ፓርቲው፤ ‹‹የአዲስ አበባ ክልላዊ መንግስት››ን ማስተዳደር የሚገባው የአዲስ አበባ ተወላጅና ቀደምት ነዋሪ መሆን አለበት ይላል - በመግለጫው፡፡አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል እንድትሆን የኢትዮጵያውያን አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ጠየቀ፡፡ ድርጅቱ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫው፤ በፓርቲነት ከተቋቋመበት 1992 ዓ.ም ጀምሮ በዋናነት የአዲስ አበባን ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ጥያቄ እስከ ክልል መሆን እንቅስቃሴ ሲራምድ መቆየቱን አስታውቋል፡፡ በአዲስ አበባ ውስጥ ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፤ በፖለቲካው በኢኮኖሚውና ማህበራዊው ዘርፍ እድገቷ እንዲፋጠን፤ የተወላጁና ነዋሪው የእኩልነት መብታቸው በእኩል እንዲጠበቅ አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል መሆን አለባት ብሏል - ድርጅቱ፡፡ ይሄንኑ ጥያቄውንም ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ማቅረቡን ገልጿል፡፡ አዲስ አበባ የ89 ብሄር ብሄረሰቦች ክልል እንዲሁም የፌደራል መንግስቱ ርዕሰ ከተማ እንደሆነች ያወሳል፡፡ በሕዝብ ብዛትም ከሁሉም ክልሎች በ3ኛ ደረጃ መቀመጧን የገለፀው ድርጅቱ፤ ከሕዝብ ብዛቷም ሆነ ማህበራዊ መስተጋብሯ አንፃር ራሷን የቻለች ክልል መሆን ይገባታል ብሏል፡፡ አዲስ አበባ ራስ ገዝ ሆነ የራሷን ክልላዊ መንግስት እንድታቋቁም፣ የራሷን ክልል ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ እንድትወጣ፣ የራሷን ሃብትና መሬት በራሷ እንድታስተዳድር እንዲሁም ራሷን በራሷ የማስተዳደር አላማን መሰረት ያደረገ ክልላዊ መስተዳድር እንዲዋቀርላት ድርጅቱ በደብዳቤው ጠይቋል፡፡ አዲስ አበባ የራሷን ግብር ለራሷ የምትሰብስብ፣ ፀጥታና ሰላሟን በራሷ ፀጥታ ሀይል የምትመራ፣ በፌደሬሽን ም/ቤት ውስጥ የራሷ ተወካይ ያላት እንድትሆንም የጠየቀው ፓርቲው፤ ‹‹የአዲስ አበባ ክልላዊ መንግስት››ን ማስተዳደር የሚገባው የአዲስ አበባ ተወላጅና ቀደምት ነዋሪ መሆን አለበት ይላል - በመግለጫው፡፡ADDISADMASSNEWS.COMአዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል እንድትሆን ተጠየቀ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል እንድትሆን የኢትዮጵያውያን አንድነት ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ጠየቀ፡፡ ድርጅቱ ለአዲስ አድማስ በላከው መግለጫው፤ በፓርቲነት ከተቋቋ...0 Comments 0 Shares
-
- የ200 ሺ ሰዎች የሃብት ዝርዝር መዝገቢያለሁ ይላል - ፀረ ሙስና ኮሚሽን - የማንኛውም ባለሥልጣን የሃብት ብዛትን ለማወቅ ምን ያስፈልጋል? - በአካል መቅረብ፣ ‹‹ምክንያታዊ ሆኖ መጠየቅ›› ከፌዴራል እስከ ክልል፣ ከፕሬዚዳንትና ከጠቅላይ ሚኒስትር እስከ ታች ሃላፊዎች ድረስ፣ የምክር ቤት አባላትንና የመንግሥት ሰራተኞችን… በአጠቃላይ የ200 ሺህ ሰዎችን የሃብት አይነትና ብዛት የሚዘረዝር የመረጃ መጋዘን - የብዙ መቶ ሚሊዮን መረጃዎች ጥንቅር ነው፡፡ ስም፣ ዕድሜ፣ የቤተሰብ ሁኔታና አድራሻ የመሳሰሉት ነገሮችን ጨምሮ የንብረት አይነትና ብዛትን ያካትታል፡፡ የተመዘገቡ መረጃዎችን አጠናቅሮ በቅጡ እንዳሰናዳ የገለፀው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የባለሥልጣናትን የሀብት መረጃ ለሕዝብ ከፍቻለሁ ብሏል፡፡ አላንዳች ምክንያት የሰዎችን ሀብትና የጓዳ ንብረት ለማወቅ እንኳን በተከፈተ በር በጭላንጭል አጮልቆ የማየት ሱስን ለማርካት የተዘጋጀ መረጃ አይደለም፡፡ ይልቅስ፣ ሰዎች በጥረታቸው ንብረት እንዲያፈሩ እንጅ፣ ስልጣንን ለስርቆትና ለጉቦ እንዳይጠቀሙ ለመከላከል ያግዛል ተብሎ የተዘጋጀ መረጃ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ፣ የባለሥልጣናትና የበታች ሃላፊዎችን የሃብት መጠን ለማወቅ የፈለገ ሰው ምን ማሟላት አለበት? ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ሌለ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ዜጎች ወደ ኮሚሽኑ በአካል በመቅረብ፣ ‹‹ምክንያታዊ ሆኖ በመጠየቅ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ›› የባለሥልጣናትን ሃብት መመልከት እንደሚቻል የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ወደፊት፣ ለሁሉም ሕዝብ፣ በያለበት ተደራሽ ለማድረግ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ጥንቅር እየተከናወነና እየተሰናዳ ነው ብለዋል - ዳይሬክተሩ፡፡ በኮሚሽኑ የተሰበሰበውና የተሰናዳው መረጃ፤ ሦስት የመንግሥት አካላትን ይመለከታል፡፡ 1ኛ፣ የሕዝብ ተመራጮች (የፌዴራል ፓርላማ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ተመራጮች)፣ 2ኛ፣ የፌዴራልና የክልል የመንግስት ተሿሚዎች፣ 3ኛ ደግሞ፣ ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን ያላቸው የመንግስት ተቀጣሪዎች፣ አማካሪዎችና ሠራተኞች ላይ ያተኮረ ነው የኮሚሽኑ መረጃ፡፡ በዚህ መሠረት፣ ከ2 መቶ ሺህ በላይ ባለሥልጣናት፣ የምክር ቤት አባላትና የመንግስት ሰራተኞችም ሀብት ተመዝግቦ በኮሚሽኑ የመረጃ ቋት ውስጥ እንደሚገኝ አቶ መስፍን አስታውቀዋል፡፡- የ200 ሺ ሰዎች የሃብት ዝርዝር መዝገቢያለሁ ይላል - ፀረ ሙስና ኮሚሽን - የማንኛውም ባለሥልጣን የሃብት ብዛትን ለማወቅ ምን ያስፈልጋል? - በአካል መቅረብ፣ ‹‹ምክንያታዊ ሆኖ መጠየቅ›› ከፌዴራል እስከ ክልል፣ ከፕሬዚዳንትና ከጠቅላይ ሚኒስትር እስከ ታች ሃላፊዎች ድረስ፣ የምክር ቤት አባላትንና የመንግሥት ሰራተኞችን… በአጠቃላይ የ200 ሺህ ሰዎችን የሃብት አይነትና ብዛት የሚዘረዝር የመረጃ መጋዘን - የብዙ መቶ ሚሊዮን መረጃዎች ጥንቅር ነው፡፡ ስም፣ ዕድሜ፣ የቤተሰብ ሁኔታና አድራሻ የመሳሰሉት ነገሮችን ጨምሮ የንብረት አይነትና ብዛትን ያካትታል፡፡ የተመዘገቡ መረጃዎችን አጠናቅሮ በቅጡ እንዳሰናዳ የገለፀው የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የባለሥልጣናትን የሀብት መረጃ ለሕዝብ ከፍቻለሁ ብሏል፡፡ አላንዳች ምክንያት የሰዎችን ሀብትና የጓዳ ንብረት ለማወቅ እንኳን በተከፈተ በር በጭላንጭል አጮልቆ የማየት ሱስን ለማርካት የተዘጋጀ መረጃ አይደለም፡፡ ይልቅስ፣ ሰዎች በጥረታቸው ንብረት እንዲያፈሩ እንጅ፣ ስልጣንን ለስርቆትና ለጉቦ እንዳይጠቀሙ ለመከላከል ያግዛል ተብሎ የተዘጋጀ መረጃ ነው፡፡ የሆኖ ሆኖ፣ የባለሥልጣናትና የበታች ሃላፊዎችን የሃብት መጠን ለማወቅ የፈለገ ሰው ምን ማሟላት አለበት? ምንም ቅድመ ሁኔታ እንደ ሌለ ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ዜጎች ወደ ኮሚሽኑ በአካል በመቅረብ፣ ‹‹ምክንያታዊ ሆኖ በመጠየቅ፣ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ›› የባለሥልጣናትን ሃብት መመልከት እንደሚቻል የኮሚሽኑ የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ዳይሬክተር አቶ መስፍን በላይ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡ ወደፊት፣ ለሁሉም ሕዝብ፣ በያለበት ተደራሽ ለማድረግ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ የመረጃ ጥንቅር እየተከናወነና እየተሰናዳ ነው ብለዋል - ዳይሬክተሩ፡፡ በኮሚሽኑ የተሰበሰበውና የተሰናዳው መረጃ፤ ሦስት የመንግሥት አካላትን ይመለከታል፡፡ 1ኛ፣ የሕዝብ ተመራጮች (የፌዴራል ፓርላማ፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ተመራጮች)፣ 2ኛ፣ የፌዴራልና የክልል የመንግስት ተሿሚዎች፣ 3ኛ ደግሞ፣ ውሳኔ የማሳለፍ ስልጣን ያላቸው የመንግስት ተቀጣሪዎች፣ አማካሪዎችና ሠራተኞች ላይ ያተኮረ ነው የኮሚሽኑ መረጃ፡፡ በዚህ መሠረት፣ ከ2 መቶ ሺህ በላይ ባለሥልጣናት፣ የምክር ቤት አባላትና የመንግስት ሰራተኞችም ሀብት ተመዝግቦ በኮሚሽኑ የመረጃ ቋት ውስጥ እንደሚገኝ አቶ መስፍን አስታውቀዋል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMየማንን ሃብት ማወቅ ይፈልጋሉ? - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> - የ200 ሺ ሰዎች የሃብት ዝርዝር መዝገቢያለሁ ይላል - ፀረ ሙስና ኮሚሽን<br /> - የማንኛውም ባለሥልጣን የሃብት ብዛትን ለማወቅ ምን ያስፈልጋል...0 Comments 0 Shares
-
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የኤክሳዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው። አዋጁ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርና የአምራች ኩባንያዎችን ህልውና የሚፈታተን ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ያሉበትን ክፍተቶች ለማሟላትና ለመንግሥትም ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት ያስችላል ተብሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበውና ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፤ በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ አገር በሚገቡ የተለያዩ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥል ነው፡፡ በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የቅንጦት ዕቃዎች ተብለው የተለዩትና ተጨማሪ የኤክሳይዝ ታክስ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ጣፋጭና ጨዋማ ምግቦች የአልኮል መጠጦች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የታሸጉና ጋዝ ያላቸው ውሃዎችን የለስላሳ መጠጦች፣ ይገኙበታል፡፡ የኤክሳይዝ ታክሱ በሕብረተሰቡ ጤናና በአካባቢ ደህንነት ላይ ችግር ያስከትላሉ በተባሉ የነዳጅ ምርቶች. ተሽከርካሪዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም በመዋቢያ ቁሳቁሶች ላይ ተጥሏል፡፡ ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ መንግሥት ተገቢውን ታክስ እንዲሰበሰብ የሚያግዝ፣ ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነም በዚሁ ረቂቅ አዋጁ ላይ ተገልጿል፡፡ የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ የሚጎዱ፣ በማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ችግር የሚያስከትሉና መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው የማይቀንስ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ታክስ መጣል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡ በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፤ ዝቅተኛው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን 10 ከመቶ ሲሆን ይሄ ታክስ ከሚጣልባቸው ምርቶች ውስጥ የፎቶና የቪዲዮ ካሜራዎች፣ የቲቪ መቀበያና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡ ትምባሆ 30 በመቶ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) 40 በመቶ (በአንድ ኪሎ ግራም ፌስታል ላይ)፣ ስኳር 20 በመቶ፣ ሳቹሬቲድ ሰብ (ለጤና ጎጂ የሆነ ቅባትን የያዙ ዘይቶች ከ30-50 በመቶ፣ ዱቄት ለስላሳ መጠጦች፣ አልኮል አልባ የታሸጉ መጠጦች፣ ጋዝ ያላቸው የታሸጉ ውሃዎች ከ15-30 በመቶ፣ ቢራ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ በበቀለ ገብስ የተመረተ 35 ከመቶ እንዲሁም የወይን መጠጥ ግብአቶች ከ30-40 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸዋል፡፡ በኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተገለፀው ተሽከርካሪዎች እንደ አገልግሎት ዘመናቸው የሚጣልባቸው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን የሚለያይ ሲሆን ከዜሮ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያገለገሉ መኪናዎች 100 ፐርሰንት ፣ ከ7 ዓመት በላይ ያገለገሉ መኪኖች ደግሞ እስከ 500 ፐርሰንት የሚደርስ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህም ማለት የአገልግሎት ዘመናቸው ከ2012 በፊት ባሉ መኪኖች ላይ የሚጣለው የ500 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ የመኪኖቹን ዋጋ በአራትና በአምስት እጥፍ የሚያሳድገው ይሆናል፡፡ፖሊስ ክበብ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ካሉ የመኪና መሸጫ ማዕከላት የአንዱ ባለቤት የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ የማነ እንደተናገሩት ፣ በአሁኑ ወቅት ከ400 ሺ ብር ባልበለጠ ዋጋ እየተሸጡ ያሉ እንደ ቪትዝ ያሉ አነስተና መኪኖች በዚህ በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ መሰረት፣ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚሸጡ ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሕብረተሰቡን የመግዛት አቅም ሙሉ በሙሉ የሚገዳደር በመሆኑ እኛም ከዘርፉ ለመውጣት እንገደዳለን ብለዋል። በተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ያገለገሉ የእርሻ ትራክተሮችንም የሚመለከት ሲሆን እነዚህ ትራክተሮችም እስከ 400 በመቶ የሚደርስ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታም አገሪቱ ከተያያዘችውና ግብርናችንን በማዘመን በምግብ ራሳችንን የመቻል እቅድ ጋር በእጅጉ የሚቃረንና በሚገባ ታስቦበት ያልተወሰነ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ እንደ ስኳር፣ ዘይት፣ ጨውና ውሃ ባሉ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሊጣል የታሰበው የኤክሳይዝ ታክስ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት በእጅጉ የሚያባብስና የብዙሃኑን ሕዝብ ኑሮ የሚፈታተን መሆኑን የተናገሩ አስተያየት ሰጪዎች ፣ መንግሥት የማሻሻያ አዋጁን ከማጽደቁ በፊት ቆም ብሎ ሊያስብበትና ሁኔታውን በአግባቡ ሊመረምር ይገባል ብለዋል፡፡ በቢራ ምርቶች ላይ ሊጣል የታሰበውን የ35 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ኢንዱስትሪውን ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ የሚጥልና አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የታክስ ገቢ የሚያሳጣ እንደሆነ የቢራ አምራች ፋብሪካዎች ማህበር ገልጻል፡፡ ከማህበሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ በዘርፉ በሚያስከትለው ከፍተኛ ጫና ሳቢያ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚገደዱ ሲሆን ይህም የሽያጩን መጠን በእጅጉ ይቀንሰዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም ፋብሪካዎቹ ሰራተኞቻቸውን ለመቀነስ ይገደዳሉ፡፡ ለፋብሪካዎቹ ግብአት የሚሆን የቢራ ገብስ አምራች ገበሬዎችም ምርታቸውን የሚቀበላቸው ባለመኖሩ ምክንያት ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ግብር የምታጣ ሲሆን የቢራ አምራች ፋብሪካዎቹም እያደረጉ ያሉትን የማህበረሰብ ድጋፎች በእጅጉ ሊቀንሱ እንደሚገደዱ ከቢራ አምራች ፋብሪካዎች ማህበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። እንኳንስ ኤክሳይዝ ታክሱ ተጨምሮበት የአልኮል መጠጦች በሚዲያዎች እንዳይተዋወቁ በመደረጉ ሳቢያ በሽያጩ ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት መድረሱን ያመለከተው ይኸው መረጃ አዲሱ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ከጸደቀ በዘርፉ ሊሰማሩ በዝግጅት ላይ ያሉትንም ሆነ አሁን በሥራ ላይ የሚገኙትን የቢራ ምርት ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ የሚጎዳ ይሆናል ብሏል፡፡ መንግሥት ሁኔታውን በሚገባ ሊያጤነውና በአንድ ጊዜ ለመጣል ያሰበውን የኤክሳይዝ ታክስ በየአመቱ በትንሹ እየጣለ ካሰበበት ሊደርስ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በአንድ ጠርሙስ ቢራ ዋጋ ላይ የዘጠኝ ብር ጭማሪ ይደረግበታል ተብሏል ፡፡ ሰዎች ከሚጠቀሙባቸው የቅንጦት ዕቃዎች ላይ ገቢ በመሰብሰብ በድህነት ላይ ለሚገኙ ዜጎች ለመደጎም እንዲያስችል ታስቦ የተጣለው የታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የኤክሳዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው። አዋጁ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርና የአምራች ኩባንያዎችን ህልውና የሚፈታተን ነው ተብሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ያሉበትን ክፍተቶች ለማሟላትና ለመንግሥትም ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት ያስችላል ተብሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበውና ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፤ በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ አገር በሚገቡ የተለያዩ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥል ነው፡፡ በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የቅንጦት ዕቃዎች ተብለው የተለዩትና ተጨማሪ የኤክሳይዝ ታክስ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ጣፋጭና ጨዋማ ምግቦች የአልኮል መጠጦች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የታሸጉና ጋዝ ያላቸው ውሃዎችን የለስላሳ መጠጦች፣ ይገኙበታል፡፡ የኤክሳይዝ ታክሱ በሕብረተሰቡ ጤናና በአካባቢ ደህንነት ላይ ችግር ያስከትላሉ በተባሉ የነዳጅ ምርቶች. ተሽከርካሪዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እንዲሁም በመዋቢያ ቁሳቁሶች ላይ ተጥሏል፡፡ ረቂቅ የማሻሻያ አዋጁ መንግሥት ተገቢውን ታክስ እንዲሰበሰብ የሚያግዝ፣ ኮንትሮባንድና ሕገወጥ ንግድን ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነም በዚሁ ረቂቅ አዋጁ ላይ ተገልጿል፡፡ የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ የሚጎዱ፣ በማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ችግር የሚያስከትሉና መሰረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው የማይቀንስ ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ ታክስ መጣል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተጠቁሟል፡፡ በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ መሰረት፤ ዝቅተኛው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን 10 ከመቶ ሲሆን ይሄ ታክስ ከሚጣልባቸው ምርቶች ውስጥ የፎቶና የቪዲዮ ካሜራዎች፣ የቲቪ መቀበያና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ይገኙበታል፡፡ ትምባሆ 30 በመቶ የፕላስቲክ ከረጢት (ፌስታል) 40 በመቶ (በአንድ ኪሎ ግራም ፌስታል ላይ)፣ ስኳር 20 በመቶ፣ ሳቹሬቲድ ሰብ (ለጤና ጎጂ የሆነ ቅባትን የያዙ ዘይቶች ከ30-50 በመቶ፣ ዱቄት ለስላሳ መጠጦች፣ አልኮል አልባ የታሸጉ መጠጦች፣ ጋዝ ያላቸው የታሸጉ ውሃዎች ከ15-30 በመቶ፣ ቢራ ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ በበቀለ ገብስ የተመረተ 35 ከመቶ እንዲሁም የወይን መጠጥ ግብአቶች ከ30-40 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸዋል፡፡ በኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ ላይ እንደተገለፀው ተሽከርካሪዎች እንደ አገልግሎት ዘመናቸው የሚጣልባቸው የኤክሳይዝ ታክስ መጠን የሚለያይ ሲሆን ከዜሮ ዓመት እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያገለገሉ መኪናዎች 100 ፐርሰንት ፣ ከ7 ዓመት በላይ ያገለገሉ መኪኖች ደግሞ እስከ 500 ፐርሰንት የሚደርስ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህም ማለት የአገልግሎት ዘመናቸው ከ2012 በፊት ባሉ መኪኖች ላይ የሚጣለው የ500 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ የመኪኖቹን ዋጋ በአራትና በአምስት እጥፍ የሚያሳድገው ይሆናል፡፡ፖሊስ ክበብ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ካሉ የመኪና መሸጫ ማዕከላት የአንዱ ባለቤት የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ የማነ እንደተናገሩት ፣ በአሁኑ ወቅት ከ400 ሺ ብር ባልበለጠ ዋጋ እየተሸጡ ያሉ እንደ ቪትዝ ያሉ አነስተና መኪኖች በዚህ በአዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ መሰረት፣ ከአንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር በላይ የሚሸጡ ይሆናሉ፡፡ ይህ ደግሞ የሕብረተሰቡን የመግዛት አቅም ሙሉ በሙሉ የሚገዳደር በመሆኑ እኛም ከዘርፉ ለመውጣት እንገደዳለን ብለዋል። በተሽከርካሪዎች ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ያገለገሉ የእርሻ ትራክተሮችንም የሚመለከት ሲሆን እነዚህ ትራክተሮችም እስከ 400 በመቶ የሚደርስ የኤክሳይዝ ታክስ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህ ሁኔታም አገሪቱ ከተያያዘችውና ግብርናችንን በማዘመን በምግብ ራሳችንን የመቻል እቅድ ጋር በእጅጉ የሚቃረንና በሚገባ ታስቦበት ያልተወሰነ መሆኑን አስተያየት ሰጪዎች ይገልጻሉ፡፡ እንደ ስኳር፣ ዘይት፣ ጨውና ውሃ ባሉ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሊጣል የታሰበው የኤክሳይዝ ታክስ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚታየውን የኑሮ ውድነት በእጅጉ የሚያባብስና የብዙሃኑን ሕዝብ ኑሮ የሚፈታተን መሆኑን የተናገሩ አስተያየት ሰጪዎች ፣ መንግሥት የማሻሻያ አዋጁን ከማጽደቁ በፊት ቆም ብሎ ሊያስብበትና ሁኔታውን በአግባቡ ሊመረምር ይገባል ብለዋል፡፡ በቢራ ምርቶች ላይ ሊጣል የታሰበውን የ35 በመቶ የኤክሳይዝ ታክስ ኢንዱስትሪውን ሙሉ በሙሉ አደጋ ላይ የሚጥልና አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን የታክስ ገቢ የሚያሳጣ እንደሆነ የቢራ አምራች ፋብሪካዎች ማህበር ገልጻል፡፡ ከማህበሩ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጁ በዘርፉ በሚያስከትለው ከፍተኛ ጫና ሳቢያ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ የሚገደዱ ሲሆን ይህም የሽያጩን መጠን በእጅጉ ይቀንሰዋል፡፡ በዚህ ምክንያትም ፋብሪካዎቹ ሰራተኞቻቸውን ለመቀነስ ይገደዳሉ፡፡ ለፋብሪካዎቹ ግብአት የሚሆን የቢራ ገብስ አምራች ገበሬዎችም ምርታቸውን የሚቀበላቸው ባለመኖሩ ምክንያት ለኪሳራ ይዳረጋሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ግብር የምታጣ ሲሆን የቢራ አምራች ፋብሪካዎቹም እያደረጉ ያሉትን የማህበረሰብ ድጋፎች በእጅጉ ሊቀንሱ እንደሚገደዱ ከቢራ አምራች ፋብሪካዎች ማህበር የተገኘው መረጃ ያመለክታል። እንኳንስ ኤክሳይዝ ታክሱ ተጨምሮበት የአልኮል መጠጦች በሚዲያዎች እንዳይተዋወቁ በመደረጉ ሳቢያ በሽያጩ ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት መድረሱን ያመለከተው ይኸው መረጃ አዲሱ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ከጸደቀ በዘርፉ ሊሰማሩ በዝግጅት ላይ ያሉትንም ሆነ አሁን በሥራ ላይ የሚገኙትን የቢራ ምርት ኢንቨስትመንቶች በእጅጉ የሚጎዳ ይሆናል ብሏል፡፡ መንግሥት ሁኔታውን በሚገባ ሊያጤነውና በአንድ ጊዜ ለመጣል ያሰበውን የኤክሳይዝ ታክስ በየአመቱ በትንሹ እየጣለ ካሰበበት ሊደርስ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አዲሱ የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ በአንድ ጠርሙስ ቢራ ዋጋ ላይ የዘጠኝ ብር ጭማሪ ይደረግበታል ተብሏል ፡፡ ሰዎች ከሚጠቀሙባቸው የቅንጦት ዕቃዎች ላይ ገቢ በመሰብሰብ በድህነት ላይ ለሚገኙ ዜጎች ለመደጎም እንዲያስችል ታስቦ የተጣለው የታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር እይታ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMየኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የኤክሳዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው። አዋ...0 Comments 0 Shares
-
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአመራርና በውሳኔ ሰጭነት ደረጃ የሴቶች ተሳትፎ መጠን በእጅጉ የጨመረ ሲሆን በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ፡፡ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ድርጅትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገ ጉባኤ ላይ እንደተመለከተው፤ ኢትዮጵያ ሴቶችን በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ በኩል ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች፡፡ በ2019 የተባበሩት መንግስታት ባወጣው ሪፖርትም፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ተጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀል በመድረኩ ባቀረቡት የዳሰሳ ጥናት ሴቶች በመራጭነት በ19 በመቶ፣ በተመራጭነት በ21 በመቶ ተሳትፏቸው መጨመሩን ገልጸዋል፡፡ ሴቶች በፓርላማ ተመራጭነትና ተሳትፎም ከ25 ዓመት በፊት ከነበረው 3 በመቶ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 38 በመቶ ማደጉን እንዲሁም በሚኒስትርነት ደረጃም ግማሽ ያህሉን መያዛቸውን አስታውቀዋል - ኮሚሽኑ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ሴቶች በከፍተኛ የውሳኔ ሰጭነት ያላቸው ድርሻ ውስን መሆኑንና መሻሻል እንዳለበት በሰሞኑ መድረክ ተመልክቷል፡፡በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአመራርና በውሳኔ ሰጭነት ደረጃ የሴቶች ተሳትፎ መጠን በእጅጉ የጨመረ ሲሆን በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለፀ፡፡ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ድርጅትና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ከትናንት በስቲያ አዲስ አበባ ውስጥ በተደረገ ጉባኤ ላይ እንደተመለከተው፤ ኢትዮጵያ ሴቶችን በውሳኔ ሰጪነት በማሳተፍ በኩል ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች፡፡ በ2019 የተባበሩት መንግስታት ባወጣው ሪፖርትም፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ በአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ መቀመጧም ተጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀል በመድረኩ ባቀረቡት የዳሰሳ ጥናት ሴቶች በመራጭነት በ19 በመቶ፣ በተመራጭነት በ21 በመቶ ተሳትፏቸው መጨመሩን ገልጸዋል፡፡ ሴቶች በፓርላማ ተመራጭነትና ተሳትፎም ከ25 ዓመት በፊት ከነበረው 3 በመቶ፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 38 በመቶ ማደጉን እንዲሁም በሚኒስትርነት ደረጃም ግማሽ ያህሉን መያዛቸውን አስታውቀዋል - ኮሚሽኑ፡፡ ይሁን እንጂ አሁንም ሴቶች በከፍተኛ የውሳኔ ሰጭነት ያላቸው ድርሻ ውስን መሆኑንና መሻሻል እንዳለበት በሰሞኑ መድረክ ተመልክቷል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMኢትዮጵያ በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከዓለም በ16ኛ ደረጃ ተቀምጣለች - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአመራርና በውሳኔ ሰጭነት ደረጃ የሴቶች ተሳትፎ መጠን በእጅጉ የጨመረ ሲሆን በሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ከአለም በ16ኛ ደረጃ ላይ እንደ...0 Comments 0 Shares
-
- ጠ/ሚ ዐቢይ፣ ገና ከጅምሩ፣ እንዲሁም ስልጣን ከያዙ በኋላ የሳተላይት ፕሮግራምና የህዋ ፕሮጀክት እንዲፋጠን አድርገዋል - የሕዋ ምርምርን የሚወዱ የፊዚክስ ምሁር፣ ወጣት ምሩቃንና አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ የህዋ ሳይንስ ማህበርን በመመስረት አስተዋጽኦ አበርክተዋል - ሼህ መሀመድ አልአሙዲ፣ በተለመደው ልግሳና፣ ለኢትዮጵያ የህዋ ተቋም 5 ሚሊዮን ዶላር በመስጠት ህይወት ዘርተውበታል - የሳውዲ መንግስት፣ በተሟላ ምህረት ነፃነታቸውን እንዲመልስላቸው፣ ጠ/ሚ ዐቢይ፣ በተለመደ ብልህነታቸው ቢጥሩ ለኢትዮጵያ ኩራት ነው 72 ኪሎ ግራም ሳተላይት ለማምጠቅ 6 ሚሊዮን ዶላር፣ በአዲስ አበባ እንጦጦ ላይ የመከታተያና የመረጃ ጣቢያ ለማደራጀት 3.ሚ ዶላር፣ (በድምር 300 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ) ገንዘብ ወጥቷል። ቀላል ሀብት አይደለም፡፡ ነገር ግን፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ እንደገፁት፣ የሳተላይት መረጃዎችን ለመግዛት፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ 350 ሚሊዮን ብር ትከፍላለች፡፡ ለህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚመደብ ገንዘብ፣ ሳተላይት ለማምጠቅ የሚውል ሀብት፣ በቀጥተኛ የኢኮኖሚ ስሌት ብቻ ቢታይ እንኳ፣ ያዋጣል፡፡ ጠቀሜታው ግን ከዚያም በላይ በእጅጉ የላቀ ነው፡፡ ደረጃውና መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጂ፣ ከህዋ ሳይንስ ውጭ፣ የሰው ልጅ ሕይወት እጅግ ጨለማ ነው፡፡ የሰዓትና የቀን፣ የወቅትና የዓመት ቆጠራ፣ በመቼ ወራት ቁር ወይም ሃሩር እንደሚሆን፣… የእርሻ ዝናባማ ወራትን፣ የአበባና የፍሬ ጊዜያትን፣ የአዝመራ ነፋሻማ ቀናትን አስቀድሞ መገመት፣ አድራሻንና የጉዞ አቅጣጫን መለየት… የሚቻለው ቀና ብለው ህዋን የሚቃኙ በሚመረምሩ፣ የፀሐይና የጨረቃ እንዲሁም የከዋክብት ሁኔታን እየተከታተሉ መረጃ የሚያደራጁ፣ በስሌትና በቀመር ጭምር ቅጥ ያለው እውቀትን በሚያዳብሩ ጠቢባን አማካኝነት ነው፡፡ ከሜስፓታሚያ እስከ ግብፅ፣ ከኢትዮጵያ እስከ አዝቴክ፣ ከዚያም እስከ ግሪክ ድረስ፣ ከህዋ ምርመርና እውቀት ተጠነጥሎ የተፈጠረ የጥንት ስልጣኔ የለም፡፡ ኢትዮጵያም ከጥቂት ከአለማችን የጥንታዊ ስልጣኔ ማዕከላት አንዷ እንደመሆኗ፣ በጥንታዊ የህዋ ሳይንስ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ጋር ስሟ ይነሳል፡፡ ትንሽም ይሁን ትልቅ፣ የትኛውም የስልጣኔ ጉዞ፣ ሁሌም ከህዋ ሳይንስ ጋር የተቆራኘ ነው። ዛሬ ደግሞ ቁልፍ የኢኮኖሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዚያ ላይ የደህንነትና የህልውና ቁልፍ አለኝታና መሳሪያ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት፣ የኢትዮጵያ የሳተላይት ፕሮጀክት ትርጉሙ ሰፊ ነው፡፡ የእውቀትና የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ፍቅርን በህጻናት ዘንድ ለማስፋፋት ይረዳል፡፡ በህዋ መስክ፣ የኢትዮጵያን አቅም ያሳድጋል - 20 ወጣቶች በዚህ አጋጣሚ በህዋ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ የእውቀትና የክህሎት ብቃትን አግኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በብዙ ገፅታዋ ትልቅ አገር ናት፡፡ በህዋ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ ከቀዳሚዎች የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ መሆን አለባት:: ለዚህም፣ የአሁኗ ሳተላይት መነሻ ትሆናለች ብለዋል - የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን፡፡በ10 ዓመታት ለተለያየ አገልግሎት የሚጠቅሙ፣ በመጠናቸውም የገዘፉ 15 ሳተላይቶችን የማምጠቅ እቅድ እንዳለ አብራርተዋል፡፡ ‹‹ETRSS - 1 ›› የተሰኘችው የኢትዮጵያ ሳተላይት፣ ለግብርናና ለደን ልማት፣ ለአየር ፀባይ ክትትልና ለማዕድን ጥናት ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት እንደምታገለግልም ተናግረዋል፡፡ ሳተላይቷ ግብርናን በተሻለ ምርምር ለማዘመንና በጠንካራ መረጃ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና እንዳላት ገልፀው፣ በማዕድን ጥናት በኩልም መሬት ሳይቆፈርና ብዙ ወጪ ሳይወጣ የት ቦታ ምን ማዕድን አለ እንዳለ ለመለየት እንደምትጠቅም ዶ/ር ሰለሞን አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት መረጃዎችን የምታገኘው እስከ 350 ሚሊዮን ብር በየአመቱ በመክፈል ነው፤ ሳተላይት ለማምጠቅ የሚወጣው ገንዘብ አዋጪ ይሆናል ብለዋል፡፡ሳተላይት ለማምጠቅ አራት ዓመታት መፍጀቱ የተለፀ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ወደ ህዋ የሚላኩት የኮሚኒኬሽን፣ የብሮድካስቲንግና ተጨማሪ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ግን ይሄን ያህል ጊዜ እንደማይፈጁ ተገልጿል፡፡- ጠ/ሚ ዐቢይ፣ ገና ከጅምሩ፣ እንዲሁም ስልጣን ከያዙ በኋላ የሳተላይት ፕሮግራምና የህዋ ፕሮጀክት እንዲፋጠን አድርገዋል - የሕዋ ምርምርን የሚወዱ የፊዚክስ ምሁር፣ ወጣት ምሩቃንና አቶ ተፈራ ዋልዋ፣ የህዋ ሳይንስ ማህበርን በመመስረት አስተዋጽኦ አበርክተዋል - ሼህ መሀመድ አልአሙዲ፣ በተለመደው ልግሳና፣ ለኢትዮጵያ የህዋ ተቋም 5 ሚሊዮን ዶላር በመስጠት ህይወት ዘርተውበታል - የሳውዲ መንግስት፣ በተሟላ ምህረት ነፃነታቸውን እንዲመልስላቸው፣ ጠ/ሚ ዐቢይ፣ በተለመደ ብልህነታቸው ቢጥሩ ለኢትዮጵያ ኩራት ነው 72 ኪሎ ግራም ሳተላይት ለማምጠቅ 6 ሚሊዮን ዶላር፣ በአዲስ አበባ እንጦጦ ላይ የመከታተያና የመረጃ ጣቢያ ለማደራጀት 3.ሚ ዶላር፣ (በድምር 300 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ) ገንዘብ ወጥቷል። ቀላል ሀብት አይደለም፡፡ ነገር ግን፣ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ እንደገፁት፣ የሳተላይት መረጃዎችን ለመግዛት፣ ኢትዮጵያ በየዓመቱ 350 ሚሊዮን ብር ትከፍላለች፡፡ ለህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚመደብ ገንዘብ፣ ሳተላይት ለማምጠቅ የሚውል ሀብት፣ በቀጥተኛ የኢኮኖሚ ስሌት ብቻ ቢታይ እንኳ፣ ያዋጣል፡፡ ጠቀሜታው ግን ከዚያም በላይ በእጅጉ የላቀ ነው፡፡ ደረጃውና መጠኑ ይለያይ እንደሆነ እንጂ፣ ከህዋ ሳይንስ ውጭ፣ የሰው ልጅ ሕይወት እጅግ ጨለማ ነው፡፡ የሰዓትና የቀን፣ የወቅትና የዓመት ቆጠራ፣ በመቼ ወራት ቁር ወይም ሃሩር እንደሚሆን፣… የእርሻ ዝናባማ ወራትን፣ የአበባና የፍሬ ጊዜያትን፣ የአዝመራ ነፋሻማ ቀናትን አስቀድሞ መገመት፣ አድራሻንና የጉዞ አቅጣጫን መለየት… የሚቻለው ቀና ብለው ህዋን የሚቃኙ በሚመረምሩ፣ የፀሐይና የጨረቃ እንዲሁም የከዋክብት ሁኔታን እየተከታተሉ መረጃ የሚያደራጁ፣ በስሌትና በቀመር ጭምር ቅጥ ያለው እውቀትን በሚያዳብሩ ጠቢባን አማካኝነት ነው፡፡ ከሜስፓታሚያ እስከ ግብፅ፣ ከኢትዮጵያ እስከ አዝቴክ፣ ከዚያም እስከ ግሪክ ድረስ፣ ከህዋ ምርመርና እውቀት ተጠነጥሎ የተፈጠረ የጥንት ስልጣኔ የለም፡፡ ኢትዮጵያም ከጥቂት ከአለማችን የጥንታዊ ስልጣኔ ማዕከላት አንዷ እንደመሆኗ፣ በጥንታዊ የህዋ ሳይንስ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት ጋር ስሟ ይነሳል፡፡ ትንሽም ይሁን ትልቅ፣ የትኛውም የስልጣኔ ጉዞ፣ ሁሌም ከህዋ ሳይንስ ጋር የተቆራኘ ነው። ዛሬ ደግሞ ቁልፍ የኢኮኖሚ ጉዳይ ሆኗል፡፡ በዚያ ላይ የደህንነትና የህልውና ቁልፍ አለኝታና መሳሪያ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት፣ የኢትዮጵያ የሳተላይት ፕሮጀክት ትርጉሙ ሰፊ ነው፡፡ የእውቀትና የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ፍቅርን በህጻናት ዘንድ ለማስፋፋት ይረዳል፡፡ በህዋ መስክ፣ የኢትዮጵያን አቅም ያሳድጋል - 20 ወጣቶች በዚህ አጋጣሚ በህዋ ቴክኖሎጂ ከፍተኛ የእውቀትና የክህሎት ብቃትን አግኝተዋል፡፡ ኢትዮጵያ በብዙ ገፅታዋ ትልቅ አገር ናት፡፡ በህዋ ሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኮኖሚ ከቀዳሚዎች የአፍሪካ አገራት መካከል አንዷ መሆን አለባት:: ለዚህም፣ የአሁኗ ሳተላይት መነሻ ትሆናለች ብለዋል - የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰለሞን፡፡በ10 ዓመታት ለተለያየ አገልግሎት የሚጠቅሙ፣ በመጠናቸውም የገዘፉ 15 ሳተላይቶችን የማምጠቅ እቅድ እንዳለ አብራርተዋል፡፡ ‹‹ETRSS - 1 ›› የተሰኘችው የኢትዮጵያ ሳተላይት፣ ለግብርናና ለደን ልማት፣ ለአየር ፀባይ ክትትልና ለማዕድን ጥናት ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት እንደምታገለግልም ተናግረዋል፡፡ ሳተላይቷ ግብርናን በተሻለ ምርምር ለማዘመንና በጠንካራ መረጃ ለማሳደግ ቁልፍ ሚና እንዳላት ገልፀው፣ በማዕድን ጥናት በኩልም መሬት ሳይቆፈርና ብዙ ወጪ ሳይወጣ የት ቦታ ምን ማዕድን አለ እንዳለ ለመለየት እንደምትጠቅም ዶ/ር ሰለሞን አብራርተዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት መረጃዎችን የምታገኘው እስከ 350 ሚሊዮን ብር በየአመቱ በመክፈል ነው፤ ሳተላይት ለማምጠቅ የሚወጣው ገንዘብ አዋጪ ይሆናል ብለዋል፡፡ሳተላይት ለማምጠቅ አራት ዓመታት መፍጀቱ የተለፀ ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ወደ ህዋ የሚላኩት የኮሚኒኬሽን፣ የብሮድካስቲንግና ተጨማሪ የመሬት ምልከታ ሳተላይቶች ግን ይሄን ያህል ጊዜ እንደማይፈጁ ተገልጿል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMወደ ከፍታ መምጠቅ ለኢትዮጵያ የሚመጥን የነገ ታሪክ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> - ጠ/ሚ ዐቢይ፣ ገና ከጅምሩ፣ እንዲሁም ስልጣን ከያዙ በኋላ የሳተላይት ፕሮግራምና የህዋ ፕሮጀክት እንዲፋጠን አድርገዋል<br /> - የሕዋ ምርምርን...0 Comments 0 Shares
