በጎንደር ከተማ በአጋቾች የተወሰደችው የ2 ዓመት ህፃን ግድያ ቁጣ ቀሰቀሰ
በድጋሚ የታደሰ
በጎንደር ከተማ ባለፈው አርብ ባልታወቁ ሰዎች ታግታ ከተወሰደች በኋላ ግማሽ ሚልየን ብር ተጠይቆባት የነበረችው የ2 አመት ህፃን በትላንትው እለት መገደሏ ከተሰማ ወዲህ በከተማው ነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል፡፡
አጋቾቹ ህፃኗን የገደሏት ወላጆቿ በድርድር እንዲከፍሉ የጠየቁትን 300 ሺ ብር ከተቀበሉ በኋላ ነው:: ዜናውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥተው ቁጣቸውን አሰምተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን...