የፕሪምየርሊጉ ተሳታፊ ሳውዝሀምተን ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ በክለቡ የተሰናበቱት የክላውድ ፒዮል ምትክ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን አሳውቋል።

በሊጉ የስምንተኛ ደረጃን ያገኙት እንዲሁም በ EFL ዋንጫ ለፍጻሜ መድረስ ችለው የነበሩት ክላውድ ፑኤልን ያሰናበተው ሳውዝሀምፕተን ማውሪሲዮ ፔሌግሪኖን ቀጥሯል።

የቀድሞ የአላቬስ አሰልጣኝ የነበሩት አርጀንቲናዊው ፔሌግሪኖ “ቅዱሰኖቹን” ለማሰልጠን የ ሶስት አመት ኮንትራት የፈረሙ ሲሆን ከማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በኋላ ሌላኛው አርጀንቲናዊው የክለቡ አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

“የሳውዝሀምፕተን አዲሱ አሰልጣኝ በመሆኔ በጣም ተደስቻለው። ክለቡ ጠንካራ፣የተረጋጋ እና አዝናኝ እግርኳስ የሚጫወት ስም ያለው ቡድን ነው።” በማለት አዲሱ አሰልጣኙ ያላቸው ፍልስፍና ከክለቡ አደረጃጀት ጋር አብሮ የሚሄድ እንደሆነ ገልጸዋል።

“ጨዋታዎችን ማሸነፍ እፈልጋለው።ውጤታማ በመሆን የቡድን መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ለመገንባት እፈልጋለው።” ሲሉም ፔሌግሪኖ ጨምረው ተናግረዋል።

ፔሌግሪኖ በላሊጋ አላቬስን ማሰልጠን የቻሉ ሲሆን በግንቦት ወር ላይ ከቡድኑ ጋር ከመለያየታቸው በፊት በስፔን ዋንጫ አላቬስን በመምራት ባርሴሎን መግጠም ችለው እንደነበር ይታወሳል።
የፕሪምየርሊጉ ተሳታፊ ሳውዝሀምተን ከአንድ አመት ቆይታ በኋላ በክለቡ የተሰናበቱት የክላውድ ፒዮል ምትክ አዲስ አሰልጣኝ መቅጠሩን አሳውቋል። በሊጉ የስምንተኛ ደረጃን ያገኙት እንዲሁም በ EFL ዋንጫ ለፍጻሜ መድረስ ችለው የነበሩት ክላውድ ፑኤልን ያሰናበተው ሳውዝሀምፕተን ማውሪሲዮ ፔሌግሪኖን ቀጥሯል። የቀድሞ የአላቬስ አሰልጣኝ የነበሩት አርጀንቲናዊው ፔሌግሪኖ “ቅዱሰኖቹን” ለማሰልጠን የ ሶስት አመት ኮንትራት የፈረሙ ሲሆን ከማውሪሲዮ ፖቸቲኖ በኋላ ሌላኛው አርጀንቲናዊው የክለቡ አሰልጣኝ መሆን ችለዋል። “የሳውዝሀምፕተን አዲሱ አሰልጣኝ በመሆኔ በጣም ተደስቻለው። ክለቡ ጠንካራ፣የተረጋጋ እና አዝናኝ እግርኳስ የሚጫወት ስም ያለው ቡድን ነው።” በማለት አዲሱ አሰልጣኙ ያላቸው ፍልስፍና ከክለቡ አደረጃጀት ጋር አብሮ የሚሄድ እንደሆነ ገልጸዋል። “ጨዋታዎችን ማሸነፍ እፈልጋለው።ውጤታማ በመሆን የቡድን መንፈስ ሙሉ ለሙሉ ለመገንባት እፈልጋለው።” ሲሉም ፔሌግሪኖ ጨምረው ተናግረዋል። ፔሌግሪኖ በላሊጋ አላቬስን ማሰልጠን የቻሉ ሲሆን በግንቦት ወር ላይ ከቡድኑ ጋር ከመለያየታቸው በፊት በስፔን ዋንጫ አላቬስን በመምራት ባርሴሎን መግጠም ችለው እንደነበር ይታወሳል።
0 Comments 0 Shares