-
ከ1ሺህ አምስት መቶ አመታት በላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ዘንድ በየአመቱ ጥር 11 የሚከበረው የጥምቀት በአል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡ ታውቋል፡፡ የአለም ቅርሶችን እያጠና በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ዘርፎች መዝግቦ እውቅና የሚሰጠው የተባበሩት መንግስታት የሣይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ረቡዕ ታህሳስ 1 ቀን 2012 ይፋ ባደረገው መረጃው፣ ጥምቀትን ጨምሮ አምስት የአለም ባህላዊ ቅርሶችን በማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች ዘርፍ፣ ‹‹በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት›› መመዝገቡን አስታውቋል፡፡የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በርካታ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ለአዲስ አድማስ ያብራሩት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃና ጥናት ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በመጨረሻም ዩኔስኮ ረቡዕ እለት መመዝገቡን ይፋ አድርጓል ብለዋል፡፡ የጥምቀት በዓል ከኢሬቻ፣ ጫንበላላ እና የደመራ መስቀል በዓል ቀጥሎ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው አራተኛው የማይዳሰስ ቅርስ መሆኑ የሀገሪቱን የቱሪስት መስህብነት የበለጠ የሚያሳድግ ይሆናል ብለዋል ረዳት ፕሮፌሰሩ፡፡ “ጥምቀት በየአካባቢው ሲከበር በልዩ ልዩ መልኮች ነው” ያሉት ምሁሩ፤ በአለም እውቅና ማግኘቱ ቅርሱን የበለጠ የመጠበቅ ኃላፊነት ይጥልብናል ብለዋል፡፡ ለዩኔስኮ በአለም ዙሪያ 49 ያህል ተመሳሳይ ባህላዊ ሁነቶች በማይዳሰሱ ቅርስነት እንዲመዘገቡ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም ሚዛን ደፍተው የተመዘገቡት ጥምቀትን ጨምሮ አምስት ያህል ብቻ መሆናቸው ታውቋል፡፡ከ1ሺህ አምስት መቶ አመታት በላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ዘንድ በየአመቱ ጥር 11 የሚከበረው የጥምቀት በአል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መመዝገቡ ታውቋል፡፡ የአለም ቅርሶችን እያጠና በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ ዘርፎች መዝግቦ እውቅና የሚሰጠው የተባበሩት መንግስታት የሣይንስ፣ የትምህርትና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ረቡዕ ታህሳስ 1 ቀን 2012 ይፋ ባደረገው መረጃው፣ ጥምቀትን ጨምሮ አምስት የአለም ባህላዊ ቅርሶችን በማይዳሰሱ የአለም ቅርሶች ዘርፍ፣ ‹‹በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት›› መመዝገቡን አስታውቋል፡፡የጥምቀት በዓል በዩኔስኮ ለማስመዝገብ በርካታ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን ለአዲስ አድማስ ያብራሩት የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃና ጥናት ባለስልጣን ም/ዳይሬክተር ረ/ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በመጨረሻም ዩኔስኮ ረቡዕ እለት መመዝገቡን ይፋ አድርጓል ብለዋል፡፡ የጥምቀት በዓል ከኢሬቻ፣ ጫንበላላ እና የደመራ መስቀል በዓል ቀጥሎ ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው አራተኛው የማይዳሰስ ቅርስ መሆኑ የሀገሪቱን የቱሪስት መስህብነት የበለጠ የሚያሳድግ ይሆናል ብለዋል ረዳት ፕሮፌሰሩ፡፡ “ጥምቀት በየአካባቢው ሲከበር በልዩ ልዩ መልኮች ነው” ያሉት ምሁሩ፤ በአለም እውቅና ማግኘቱ ቅርሱን የበለጠ የመጠበቅ ኃላፊነት ይጥልብናል ብለዋል፡፡ ለዩኔስኮ በአለም ዙሪያ 49 ያህል ተመሳሳይ ባህላዊ ሁነቶች በማይዳሰሱ ቅርስነት እንዲመዘገቡ ተጠይቆ የነበረ ቢሆንም ሚዛን ደፍተው የተመዘገቡት ጥምቀትን ጨምሮ አምስት ያህል ብቻ መሆናቸው ታውቋል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMጥምቀት በዩኔስኮ 4ኛው የኢትዮጵያ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ ተመዘገበ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> ከ1ሺህ አምስት መቶ አመታት በላይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያኖች ዘንድ በየአመቱ ጥር 11 የሚከበረው የጥምቀት በአል በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት መ...0 Comments 0 Shares
-
ስድስት ወራት በፊት ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰብ ፖለቲከኞች ተዋህደው የመሰረቱት ኢዜማ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝበትን የእራት መርሃ ግብር በነገው እለት በኢንተርኮንቲኔንታል የሚያካሂድ ሲሆን ገቢው ፓርቲውን በሃብትና ፋይናንስ ለማጠናከር ይውላል ተብሏል፡፡አንድ ሰው 2ሺህ ብር ከፍሎ በሚታደምበት በነገ ምሽቱ የእራት መርሃ ግብር ላይ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።እራት ግብዣው ላይ የሚታደሙ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢዜማና አባላቱ እንዲሁም አደረጃጀቱና አወቃቀሩ ግንዛቤ ይሰጣቸዋል በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎችም ይዝናናሉ ተብሏል መድረኩ ለኢትዮጵያ ተመሳሳይ ህልም ያላቸው ወገኖች በአንድነት ተገናኝተው እርስ በእርስ የሚተዋወቁበትና የግንኙነት መስመሮቻቸውን የሚያጠብቁበት ይሆናል ተብሏል፡፡ኢዜማ በዚህ የገቢና ግብዓት ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ ከገንዘብ በተጨማሪ በአይነት ማለትም ህንፃዎች፣ የቢሮ ቁሳቁሶች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ሀብቶችንም እንደሚያሰባስቡ ተገልጻል፡፡ ለቀጣዩ ምርጫ በሙሉ አቅሙ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጸው ኢዜማ ከ100 በላይ እውቅ ምሁራን የተሳተፈባቸው 18 የፖሊሲ ሰንዶችን ማዘጋጀቱን፣ ከ4 መቶ በላይ የምርጫ ወረዳዎችን አደራጅቶ ማጠናቀቁን፣ በ25 አለም ከተሞች የድጋፍ ማህበር ማቋቋሙንም አስታውቋል።ስድስት ወራት በፊት ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰብ ፖለቲከኞች ተዋህደው የመሰረቱት ኢዜማ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝበትን የእራት መርሃ ግብር በነገው እለት በኢንተርኮንቲኔንታል የሚያካሂድ ሲሆን ገቢው ፓርቲውን በሃብትና ፋይናንስ ለማጠናከር ይውላል ተብሏል፡፡አንድ ሰው 2ሺህ ብር ከፍሎ በሚታደምበት በነገ ምሽቱ የእራት መርሃ ግብር ላይ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦችና ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ይሳተፋሉ ተብሏል።እራት ግብዣው ላይ የሚታደሙ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢዜማና አባላቱ እንዲሁም አደረጃጀቱና አወቃቀሩ ግንዛቤ ይሰጣቸዋል በተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ስራዎችም ይዝናናሉ ተብሏል መድረኩ ለኢትዮጵያ ተመሳሳይ ህልም ያላቸው ወገኖች በአንድነት ተገናኝተው እርስ በእርስ የሚተዋወቁበትና የግንኙነት መስመሮቻቸውን የሚያጠብቁበት ይሆናል ተብሏል፡፡ኢዜማ በዚህ የገቢና ግብዓት ማሰባሰብ መርሃ ግብሩ ከገንዘብ በተጨማሪ በአይነት ማለትም ህንፃዎች፣ የቢሮ ቁሳቁሶች፣ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ሀብቶችንም እንደሚያሰባስቡ ተገልጻል፡፡ ለቀጣዩ ምርጫ በሙሉ አቅሙ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚገልጸው ኢዜማ ከ100 በላይ እውቅ ምሁራን የተሳተፈባቸው 18 የፖሊሲ ሰንዶችን ማዘጋጀቱን፣ ከ4 መቶ በላይ የምርጫ ወረዳዎችን አደራጅቶ ማጠናቀቁን፣ በ25 አለም ከተሞች የድጋፍ ማህበር ማቋቋሙንም አስታውቋል።ADDISADMASSNEWS.COMኢዜማ በነገው ምሽት የእራት ፕሮግራም 10 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዷል - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> ስድስት ወራት በፊት ዘጠኝ የፖለቲካ ድርጅቶችና ግለሰብ ፖለቲከኞች ተዋህደው የመሰረቱት ኢዜማ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ገቢ የሚያገኝበትን የእራት መርሃ ግብር በነ...0 Comments 0 Shares
