የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች የሚቀበልበትን አሰራር ሥራ ላይ ለማዋል ተዘጋጅቻለሁ አለ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከመጪው 2017 የትምህርት አመት ጀምሮ፣ ተማሪዎችን የሚቀበልበትን አዲስ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱን አስታወቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ፣ በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያው የመንግስት ራስገዝ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋም ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፣ በመጪው አመት በዩኒቨርሲቲው የሚማሩ ተማሪዎች በመንግስት የሚመደቡ ሳይሆኑ፣ በተቋም መስፈርት መሰረት የሚመለመሉ...