ወንድ ብቻውን ነው የሚያለቅሰው
=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤት ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ የማታ ሌሊት ነው የወንድ ልጅ
እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው
ብቻውን ነው የሚረታው
ችሎ ውጦ ተጨብጦ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ
መሽቶ ረፍዶ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር
የኋላ የኋላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ብቸኝነት ብቻ
ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ እንባ ወዙ እሚነጥብ
ብቻውን ነው ብቻውን ነው
የእንባ ጨለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥብው
ችሎ ውጦ ተጨብጦ ሰቀቀኑ በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ እንደ ደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤት ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተከናንቦ ተሸማቆ ተሸምቆ
የብቻ ብቸኝነቱ የጨለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ ሌት ወንድ ብቻውን ነው
እሚያለቅስ
--ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤት ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ የማታ ሌሊት ነው የወንድ ልጅ
እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው
ብቻውን ነው የሚረታው
ችሎ ውጦ ተጨብጦ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ
መሽቶ ረፍዶ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር
የኋላ የኋላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ብቸኝነት ብቻ
ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ እንባ ወዙ እሚነጥብ
ብቻውን ነው ብቻውን ነው
የእንባ ጨለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥብው
ችሎ ውጦ ተጨብጦ ሰቀቀኑ በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ እንደ ደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤት ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተከናንቦ ተሸማቆ ተሸምቆ
የብቻ ብቸኝነቱ የጨለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ ሌት ወንድ ብቻውን ነው
እሚያለቅስ
--ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
ወንድ ብቻውን ነው የሚያለቅሰው
=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=-=
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተገልሎ ተሸማቆ ተሸምቆ
ከቤት ሰው ተደብቆ
መሽቶ የማታ የማታ ሌሊት ነው የወንድ ልጅ
እንባው
ብቻውን ነው የሚፈታው
ብቻውን ነው የሚረታው
ችሎ ውጦ ተጨብጦ ተማምጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተወጥሮ
እንደ ደመና ተቋጥሮ
እውስጥ አንጀቱ ተቀብሮ
መሽቶ ረፍዶ ጀምበር ጠልቆ
የጨለማ ድባብ ወድቆ
በእንቅልፍ ጥላ ሲከበብ በዝምታ ሲዋጥ አገር
ፍጡር ሁሉ ተስለምልሞ ብቸኝነት ብቻ ሲቀር
የኋላ የኋላ ማታ
ምድር አገሩ በእፎይታ
ዓይኑን በእንቅልፍ ሲያስፈታ
ሁሉ በእረፍት ዓለም ርቆ ብቸኝነት ብቻ
ሲቀርብ
ያኔ ነው ወንድ ዓይኑ የሚረጥብ
የብቻ እንባ ወዙ እሚነጥብ
ብቻውን ነው ብቻውን ነው
የእንባ ጨለማ ለብሶ ነው
ወንድ ልጅ ወዙ እሚነጥብው
ችሎ ውጦ ተጨብጦ ሰቀቀኑ በሆዱ አጥሮ
በአንጀቱ ገበና ቀብሮ
ውሎ ጭጭ እፍን ብሎ እንደ ደመና ተቋጥሮ
ጣሩን ውጦ ተጣጥሮ
በሲቃ ግት ተሰትሮ
ከወዳጅ ከዘመድ ርቆ
ከቤት ሰው ተደብቆ
አንጀቱን በአንጀቱ ታጥቆ
ተሸሽጎ ተከናንቦ ተሸማቆ ተሸምቆ
የብቻ ብቸኝነቱ የጨለማ ልብሱ እስኪደርስ
በዓይን አዋጅ ሃሞቱ እንዳይረክስ
ቅስሙ በገበያ እንዳይፈስ
ተገልሎ በእኩለ ሌት ወንድ ብቻውን ነው
እሚያለቅስ
--ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
