አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 16 ዓ.ም ከአባታቸው ኤጀርሳ በዳኔ እና ከእናታቸው ዮንዢ ወርቅ በለጤ ተወለዱ።

በ14 አመታቸውም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል።

ከዚያም በአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር በመቀጠር በተዋናይት፥ የተለያዩ ተውኔቶችን ተጫውተዋል።

በወቅቱም የሴት ተዋናዮች ባለመኖራቸው የሴት ገጸ ባህሪ ተላብሰው ይጫወቱ ነበር።

የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆኑት አርቲስት ተስፋዬ መድረክ መሪ፣ ተዋናይ፣ ሙዚቀኛ ትርኢት አቅራቢ፣ ድምፃዊ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፣ ደራሲና ተረት ነጋሪ ነበሩ።

በገና፣ ክራር፣ መሰንቆ፣ አኮርድዮንና ትራምፔት ከሚጫወቷቸው የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

በድምጻዊነት ደግሞ “ዓለም እንደምን ነሽ ደህና ሰነበትሽ ወይ” እና “ፀሃይ” የተሰኙ ዘፈኖቻቸውን አድርሰዋል።

ከአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ በኋላም በብሄራዊ ቲያትር አገልግለዋል።

ሀ ሁ በስድስት ወር፣ ኤዲፐስ ንጉስ፣ አሉላ አባ ነጋ፣ ዳዊትና ኦርዮን፣ ኦቴሎ፣ አስቀያሚዋ ልጃገረድ እና ስነ ስቅለት ደግሞ አባባ ተስፋዬ የተወኑባቸው ተውኔቶች ናቸው።

ብጥልህሳ፣ ነው ለካ እና ጠላ ሻጯ የተሰኙ ተውኔቶችን ደግሞ በድርሰት አቅርበዋል።

ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የልጆች የተረት መጽሃፍትን ጽፈዋል።

አርቲስት ተስፋዬ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ድርጅት ውስጥ፥ የልጆች ጊዜ የሚል ፕሮግራም በመቅረጽ ለልጆች በሚጠቅም መልኩ አባታዊ ምክራቸውን ለልጆች ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

በዚህም አባባ ተስፋዬ የሚል መጠሪያን ማግኘት ችለዋል፤ ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስም ተወዳጅ ዝግጅታቸውን ከአባታዊ ምክራቸው ጋር አድርሰዋል።

ፕሮግራማቸውን ሲጀምሩ “ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች” የሚለው አባባላቸው በበርካቶች ዘንድ የሚታወስና የማይረሳ ነው።

አባባ ተስፋዬ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሳምንቱ መጨረሻ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የክብር ዶክትሬት አግኝተው ነበር።

አባባ ተስፋዬ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው በተወለዱ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 16 ዓ.ም ከአባታቸው ኤጀርሳ በዳኔ እና ከእናታቸው ዮንዢ ወርቅ በለጤ ተወለዱ። በ14 አመታቸውም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን ተከታትለዋል። ከዚያም በአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር በመቀጠር በተዋናይት፥ የተለያዩ ተውኔቶችን ተጫውተዋል። በወቅቱም የሴት ተዋናዮች ባለመኖራቸው የሴት ገጸ ባህሪ ተላብሰው ይጫወቱ ነበር። የበርካታ ሙያዎች ባለቤት የሆኑት አርቲስት ተስፋዬ መድረክ መሪ፣ ተዋናይ፣ ሙዚቀኛ ትርኢት አቅራቢ፣ ድምፃዊ፣ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች፣ የውዝዋዜ አሰልጣኝ፣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ፣ ደራሲና ተረት ነጋሪ ነበሩ። በገና፣ ክራር፣ መሰንቆ፣ አኮርድዮንና ትራምፔት ከሚጫወቷቸው የሙዚቃ መሳሪያዎች መካከል ይጠቀሳሉ። በድምጻዊነት ደግሞ “ዓለም እንደምን ነሽ ደህና ሰነበትሽ ወይ” እና “ፀሃይ” የተሰኙ ዘፈኖቻቸውን አድርሰዋል። ከአዲስ አበባ ባህልና ቲያትር አዳራሽ በኋላም በብሄራዊ ቲያትር አገልግለዋል። ሀ ሁ በስድስት ወር፣ ኤዲፐስ ንጉስ፣ አሉላ አባ ነጋ፣ ዳዊትና ኦርዮን፣ ኦቴሎ፣ አስቀያሚዋ ልጃገረድ እና ስነ ስቅለት ደግሞ አባባ ተስፋዬ የተወኑባቸው ተውኔቶች ናቸው። ብጥልህሳ፣ ነው ለካ እና ጠላ ሻጯ የተሰኙ ተውኔቶችን ደግሞ በድርሰት አቅርበዋል። ከዚህ ባለፈም የተለያዩ የልጆች የተረት መጽሃፍትን ጽፈዋል። አርቲስት ተስፋዬ በቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዠን ድርጅት ውስጥ፥ የልጆች ጊዜ የሚል ፕሮግራም በመቅረጽ ለልጆች በሚጠቅም መልኩ አባታዊ ምክራቸውን ለልጆች ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በዚህም አባባ ተስፋዬ የሚል መጠሪያን ማግኘት ችለዋል፤ ከድርጅቱ እስከለቀቁበት ጊዜ ድረስም ተወዳጅ ዝግጅታቸውን ከአባታዊ ምክራቸው ጋር አድርሰዋል። ፕሮግራማቸውን ሲጀምሩ “ደህና ናችሁ ልጆች የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንደምን አላችሁ ልጆች” የሚለው አባባላቸው በበርካቶች ዘንድ የሚታወስና የማይረሳ ነው። አባባ ተስፋዬ በኪነ ጥበብ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሳምንቱ መጨረሻ ከዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የክብር ዶክትሬት አግኝተው ነበር። አባባ ተስፋዬ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በመኖሪያ ቤታቸው በተወለዱ በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
WWW.FANABC.COM
FBC - አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 24 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ (አባባ ተስፋዬ) በ94 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አርቲስት ተስፋዬ ሳህሉ በቀድሞው የባሌ ክፍለ ሃገር ልዩ ስሙ ከዶ በተባለ ስፍራ ሰኔ 20 ቀን 19 1...
0 Comments 0 Shares