-
ሳምንቱ የኢትዮጵያውያን ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ሳይጨምር ቢያንስ አምስት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ባበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ተግባር ተሸልመዋል፤ ተከብረዋል፡፡ አንጋፋው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ በህይወት ዘመናቸው ለሰብአዊነት ያደረጉት ተጋድሎ ሚዛን የሚደፋ ነው ሲል ዕውቅና የሰጠው ‹‹ዲፌንድ ዲፌንደርስ›› የተሰኘው የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ቡድን ነው፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትን በማቋቋም ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውና ለሰብአዊነት የወገነ ሰብዕናቸው ለሽልማቱ እንዳበቃቸው ቡድኑ አስታውቋል፡፡ ‹‹ዲፌንድ ዲፌንደርስ››፤ የፓን አፍሪካ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ኔትዎርክ፣ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በጋራ የመሰረቱትና ዋና መቀመጫውን ኡጋንዳ ያደረገ የመብት ተሟጋቾች ቡድን መሆኑ ታውቋል፡፡ ሌላዋ በሰብአዊ ተግባሯ በዚህ ሳምንት አለማቀፍ ሽልማት ያገኘችው ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራህቱ ነች፡፡ ፍሬወይኒ፤ በገጠር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶችን ስለ ወር አበባና የንጽህና አጠባበቅ ግንዛቤ በመስጠት፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነፃ በማደል ላበረከተችው ሰብአዊነት የተሞላበት ተግባር፣ ሴኤንኤን ‹‹የ2019 የአመቱ ጀግና›› ሲል ሸልሟታል፡፡ ለገጠር ታዳጊ ሴቶች እየታጠበ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ የሚያመርት ማሽን ሰርታ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም ታውቋል፡፡ ለፈፀሙት ታላቅ የሰብአዊነት ተግባር ሽልማት ያገኙት ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ታዋቂው የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ አመሃ መኮንን ናቸው፡፡ በተለይ ባለፉት አስር አመታት በፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ለሚከሰሱ ወገኖች በነፃ ጭምር ጥብቅና በመቆም የሚታወቁት አቶ አመሃ መኮንን፤ የፀረ ሽብር ህጉ ሰብአዊነትን የሚደፈጥጥ እንደሆነ በመግለጽ የሰላ ትችት ሲያቀርቡ ከነበሩ ግንባር ቀደም ኢትዮጵያውያን መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በፕ/ር መስፍንና በጥቂት ወዳጆቻቸው ከ27 አመት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል እንዲሁም ዋና ሰብሳቢ በመሆን ያገለገሉት አቶ አመሃ፤ የ2019 የፈረንሳይ ጀርመን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማትን አግኝተዋል፡፡ በተቀበሉት ሽልማት ዙሪያ ለአዲስ አድማስ አስተያየታቸውን የገለፁት አቶ አመሃ፤ ባለፉት 27 አመታት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደነበር ጠቅሰው፤ ‹‹ይህ ድርጊት እንዲቀንስና እንዳይፈፀም በርካቶች ታግለዋል፤ እኔና እኔን የመሰሉ ሰዎችም በዚህ በኩል የሚቻለንን አድርገናል›› ብለዋል፡፡ ‹‹መጀመሪያም ጉልበቴን ሳልቆጥብ ነበር የሰራሁት፤ ከዚህ በኋላም ለሰብአዊነት መረጋገጥ የምቆጥበው ጉልበት አይኖርም። አዳዲስ ፈተናዎችም እየመጡ ስለሆነ በነዚህም ላይ ከጓዶቼ ጋር ለመስራትና የጀመርነው የተስፋ መንገድ ተመልሶ እንዳይጨልም እታገላለሁ፤ አስተዋጽኦዬን እቀጥላለሁ›› ብለዋል አቶ አመሃ፡፡ የፖለቲካ አመራሮች በሚያደርጓቸው ንግግሮችና ቅስቀሳዎች በሰብአዊነት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መጠንቀቅ አለባቸው ያሉት አቶ አመሃ፤ ጉዳት ሲያጋጥምም ወገን ሳይለዩ በሰውነት ብቻ ማውገዝና ችግሩን መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ‹‹የ2019 በተፈጥሮ ሃብት ጉዳይ ተጽእኖ ፈጣሪ›› በሚል ከአለማቀፉ የደረጃዎችና ምዘና ኤጀንሲ በዚህ ሳምንት የተሸለሙ ሌላው ኢትዮጵያዊ ምሁር ደግሞ ዶ/ር መሃመድ አባኦሊ ናቸው። በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሃብትና የስነ ደን ሃብት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ አባኦሊ፤ የምርምር ጽሑፋቸው ከ90 የአለም ሀገራት ከቀረቡ 5ሺ 278 እጩዎች መሃል በአንደኝነት ተመርጦ ነው ለሽልማት የበቁት፡፡ሳምንቱ የኢትዮጵያውያን ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ሳይጨምር ቢያንስ አምስት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ባበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ተግባር ተሸልመዋል፤ ተከብረዋል፡፡ አንጋፋው ፖለቲከኛና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ በህይወት ዘመናቸው ለሰብአዊነት ያደረጉት ተጋድሎ ሚዛን የሚደፋ ነው ሲል ዕውቅና የሰጠው ‹‹ዲፌንድ ዲፌንደርስ›› የተሰኘው የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ቡድን ነው፡፡ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት እንዲከበር፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅትን በማቋቋም ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውና ለሰብአዊነት የወገነ ሰብዕናቸው ለሽልማቱ እንዳበቃቸው ቡድኑ አስታውቋል፡፡ ‹‹ዲፌንድ ዲፌንደርስ››፤ የፓን አፍሪካ የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች ኔትዎርክ፣ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበርና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ በጋራ የመሰረቱትና ዋና መቀመጫውን ኡጋንዳ ያደረገ የመብት ተሟጋቾች ቡድን መሆኑ ታውቋል፡፡ ሌላዋ በሰብአዊ ተግባሯ በዚህ ሳምንት አለማቀፍ ሽልማት ያገኘችው ኢትዮጵያዊቷ ፍሬወይኒ መብራህቱ ነች፡፡ ፍሬወይኒ፤ በገጠር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወጣት ሴቶችን ስለ ወር አበባና የንጽህና አጠባበቅ ግንዛቤ በመስጠት፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነፃ በማደል ላበረከተችው ሰብአዊነት የተሞላበት ተግባር፣ ሴኤንኤን ‹‹የ2019 የአመቱ ጀግና›› ሲል ሸልሟታል፡፡ ለገጠር ታዳጊ ሴቶች እየታጠበ ጥቅም ላይ የሚውል ሞዴስ የሚያመርት ማሽን ሰርታ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑም ታውቋል፡፡ ለፈፀሙት ታላቅ የሰብአዊነት ተግባር ሽልማት ያገኙት ሌላው ኢትዮጵያዊ ደግሞ ታዋቂው የህግ አማካሪና ጠበቃ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ አቶ አመሃ መኮንን ናቸው፡፡ በተለይ ባለፉት አስር አመታት በፀረ ሽብርተኝነት ህጉ ለሚከሰሱ ወገኖች በነፃ ጭምር ጥብቅና በመቆም የሚታወቁት አቶ አመሃ መኮንን፤ የፀረ ሽብር ህጉ ሰብአዊነትን የሚደፈጥጥ እንደሆነ በመግለጽ የሰላ ትችት ሲያቀርቡ ከነበሩ ግንባር ቀደም ኢትዮጵያውያን መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በፕ/ር መስፍንና በጥቂት ወዳጆቻቸው ከ27 አመት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ አባል እንዲሁም ዋና ሰብሳቢ በመሆን ያገለገሉት አቶ አመሃ፤ የ2019 የፈረንሳይ ጀርመን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሽልማትን አግኝተዋል፡፡ በተቀበሉት ሽልማት ዙሪያ ለአዲስ አድማስ አስተያየታቸውን የገለፁት አቶ አመሃ፤ ባለፉት 27 አመታት በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደነበር ጠቅሰው፤ ‹‹ይህ ድርጊት እንዲቀንስና እንዳይፈፀም በርካቶች ታግለዋል፤ እኔና እኔን የመሰሉ ሰዎችም በዚህ በኩል የሚቻለንን አድርገናል›› ብለዋል፡፡ ‹‹መጀመሪያም ጉልበቴን ሳልቆጥብ ነበር የሰራሁት፤ ከዚህ በኋላም ለሰብአዊነት መረጋገጥ የምቆጥበው ጉልበት አይኖርም። አዳዲስ ፈተናዎችም እየመጡ ስለሆነ በነዚህም ላይ ከጓዶቼ ጋር ለመስራትና የጀመርነው የተስፋ መንገድ ተመልሶ እንዳይጨልም እታገላለሁ፤ አስተዋጽኦዬን እቀጥላለሁ›› ብለዋል አቶ አመሃ፡፡ የፖለቲካ አመራሮች በሚያደርጓቸው ንግግሮችና ቅስቀሳዎች በሰብአዊነት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ መጠንቀቅ አለባቸው ያሉት አቶ አመሃ፤ ጉዳት ሲያጋጥምም ወገን ሳይለዩ በሰውነት ብቻ ማውገዝና ችግሩን መረዳት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ‹‹የ2019 በተፈጥሮ ሃብት ጉዳይ ተጽእኖ ፈጣሪ›› በሚል ከአለማቀፉ የደረጃዎችና ምዘና ኤጀንሲ በዚህ ሳምንት የተሸለሙ ሌላው ኢትዮጵያዊ ምሁር ደግሞ ዶ/ር መሃመድ አባኦሊ ናቸው። በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሃብትና የስነ ደን ሃብት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ አባኦሊ፤ የምርምር ጽሑፋቸው ከ90 የአለም ሀገራት ከቀረቡ 5ሺ 278 እጩዎች መሃል በአንደኝነት ተመርጦ ነው ለሽልማት የበቁት፡፡ADDISADMASSNEWS.COMኢትዮጵያውያን የተሸለሙበትና የነገሱበት ሣምንት - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> ሳምንቱ የኢትዮጵያውያን ነበር፡፡ ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን ሳይጨምር ቢያንስ አምስት ታላላቅ ኢትዮጵያውያን ባበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ተግባር ተሸልመዋል፤ ተ...0 Comments 0 Shares
-
ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ አስቸኳይ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤ እንዲጠራ የጠየቀ ሲሆን፤ ጉባኤው ሀገሪቱን ወደፊት ለማሸጋገር ወሳኝ ሁነት እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፤ ሀገሪቱ ከገባችበት ዘርፈ ብዙ ውስብስብ፣ ተደራራቢና ተመጋጋቢ ችግሮች፣ በዘላቂነት ልትወጣ የምትችለው በኢህአዴግና አጋሮቹ መዋሃድ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤ ሲካሄድ ብቻ ነው ብሏል፡፡ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤው፤ በእውቀትና እውነት የቆመ አሻጋሪ ሃሣብ የሚፈልቅበት ሀገራዊ ሁነት በመሆኑ ለሀገሪቱ ፖለቲካ ወደፊት መሻገር ወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ነው ብሏል - ፓርቲው በመግለጫው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፀጥታ አካላት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው ተጠናክረው እንዲወጡ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማትና ማህበራት፣ ህዝባዊ አደረጃጀቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ አክቲቪስቶች፣ አርቲስቶች፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አጠቃላይ ባለድርሻዎች በሙሉ ከስሜታዊነትና ወገንተኝነት ተላቀው ስለ ሀገር ሠላም፣ አንድነትና ማህበራዊ ቁርኝት እንዲሰብኩ ጥሪ አቅርቧል - ህብር ኢትዮጵያ:: መንግስት አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጥሪ እንዲያቀርብም ገለልተኛ ተቋማትና ፖለቲከኞች ግፊት እንዲያደርጉም ፓርቲው ጠይቋል፡፡ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ አስቸኳይ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤ እንዲጠራ የጠየቀ ሲሆን፤ ጉባኤው ሀገሪቱን ወደፊት ለማሸጋገር ወሳኝ ሁነት እንደሚሆን አስታውቋል፡፡ ፓርቲው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው፤ ሀገሪቱ ከገባችበት ዘርፈ ብዙ ውስብስብ፣ ተደራራቢና ተመጋጋቢ ችግሮች፣ በዘላቂነት ልትወጣ የምትችለው በኢህአዴግና አጋሮቹ መዋሃድ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤ ሲካሄድ ብቻ ነው ብሏል፡፡ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤው፤ በእውቀትና እውነት የቆመ አሻጋሪ ሃሣብ የሚፈልቅበት ሀገራዊ ሁነት በመሆኑ ለሀገሪቱ ፖለቲካ ወደፊት መሻገር ወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ነው ብሏል - ፓርቲው በመግለጫው፡፡ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፀጥታ አካላት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆነው ተጠናክረው እንዲወጡ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ተቋማትና ማህበራት፣ ህዝባዊ አደረጃጀቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካ ልሂቃን፣ አክቲቪስቶች፣ አርቲስቶች፣ የሚዲያ ባለቤቶችና አጠቃላይ ባለድርሻዎች በሙሉ ከስሜታዊነትና ወገንተኝነት ተላቀው ስለ ሀገር ሠላም፣ አንድነትና ማህበራዊ ቁርኝት እንዲሰብኩ ጥሪ አቅርቧል - ህብር ኢትዮጵያ:: መንግስት አስቸኳይ ሁሉን አቀፍ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጥሪ እንዲያቀርብም ገለልተኛ ተቋማትና ፖለቲከኞች ግፊት እንዲያደርጉም ፓርቲው ጠይቋል፡፡ADDISADMASSNEWS.COMአስቸኳይ የብሔራዊ መግባባትና ዕርቀ ሠላም ጉባኤ እንዲጠራ ተጠየቀ - Addis Admass Newspaper | Amharic news | Ethiopian news<p style="text-align: justify;"> ህብር ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ፤ አስቸኳይ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሠላም ጉባኤ እንዲጠራ የጠየቀ ሲሆን፤ ጉባኤው ሀገሪቱን ወደፊት ለማሸጋገር ወሳኝ ሁነት...0 Comments 0 Shares
More Stories